ማሳሰቢያ፡-
በዚህ መረጃ የ320 የግል እና 20 የመንግስት በድምሩ 340 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የእውቅና ፈቃድ መረጃ ተካቷል፤ መረጃው እስከ የካቲት 2014 ዓ.ም ድረስ ያለውን የተቋማት እና የትምህርት መስኮችን የእውቅና ፈቃድ መረጃ የሚያሳይ ሲሆን፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የእውቅና ፈቃድ ባልታደሰባቸው የትምህርት መስኮች አዲስ ተማሪ መቀበል የተከለከለ መሆኑን ለማመልከት በቀይ ቀለም ምልክት ተድርጎባቸዋል፡፡ በዚሁ መሰረት የእውቅና ፈቃድ ባልተሰጠበት ካምፓስና የትምህርት መስክ፤ እንዲሁም የእውቅና ፈቃድ እድሳት ጊዜያቸው ባለፈባቸው የትምህርት መስኮች ተማሪ ተቀብሎ ማስተማር የማይቻል በመሆኑን እና ለአንዱ ካምፓስ የተሰጠው የእውቅና ፈቃድ ለሌላው የማያገለግል እንደሆነ ታውቆ አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ ባለስልጣኑ በጥብቅ ያሳስባል፡፡
በኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
የካቲት 9/2014 ዓ.ም