ሩዋንዳ ላይ በተፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ  የቤተክርስቲያን እና የእስልምና ሚና….


.

በአፍሪካ ግጭቶች ላይ ጥልቅ ምርምር ካደረጉት መካከል Pro.Timothy Longman በግንባር ቀደምትነት ተጠቃሽ ሲሆን “Christianity and Genocide in Rwanda “
(ክርስትናና የዘር ማጥፋት ዘመቻ በሩዋንዳ)
በሚል  መጽሐፉ “ሩዋንዳ በክርስቲያኖች የተሞላች አገር” እንደሆነችና 90 በመቶ ገደማ የሚሆነው ሕዝብ የቤተ ክርስቲያን አባል እንደሆነ ተናግሯል።

  ፕሮፌሰርሩ እንደገለጹት በዘር ጭፍጨፋው ወቅት ቄሶችንና ፓስተሮችን ጨምሮ በርካታ ሁቱዎች የቤተ ክርስቲያናቸው አባላት የሆኑ ቱትሲዎችን ገድለዋል። “ለቤተ ክርስቲያናቸውና ለእምነት አጋሮቻቸው ያላቸው ታማኝነት ካቶሊኮች ሌሎች ካቶሊኮችን፣ ኦርቶዶክሶች ሌሎች ኦርቶዶክሶችን፣ ፕሮቴስታንቶች ደግሞ ሌሎች ፕሮቴስታንቶችን ከመግደል ያላገዳቸው ለምን ይሆን?” በማለት ጠይቀዋል።

የሩዋንዳ አብያተ ክርስቲያናት ከዘር ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘ ያላቸው ሚና ሥር የሰደደ ነው። የዘር ማጥፋት ዘመቻው ከመካሄዱ ከአሥርተ ዓመታት በፊትም የሩዋንዳ ባለሥልጣናት ሥልጣናቸውን ላለማጣት ሲሉ ከቀሳውስት ጋር ይመሳጠሩ ነበር፤ ይህን የሚያደርጉበት አንዱ መንገድ በሕዝቡ መካከል የዘር መከፋፈል መፍጠር ነበር። ፕሮፌሰር ቲሞቲ ሎንግማን “በሩዋንዳ ቤተ ክርስቲያኖች ውስጥ የሚሰበከው ‘ስለ ፍቅርና ስለ አንድነት’ አልነበረም” በማለት ጽፈዋል።

ጽንፈኛ የሆኑ ሁቱዎች ሥልጣን ከጨበጡ በኋላም የቀሳውስት ድጋፍ አልተለያቸውም። የዘር ጭፍጨፋው ሲጀምር የሃይማኖት መሪዎች ድርጊቱን አላወገዙም፤ ከዚህ ይልቅ ምዕመኖቻቸው መንግሥትን እንዲታዘዙ ያበረታቱ ነበር። ፕሮፌሰር ቲሞቲ ሎንግማን እንደጻፉት “ብዙ የቤተ ክርስቲያን አባላት ግድያው በሃይማኖት መሪዎቹ ዘንድ ተቀባይነት እንዳገኘ ደምድመው ነበር።” እንዲያውም አንዳንዶች ለግድያ ከመሰማራታቸው በፊት ቤተ ክርስቲያን ገብተው ይጸልዩ እንደነበር ገልጸዋል።

ሩዋንዳ፦ ሞት፣ ተስፋ መቁረጥ እና ዓመፅ  (እንግሊዝኛ) የተባለው የሰብዓዊ መብቶች ሪፖርት እንዲህ ብሏል፦ “በሩዋንዳ የተፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ በሁሉም ትላልቅ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ያለውን ሥነ ምግባራዊና መንፈሳዊ ውድቀት በግልጽ የሚያሳይ ነበር።”በሩዋንዳ በወቅቱ ጭፍጨፋው ከቆመ እና ሰላም ከሰፈነ ቦሀላ ጥቂት የሚባሉ አማኞች የነበሩት አስልምና  እምነት ተከታዮች ዛሬ  በሩዋንዳ በዝተው ይገኛሉ። እንደ ምክንያት የተወሰደውም በግድያው ወቅት ዘር ቀለም ሳይለዩ የሰው ልጅን በቤተ እምነታቸው የደበቁት እና በህይወት ተርፈው ምስክርነት የተሰለጠላቸው የሙስሊም መስጂዶች በመሆናቸው ነው።

Advertisement

Author: Mulugeta Woldetsadik, Librarian/Information Professional at Hawassa University, Ethiopia [21st Century LIS Network: Information_Knowledge Retrieval & Dissemination Platform]

Mulugeta Woldetsadik, Librarian/Information Professional @ Hawassa University, , Sidama Region, Ethiopia

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: