የወለጋ ታሪክ ሰነዶች ከ1880ዎቹ እስከ 1920ዎቹ እ.ኤ.አ [Historical Document]

Alessandro Triulzi እና professor Tesema Ta’a Documents for Wollega history(1880s-1920s ) በአረብ አፍሪካ ኦሬንታል የጥናትና ምርምር ትምህርት ክፍል በናፓሊስ ዩኒቪርሲቲ ትብብርና ድጋፍ በ326 ገጽ የታተመ መጽሃፍ ነው።

ይህንን መጽሃፍ ለማግኘት ለአለፊት ሶስት አመታት ብዙ ጥረት አድርጊያለሁ ግን እስከ ዛሬው ቀን አልተሳካልኝም ነበር። መጽሃፊ ምንም እንኳን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ቢታተምም በአልታወቀ ሁኔታ መጽሃፍ ከገቢያ ደብዛው የጠፋ ብቻ ሳይሆን ዩኒቨርሲቲውም መጽሃፊ ተፈላጊ መሆኑ እየታወቀ ድጋሜ ለማሳተም ጥረት አላደረገም። ፕሮፌሰር ተሰማ ታዓን በቤተሰብ በኩል አንድ ኮፒ እንዲሰጡኝ አስጠይቄ እሳቸው ራሳቸው ለማንም የማያውሱት የማይሰጡት አንድ ኮፒ ብቻ መጽሃፊ እንዳላቸው ለማወቅ ቻልኩ። ዛሬ ግን ተሳክቶልኝ ይህንን ታሪካዊ የወለጋ ዶክመንቶችን መጽሃፍ ለማግኘት ችያለሁ ። እስኪ ስለወለጋ ከ1880ዎቹ እስከ 1950ዎቹ ድረስ ስላሉ አንዳንድ ታሪኮችን ላካፍላችሁ።

አፄ ሚኒሊክ በራስ ጎበና ዳጩ ጦር መሪነት ምዕራብ ኦሮሚያን የጊቤ መንግስትንና ወለጋን በኃይል ከተቆጣጠሩና ካስገበሩ በኃላ የወለጋውን ገዥ ደጃዝማች ኩምሳ ሞሮዳን ክርስትና አስጠምቀው የክርስትና አባታቸው ሁነው ስማቸውንም ወደ ገብረእግዚአብሄርነት አስቀይረውት ነበር። ደጃዝማች ኩምሳም ክርስትና ከመጠቃቸው በፊት የአባታቸውን የዋቄፈና እምነት ተከታይ የነበሩ ሲሆን ክርስትና ከተቀበሉ በኃላ በክርስትና አባታቸው እና በነብስ አባታቸው ቄስ በኩል “እስከዛሬ ለነበረብዎት ሃጢያት እግዚአብሔር ይቅር እንዲልዎት የፍልሰታ ፆም እንዲፃሙ” በጥብቅ ተነግሯቸው እያለ በመሃል እምዩ ደጃዝማች ኩምሳን በጾሙ አጋማሽ ወቅት አግኝተዋቸው ” ደጃዝማች ገብረ እግዚአብሄር ፆሙ እንዴት ይዞሃል?” ብለው ሲጠይቋቸው ደጃዝማችም አይ ጃንሆይ “አጓት ባይኖር አንዘልቀውም ነበር” ብለው መለሱላቸው ። ለካ ደጃዝማች ገብረእግዚአብሄር እነ ፍካሬ እየሱስ ታምረ ማርያም የተክልዩ ገድል የመሳሰሉት መጽሃፎች ስጋ: ወተት : ቅቤ አትብሉ እንጅ አጓት አትብሉ የሚል ስላልነበር የፍልሰታን ጦም አጓታቸው እየነፊ ቀን ቀን በእነ እምዩ ዘመዶች ፊት ‘መድኃኒያለምን’ ብለው ይምሉ እና ማታ ማታ በዋቄፈናው ዋቃጉራቻ ስም ይምሉ ይፀልዩ ነበር ይባላል።ደጃዝማች ኩምሳ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ወረራን በዘዴ የተከላከሉ ጀግና ነበሩ።

ስለአንዳንድ ቤተሰቦቻቸውና ስጋ ዘመዶቻቸው ደግሞ ለጠቅላላ እውቀት እንዲሆናችሁ ። ወ/ሮ አስካሌ ጆቴ ልጅ እያሱ ሚላኤልን አግብተው ነበር ። ደጃዝማች ካሳ የሞቲ ጆቴ ቱሉ የልጅ ልጅ ሲሆን የመጀመሪያው የፊንፊኔን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና የወለጋ ጠቅላይ ግዛት ገዥ ነበሩ ፣ የመጫና ቱለማ ከፍተኛ ሴት አመራር የነበረችዋ ወ/ሮ አፀደማርያም ሀብተማርያም የደጃዝማች ሀብተማርያም ገብረ እግዘአብሔር (ኩምሳ ሞረዳ) ልጅና የብርጋዴር ጄነራል ሙሉጌታ ቡሊ ሁንዴ ባለቤት ነበረች፡፡ አብዛኛዎቹ የምዕራብ ወለጋ ገዢ የነበረው ደጃዝማች ጆቴ ቱሉና የሌቃ ነቀምቴ ገዢ የነበረው የደጃዝማች ሀብተማርያም ገ/እግዚአብሔር ልጆች፣ ወንዱም ሆነ ሴቱ አብዛኛዎቹ ጋብቻ የፈፀሙት የፓለቲካ ጋብቻ ሲሆን በተለይም ከሸዋ ነገስታት፣መሳፍንትና መኳንንት ጋር ነበር፡፡

Source: ባላምባራስ ነጋሽ Negash Qemant

A related research work is available in .pdf version on Finfinnee University website click on the below button to download:

Author: Mulugeta Woldetsadik, Librarian/Information Professional at Hawassa University (HU), Ethiopia

Mulugeta Woldetsadik, Librarian/Information Professional @ Hawassa University, , Sidama Region, Ethiopia

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: