New Book_Coming Soon! ነገ እሁድ ከ2:30 ጀምሮ በኦሮሚያ ባሕል ማዕከል በድምቀት ይመረቃል።


#መረጃ_ቶጲያ‼️ ከመፅሃፍ አስመራቂ ኮሚቴው

ቶጲያ መጽሐፍ እስከዛሬው ዕለት ድረስ ከ5ሺ ኮፒ በላይ በቅድሚያ መሸጡንና ገዥዎች መጽሐፋቸውን ለመረከብ ምርቃቱን እየጠበቁ እንደሚገኙ ተሰምቷል። መጽሐፉ በእንግሊዝኛና በኦሮምኛ ቋንቋዎች ሊተረጎም ሥራ መጀመሩም ተገለጿል። ||ህዳር 15 ቀን 2015 ዓ/ል አዲስ አበባ ፤ ኢትዮጵያ ኅዳር 18 ቀን 2015 ዓ.ል በኦሮሚያ ባሕል ማዕከል እንደሚመረቅ ቀጠሮ የተያዘለት “ቶጲያ” መጽሐፍ ገና ከማተሚያ ቤት ሳይወጣ 5ሺ ኮፒ የተለያዩ መ/ቤቶችና ግለሰቦች መግዛታቸውን የምረቃ አዘጋጅ ኮሚቴው ገለጸ።

ኮሚቴው ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ የታላቋን ኢትዮጵያ ያልተዳሰሱ ታሪኮች ይበልጥ በጥልቀትና ሥነጽሑፋዊ ደረጃውን በጠበቀ መልክ የተዳሰሰበት ቶጲያ መጽሐፍ የፊታችን እሁድ ታላላቅ ደራሲያን፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የኪነጥበብ ሰዎች የሃይማኖት አባቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት እንደሚመረቅ ገልጿል።

ደራሲው ነጃሺ ከድር ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በኢንጂነሪነግ የተመረቀ እንደሆነም መግለጫው ያስረዳል። መጽሐፉ 577 ገጽ የያዘ ከ600 በላይ ማጠቀሻ መጽሐፍትን እንደተጠቀመም ተገልጿል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ መጽሐፉ በኦሮምኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች ለመተርጎም በየቋንቋዎቹ የበቁ ደራሲያንና ተርጓሚዎች ጋር ተነጋግሮ ሥራ መጀመሩን የምረቃ አዘጋጅ ኮሚቴው አክሎ ገልጿል። በሀገራችን በርካታ ቋንቋ ተናጋሪዎች ባላቸው የሱማሊኛ፣ የአፈርኛና የትግርኛ ቋንቋ ለመተርጎምም በእቅድ ደረጃ እንደተያዘ ኮሚቴው አክሎ ገልጿል። በመጨረሻም ኮሚቴው እሁድ ህዳር 18 ቀን 2015 በኦሮሞ ባሕል ማዕከል በሚካሄደው የምረቃ በዓል ሁሉም ኢትዮጵያዊያን እንዲገኙ ጥሪ በማቅረብ መግለጫውን ቋጭቷል።

Advertisement
%d bloggers like this: