[የመጽሐፍ_ምረቃ] ሎቄን በደም ሳይሆን በቀለም አሰበናት!!


 የመጽሐፍ_ምረቃ_በሀዋሳ፣ሲዳማ፣ኢትዮጵያ

የሲዳማ ህዝብ ለነፃነቱ ከከፈለው መስዋዕትነት አንዱ የሆነውLooqqe Massacre

በደራሲ ተመስገን ታደሰ የተጻፈ እውነተኛ ታሪክ ላይ መሰረት ያደረገው እና#ሎቄ የተሰኘው የልብወለድ መጽሐፍ ነገ እሁድ ከቀኑ 8:00 ሰዓት በሲዳማ ባህል አደራሽ ይመረቃል።

በዕለቱ የተለያዩ እንግዶች የምገኙ ሲሆን ከነኚህ ውስጥ የሃገር ሽማግለዎች፥ የሐይማኖት አባቶች፥ አመራሮች፥ ደራሲያን፥ የኤጄቶ አባላት እና የሎቄ እልቅት ጊዜ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው እና ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ወገኖች ተጋብዘዋል።

እርስዎም በዚህ ታሪካዊ እና አስተማሪ የልቦለድ መጽሐፍ ምረቃ ላይ እንዲታደሙ እና የስነጽሁፍ ፋናወጊዎችን እንዲያበረታቱ ተጋብዘዋል።

ስለ ሎቄ ያገባኛል የምል ትውልድ ፣ ነባር ታጋዮች በክብር እንዲገኙ ጥር ተደርጎላቸዋል።

ምንጭ፣ አፊኒ_ሚዲያና_ኮሙኒኬሽን

Advertisement
%d bloggers like this: