[Obituary] Ali Bira -The King of Oromia Music Has Passed Away {RIP}


Baay’ee ulfaata, waan jedhee ibsu hin qabu. Oromiyaan abbaa ishee, hangafa hundaa, mallattoo tokkummaa fi bilisummaa ishee dhabdeetti.

የኦሮምኛ ቋንቋና የኦሮምኛ ሙዚቃ ሬዲዩ ይሰብራል የሚለውን የጽንፈኞችንና የአፄውን ስርዓት ተረት ተረትና ኃላቀር አመለካከት ሰብሮ ያሳየ የለውጥ ሃዋርያ: አብዩተኛ : የኦሮሙማ የጥበብ ቸጎቬራ-አዴሮ Rest in Power

ባላምባራስ ነጋሽ Negash Qemant






“እኔ ኦሮሚኛ ዘፈን ስዘፍን ልክ እንደ Taboo (አስነዋሪ) ነገር ነበር፤ በተለይ ሞደርን የሆነ የኦሮሚኛ ዘፈን ስለምዘፍን። የነበሩት ስርዓቶች ጫና ነበር።እና ለእነኝህ አይነት ችግሮች መፍትሔ ለማግኘት እነኝህን የሚያንጸባርቁ ግጥሞች ‘ስርዓቱ ቆንጆ አይደለም፣ ትክክል አይደለምና መስተካከል አለበት’ የሚል አይነት መልእክት ያዘሉ ግጥሞችን ሳገኝ ያንን አይነት ዘፈኖችን እሰራለሁ።በዚያን ጊዜ ብዙ ጫና ነበር። ሙዚቃ ቤቶች የኦሮሚኛ ሙዚቃን ለገበያ ማቅረብን እንደ taboo ወይንም የተከለከለ ወይንም እንደ አክሳሪ ነገር አድርገው ነው የሚያዩት። ግን እኛ ዓላማችን ትግል ስለነበረ ገንዘብ አገኘን አላገኘን እኛው ሪኮርድ እያደረግን በነጻ ለሰው እንሰጥ ነበር። እና በዚያ መልኩ ነበር የኦሮሚኛ ሙዚቃ ቀስ ብሎ በሰዎች ዘንድ ተደማጭነትን ያገኘው። ከዚያ በኌላም ለማርኬት የሚሆኑት በሳንሱር ነው የሚያልፉት። እናም ከብዙ ቆይታና ትግል በኌላ ነበር ሙዚቃ ቤቶች መውሰድና ማሳተም የጀመሩት። ያኔም ቢሆን እንደ ልብ አልነበረም የኦሮሚኛ ሙዚቃ የሚወስዱት። “

ክቡር ዶ/ር አሊ ቢራ ከEBS ጋር ካደረገው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ ነው።
አንደ ዛሬ አንድ ሲንግል በሚልዮን በሚሸጥበት ዘመን የጀመረ ሳይሆን እንደ በጎ አድራጊ ድርጅት በራሱ ኪሳራ በማሳተም እና በነጻ በማደል ነው በዚያን ወቅት እንደ ነውር የሚቆጠረውን የአፋን ኦሮሞ ቌንቌ ዘፍኖች ዛሬ ከደረሱበት ደረጃ እንዲደርሱ የማይነቃነቅ መሰረት የጣለው።
አሊ በራሱ ታሪክ ነው፤ ተተርኮ የማያልቅ ታሪክ!

Advertisement
%d bloggers like this: