ክቡር ለማ መገርሳ ዳውድ ኢብሳን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ጀግናችንን ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስን ከአስመራ ይዞ ይገባል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። እነሆ ይህ የሀገር ፈርጥ፤ ይህ ብርቅዬ ጀግናችን እስካሁን በሕይወት ይኑር አይኑር በይፋ የታወቀ ወይም የተነገረ ነገር እስከዛሬ አልነበረም፡፡

ክብር ለኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ የጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ማስታወሻ ሀውልት ዛሬ ይመረቃል

ኤርትራ የበላችው ኮነሬል በዛብህ ጴጥሮስ በትውልድ ቦታው ሀድያ ላይ ሀውልት ተሰርቶለታል::

በሆሳዕና ከተማ የተገነባው የጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ማስታወሻ ሐውልት ዛሬ ጥር 22/2014 በደማቅ ስነ-ስርዓት ይመረቃል::

የሆሳዕና ከተማ እና አካባቢው ህዝብ ይህንን ታላቅ ሁነት ለማስተናገድ ዝግጅቱን አጠናቋል።

21st Century Library & Information Technology Network

Lema me.jpg

ልብወለድ የሚመስለው የጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ገድል (ኤርሚያስ ቶኩማ) February 12 2016

ለሀገራችን ኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ለማስከበር በግንባር ቀደምትነት ተሰልፈው ታላቅ ገድል ከፈፀሙ በርካታ ጀግኖች መሀል አንዱ ነው፡፡ በፈፀመው ወደር የሌለው ጀግንነት ሊታወስ የሚገባ የሀገር ኩራት። ነገር ግን ጀግንነቱ በወጉ ያልተነገረለት፡፡ ጀግናው ለኢትዮጵያ አየር ኃይል ዘላለማዊ ኩራት ከሆኑ ድንቅና ብርቅዬ ተዋጊዎች መሃል በጀግንነቱ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው፡ ፡ በ1944 ዓም የተወለደው ይህ ብርቅዬ ጀግና ታላቅ ገድል ከፈፀመባቸው የውጊያ ውሎዎቹ መሃል የሐምሌ 27 ቀን 1969 ዓ.ምህረቱ ይቀድማል፡፡ በዚያ ወቅት ትምክህተኛው የዚያድ ባሬ መንግስት በምስራቅ ኢትዮጵያ ግዙፍ ወታደራዊ ወረራ ይፈፅሞ ነበር፡፡ ይህንን ወረራ ለመመከት ከተሰማሩት የአየር ኃይል (አሜሪካ ሰራሽ ኤፍ 5 ኢ) ተዋጊ ጀቶች መሃል አንዱን የያዘው ይህ ጀግና ነበር። እናም በኦጋዴን ሐረዋ፣ አይሻ፣ በእነኖሜጢ እና በሌሎችም ቦታዎች የሮኬት ናዳ በማውረድ ወራሪውን የሶማሊያ ጦር ባለበት እንዲገታ ከማድረግ ባሻገር፣ 8 የጠላት ታንኮችን ከእነምድብተኛው ረመረመ፡፡ ይህንን ታላቅ ጀግንነት ባስመዘገበ በ10 ሰዓት ልዩነት እንደገና ወደምስራቅ ጦር ግንባር በመብረር የኢትዮጵያን አየር ኃይል ብቃት ያስመሰከረም ነው፡- ይህ ጀግና።

View original post 699 more words

Author: 21st Century Library & Information Technology Network [Information & Knowledge Dissemination Platform By Mulugeta Woldetsadik, Librarian/Information Professional at Hawassa University, Ethiopia]

Mulugeta Woldetsadik, Librarian/Information Professional @ Hawassa University, , Sidama Region, Ethiopia

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: