Learn More:
Introduction to Qubee Afaan Oromoo for Amharic speakers-በላቲን ቁቤ ኣፋን ኦሮሞ መጻፍ እና ማንበብ [አዘጋጅ፡ ዶ/ር ሀብታሙ ገበየሁ]
መግቢያ
ይህ ጽሁፍ ኣፋን ኦሮሞን እንደ ሁለተኛ ቋንቋቸዉ መማር ለሚፈልጉ ሰዎች ቁቤ ኣፋን ኦሮሞ እንዴት እንደሚጻፍ እና እንዴት እንደሚነበብ የሚያብራራ ትምህርታዊ ጽሁፍ ነው።
ከሁለት ዓመት በፊት “Riqicha/ሪቂቻ Afaan Oromoo grammar for beginners/ ኦሮምኛ ሰዋስዉ ለጀማሪወች” የተሰኘ መጽሃፍ ኣሳትሜ ነበር። መጽሃፉ ከታተመ አንስቶ የመጽሃፉን ትምህርቶች በቴላግራም እና በዩቲዩብ እያጋራሁ እገኛለሁ። በቴሌግራሙ ትምህርት እንደተረዳሁት በሊቲን የተጻፈው ቁቤ አፋን ኦሮሞ ለማንበብ የቸገራቸው ሰዎች የላቲኑ ጽሁፍ ኣነባበብ በኣማርኛ እንዲጽፈላቸዉ ይጠይቃሉ። በእኔ ተሞክሮ የቁቤውን ላቲን ጽሁፍ አነባበብ በአማርኛ ከማስቀመጥ ይልቅ የቁቤው ላቲን ጽሁፍ እንዴት እንደሚጻፍ እና እንዴት እንደሚነበብ በማስረዳት ሰዎች በቁቤ አፋን ኦሮሞ (በላቲን ፊደል) መጻፍ እና ማንበብ እንዲለማመዱ ማድረግ የተሻለ ነው። እኔ የሄድኩበት መንገድም ይኸዉ ነው።
በቁቤ አፋን ኦሮሞ ለማንበብ እና ለመጻፍ እንደሚታሰበው ከባድ አይደለም። በዚህ ጽሁፍ ላሳያችሁ የምፈልገውም በቁቤ አፋን ኦሮሞ እንዴት በቀላሉ መጻፍ እና ማንበብ እንደምንችል ነው። እንግልዝኛ ፊደል የሚለይ ሰው ይህን ጽሁፍ ካነበበ በኋላ በቁቤ አፋን ኦሮሞ በቀላሉ ማንበብ እና መጻፍ ይችላል!
Dr. Habtamu Gebeyheu can be contacted By Email: doctorhabtamujenberei@gmail.com
![](https://mylibrarianship.wordpress.com/wp-content/uploads/2024/06/maxresdefault-1.jpg?w=1200)