2021 Honour Roll_ Canadian Librarianship


Congratulations to the members of the Canadian librarianship community who were recognized in 2021 for their contributions to the profession and to Canadian society!

Advertisement

የታሪክ ባለቤቶች እና የትርክት ጠባቂዎች!?!


…..በኢትዮጵያ ታሪክ ይዘት እና አተራረክ ላይ ጥያቄ የሚያነሱ አካላት ባሉት መረጃዎች ላይ በመንተራስ የራሳቸውን የታሪክ አረዳድ ወደገበያው ለማስገባት ሲሰሩ ይስተዋላል፡፡ በተለይም ባለፉት ሶስት አስርት አመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ መሰረታዊ የሚባል የታሪክ ግንዛቤ ልዩነት ተፈጥሯል፡፡ ይህ ጊዜ አጭር የማይባል በመሆኑ አንድ ትውልድ በአዲስ የተለየ የታሪክ አረዳድ ውስጥ እየተቀረፀ ነው ለማለት ያስደፍራል፡፡ ምናልባት ለዚህ ቀዳሚውን ሚና የተጫወተው ደግሞ የኦሮሞ ብሄርተኛ እንቅስቃሴን በምሁራዊ ስራዎች ለመደገፍ የተደረገው መጠነ ሰፊ የጥናት እና የምርምር ጥረት ነው፡፡ ይህ ምሁራዊ የታሪክ ክለሳ እና መልሶ የመፃፍ ዘመቻ በዋነኝነት በኦሮሞ ታሪክ ጥናት ላይ ቢያተኩርም በአጠቃላይ «የኢትዮጵያ ታሪክ» በመባል የሚታወቀውን ነባር አረዳድ የተፈታተነ እና ደካማ ጎኖቹንም ለትችት አጋልጦ የሰጠ መሆኑ ግን አልቀረም። ካሁን ቀደምም ቢሆን በተቋም ደረጃ ባይሆንም እንደ ፕሮፌሰር ላጲሶ እና ሁሴን አህመድ ያሉ አንጋፋ ምሁራንም የአዲሱ ትውልድ የታሪክ አረዳድ መሀንዲሶች ነበሩ፡፡ .

በ60ዎቹ ፖለቲካ ተፅእኖ ስር የተፃፉ የተለያዩ የብሄር እና ብሄረሰብ ታሪኮች፣ እንዲሁም የትርጉም ብርሀን ያገኙ የውጭ አገር ስራዎችም በዚህ ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡ እስካሁን በተሰሩ የታሪክ ስራዎች ውስጥ የሚገኙ መረጃዎችን በማቀናጀት እና በማዳቀል ሚዛናዊ በሆኑ ፀሀፍት የተዘጋጁ ታሪክ ነክ ስራዎችም በቁጥር እየበረከቱ ሲሆን ብዙሀኑን በመድረስና ተፅእኖ በማሳደርም ትልቅ ሚና እየተጫወቱ ይገኛል፡፡

.አዲሱ የታሪክ አረዳድ እና የቀረቡበት ክሶች

ያልተነገሩ ታሪኮችን የመፃፉ እና የተፃፉትን መልሶ የመተንተኑ ጥረት ሁለት ትላልቅ ክሶች ቀርቦበታል ፡፡.

1/ «የታሪክ ክህደት» እና «የአገርን መሰረት ማናጋት» ክስ:-

የመጀመሪያው ከሀገር ክህደት ክስ የማይተናነስ የሆነው «ታሪከን የመካድ» እና «አገር የቆመችበትን መሰረት የማናጋት» የተሰኘው ክስ ነው፡፡ የዚህ ክስ አቅራቢዎች በቁጥር አናሳ ቢሆኑም የደቀ መዛሙርቶቻቸው ድምፅ ግን ከፍ ብሎ ይሰማል፡፡ እነዚህን ቡድኖች ጠለቅ ብለን ካየናቸው የነባሩ ትርክት ጠባቂዎች አድርገው ራሳቸውን የሾሙ ናቸው። ውገናቸውንም ከታሪክ እና ከእውነታ ጋር በኃይለኛው የሚጣረስ ሆኖ እናገኘዋለን።

.«ታሪክ» እና «ትርክት» በጣም የተለያዩ ናቸው፡፡ ታሪክ የተፃፈውንም ያልተፃፈውንም፣ ወደፊት የሚፃፈውንም፣ ምናልባትም ጭራሽ የህትመት ብርሀን የማየት እና የመነገር እድል የማይገጥመውንም ሁሉ የሚያጠቃልል ያለፈ ክስተት ጥቅል ስያሜ ነው፡፡ በዚህ አተረጓጎም ታሪካቸው ያልተነገረና ያልተፃፉላቸው ህዝቦች በራሳቸው «ታሪክ የሌላቸው ህዝቦች» አይደሉም። ታሪካቸው የሚቀርበውም በነበረው ይዘት እንጂ በአንድ ወቅት ለተፈጠረው ትርክት በሚኖረው ተስማሚነት ላይ በመንተራስ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ትርክት በአፈታሪክ እና በሰነድ በተገኙ መረጃዎች፣ ምናልባትም በፈጠራም ላይ በመንተራስ ስላለፈው ዘመን በአንድ ወቅት ተደራጅቶ የቀረበ የትናንት መግለጫ ነውና፡፡ በዚህ አተረጓጎም መሰረት ትርክት መፍጠር የቻለ ክፍል ሁሉ የታሪክ ባለቤት አይደለም፡፡ Eric Foner ‘Who Owns History? Rethinking the Past in a Changing World’ በሚለው መፅሀፉ የታሪክ ባለቤቶች በአንድ በኩል ሁሉም ሰዎች ሲሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ ማንም ነው ይለናል፡፡

.ታሪክም ሁሉን በአንድ ቋት ለመክተት እስካላጠበብነው ድረስ በየዘመኑ ባሉ ለውጦች በመንተራስ በድጋሜ የሚተነተን የሁሉም ግን ደግሞ የማንም ሀብት ነው፡፡ የትርክት ባለቤቶች ግን ከዚህ እውነታ በተቃራኒ ታሪክ የኛ እና የኛ ብቻ ነው በሚል ከመርህም ከተጨባጨ ሁኔታም ተቃርነው ይገኛሉ፡፡ ከዚህ ጥቅል ማዕቀፍ አንጻር አዲስ ታሪክ በተነገረ እና የተለየ ትንተና በቀረበ፣ እንዲሁም ትርክታቸው በተናጋ ቁጥር ከላይ የጠቀስናቸው ቡድኖች «የአገር መሰረትን የማናጋት» ክስ ሲያቀርቡ ይታያሉ፡፡ ከዚያም አልፈው ትርክታቸው ዛሬ ላይ ባሉ ለውጦች ሊበረዝ እና ሊከለስ የመቻሉን እድል ለመግታት «Where is the Now?» ለሚለው መሰረታዊ ጥያቄ «ዛሬ ትናንት ነው» ዓይነት ቅኝት ያለው ተግባራዊ ምላሽ በመስጠት ትናንት የተፈጠረውን ትርክት ከማስቀጠል ውጭ የዛሬው ትውልድ ሌላ አማራጭ እንደሌለው ለማሳመን ደጋግመው ይሰብካሉ፡፡ የታሪክ ባለቤቶች ከትርክት ባለቤቶች (ጠባቂዎች) በተቃራኒ የታሪክ ባለቤቶች ይገኛሉ፡፡

የታሪክ ባለቤቶች በረዥሙ የአገራችን ታሪክ ውስጥ ቀናውን እየተቀበሉ፣ የጎበጠውን በመረጃ እያቀኑ ባለቤትነታቸውን በተግባር የሚያሳዩት ናቸው፡፡ ከአንድ ንጉስ የ30 እና 40 ዓመት የንግስና ታሪክ ውስጥ የአንድ ወቅት ስህተቱን ማውገዛቸው፣ አልያም ከአንድ አገር ዘርፈ ብዙ የአስተዳደር ፖሊሲዎች ገሚሱን በአግላይነት መተቸታቸው ከያገባኛል ስሜታቸው የፈለቀ እና በአገራቸው እና ታሪካቸው ላይ የሚያሳዩት የባለቤትነት ስሜት ነጸብራቅ እንጂ ሌላ ሆኖ አናገኘውም፡፡.

እነዚህ ወገኖች የታሪክ ባለቤቶች እንጂ የትርክት ጠባቂዎች አይደሉም፡፡ የታሪክ ባለቤቶች የባለቤትነት ስሜታቸው ጥያቄ የማንሳት እና የማስተናገድ ስልጣን ይሰጣቸዋል፡፡ ትርክት ጠባቂዎች ባለመሆናቸው ላልተነገሩ ታሪኮች የማይሸበሩ፣ ስለአገራቸው ሙሉ ኃላፊነት የመውሰድ የሞራል ልዕልና ያላቸው ናቸው፡፡ የዚህች አገር መፃዒ እድልም በእኒህኞቹ ትከሻ ላይ የወደቀ ሳይሆን አይቀርም። የሁሉንም ህዝቦቿን ታሪክ የአገሪቱ መሰረታዊ የታሪክ ክፍል አድርጎ ለማስተናገድ መወሰን የሚችሉ የታሪክ ባለቤቶች በእርግጥም ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው።.

2/ «በትናንት የመባዘን» እና «የበታችነት ስሜት» ክስ:-

ሁለተኛው የክስ ዓይነት በመሰረታዊነት ከታሪክ ባለቤቶች ለታሪክ ባለቤቶች የሚቀርብ ውስጣዊ የአካሄድ ጥያቄ ሊባል የሚችል ነው፡፡ የክሱ አንደኛው መገለጫ «ታሪክ ያለፈ ነገር እንደመሆኑ በነጋችን ላይ ማተኮር ይበጀናል፤ ግዜ እና ጉልበታችንን በትናንት ላይ አናባክን» የሚል ነው፡፡ በጥቅሉ ቀና እና ተራማጅ ሀሳብ ይመስላል፡፡ ይህ ሐሳብ ልክ የሚሆነው ግን በተፈጠረው ትርክት ላይ በመንተራስ የዛሬውን የህብረተሰቦች ግንኙነት እና የኃይል አሰላለፍ ልወስን የሚል አካል እስከሌለ ድረስ ብቻ ነው፡፡ በተጨማሪም አሁን የምንገኝበት ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ደረጃ ከታሪክ ተፅእኖ የተላቀቀ፣ አነስ ካለም የሚካሄዱ ማሻሻያዎች በታሪክ የማይጎተቱበት፣ ነገን ብቻ ታሳቢ ያደረገ መስተጋብር መስፈኑን ሳያረጋግጡ እዚህ መደምደሚያ ላይ መድረስ ከባድ ነው፡፡ ከዚያም ባለፈ ደግሞ እነዚህ አካላት ተመሳሳዩን ጥያቄ ለትርክት ጠባቂዎችም የማቅረብ ወኔ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ «የፈጠራችሁት ትርክት ቆሞ ቀር ነውና ዛሬ ላይ ተመስርታችሁ ስለነገ አሳቢ፣ ተራማጅ ሁኑ» ብለው የመገሰፅ አቅሙ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ትርክት ጠባቂዎች የአገርን ታሪክ እና ማንነት የብርጭቆ ውሀ ይመስል አንዴ ከሞላ ተጨማሪ የማይቀበል ያለቀለት እውነታ አድርገው ማሰባቸውን እንዲያቆሙ የማድረግ ቁርጠኝነቱ ሊኖራቸውም ግድ ነው፡፡ ይህ ወኔ የማይኖራቸው ከሆነ እነሱንም «የትርክቱ ሰለባዎች» ከመባል አያድናቸውም፡፡.

የዚህ ክስ ሁለተኛው መገለጫ «የታሪክ ጨለማ ጥጋጥጎችን እየመረጡ ማቅረብ ከበታችነት ስሜት የተወለደ እና የህብረተሰብን አብሮነት የሚያናጋ ደካማ አካሄድ ነው» የሚለው ውንጀላ ነው፡፡ የዚህ ወቀሳ ሠንዛሪዎች እንደመፍትሄ «በጎ በጎውን እየመረጥን እናውራ» የሚል ፎርሙላ ሲሠጡ ይስተዋላል፡፡ ይህ ግን እነሱ በግላቸው «የተሻለ ነው» ብለው የተቀበሉት የታሪክ ዘገባ ቅኝት እንጂ ሳይንሳዊም ምክንያታዊም አካሄድ ሆኖ አናገኘውም፡፡ እንደውም ይህ አካሄድ በታሪክ ጥናት ውስጥ ትልቅ ቦታ የተሰጣቸውን «construction, deconstruction and reconstruction»ን የመሳሰሉ መሰረታዊ የታሪክ ቅኝት ስልቶችን የሚቃረን ነው፡፡

በማህበራዊ ሳይንስ ጥናት ‘false consensus effect’ የሚባል ፅንሰ ሀሳብ አለ፡፡ በተለያዩ የትምህርት መስኮች የተለያዩ አረዳዶች ቢኖሩትም በዋነኛነት ይህ ፅንሰ ሐሳብ ሰዎች ከሚቀርቡላቸው አማራጮች ፊት ለፊት ያለውን እና የቀለላቸውን በመምረጥ «ቀላል» ምርጫቸው ለብዙሀኑ ተገቢ የሆነ ብቸኛ ትክክለኛ ምርጫ እንደሆነ የሚደመድሙበትን ስሁት አካሄድ የሚገልፅ ነው፡፡ ለዚህ ተፅእኖ ከሚያበቁ ምክንያቶች ውስጥ በቂ መረጃ አለመኖር፣ ሁልጊዜ ቀላል ነገሮችን መመኘት፣ የራስን እይታ ከተገቢው በላይ አልቆ መመልከት፣ በአማራጮች መካከል ያሉ ጥቅምና ጉዳቶችን በጥልቀት ለመመዘን መስነፍ፤ የተለየ ሀሳብን በመምረጥ ሊመጣ የሚችልን ጣጣ መሸሽ ተጠቃሽ ናቸው። ከሞላ ጎደል ሌሎች ሥነ ልቦናዊ መንስዔዎችም አሉት፡፡ የዚህ ችግር ሰለባ መሆን በአንድ በኩል ሁልጊዜ ቀላል የሆኑና ብዙ ተቀናቃኝ የማያስነሱ አመለካከቶችን ብቻ ወደማራመድ ይገፋል። የሚያስከትለው ትልቁ አደጋ ግን በሂደት የዚህ ችግር ሰለባዎች የራሳቸውን አረዳድ ብቸኛ የንቃተ ኅሊና መለኪያ አድርገው ወደማየት መገፋታቸው ነው። በግሌ የተሻለው አማራጭ እነዚህ ወገኖች እነሱ ባመኑበት የታሪክ አረዳድ ስራቸውን ወደገበያ ማቅረብ ይመስለኛል። ከዚያ ውጭ ግን«እኛ እንድናወራ ሌሎች ዝም ይበሉ» ዓይነት የ«ቆማችሁ አሳልፉኝ» ስልት መከተላቸው በጭራሽ የሚያዋጣ አይሆንም፡፡.

በሞሀመድ እድሪስ

Koha Con2021: An International Conference that left a SAGA behind {Held in Pakistan 13-18 December 2021}


Koha is one of the most commendable open-source software based on Integrated Library Systems (ILS). This software serves the entire community with robust technology: schools, colleges, universities, public libraries, etc. The name KOHA is derived from the Maori language means a gift or donation. Chris Cormack from New Zealand initiated the software in 1999-2000. Koha is a fully-featured, scalable library management system. Koha has been developed for libraries of various sizes, volunteers, and support companies worldwide. The software is converted into 26 different languages of several continents. The latest release took place on November 25, 2021, with a new version, 21.1.

The kingdom of Damot: An Inquiry into Political and Economic Power in the Horn of Africa (13th c.) 


The kingdom of Damot: An Inquiry into Political and Economic Power in the Horn of Africa (13th c.) {Article} […}

“የኢትዮጵያ ታሪክ” ከንግሥተ ሳባ እስከ ታላቁ የአድዋ ድል ߹ ተጻፈ በብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደስላሴ_”Ethiopian History”  A must-read book packed with information


ብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደስላሴ በአጼ ምኒሊክ እና በሀይለስላሴ ዘመን ቁንጮ ባለስልጣን ከነበሩ መካከል አንዱ ናቸው። ይህን የብላቴን ጌታ ህሩይ መጽሀፍ ሁሉም ሊያነበው የሚገባ መጽሀፍ ነው፡፡

ገጽ 87 እንዲህ ይላል “….ይህም ዛሬ አዲስ አበባ ተብሎ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የሆነው አገር በዚያ ዘመን ” ፊንፊኔ ” ይባል ነበር፡፡ በቦታው ላይ የነበሩት የገላን እና የአቢቹ ጎሳ ኦሮሞዎች ችግር እንዳይፈጥሩባቸው በማሰብ ንጉስ ሳህለስላሴ አቢቹን ያቀፉ እና የወደዱ በመምሰልና ውስጥ ውስጡን ለርሱ የሚረዱ በማስመሰል እርስ በርስ ያዋጓቸው ጀመር፡፡ሁለቱም ጎሳዎች ሰባት አመት ሙሉ ሲዋጉ ነበር ንጉሱም አብቹን በመርዳትና በማገዝ ገላን ተሸነፈ፡፡ከዚያም በአብቹ ጉልበት ገላንን፣ አዳን፣ ወበሪን ፣ጅሩን፣ዋዩን፣ሰላሌን አድክመው ገባር አደረጉት፡፡.ኦሮሞዎች እርስ በርስ መዋጋት የምኒሊክን ጉልበት አበርትቶ የራሳቸውን ጉልበት አደከመው..”

ገጽ 87

ከታች ባለው ሊንክ መጽሀፉን ማውረድ ትችላላቹ።

Africa_What a Year 2021


Four Ethiopian women listed among 100 most influential Africans in 2021

“Gidey’s seemingly effortless stride will carry her to many more records, making her one of the world’s biggest athletics stars, and the next great Ethiopian sporting ambassador at a time when the country badly needs symbols of unity.”

“After cutting her teeth in the US administrations of George W. Bush and Barack Obama, Mimi Alemayehou, an Ethiopia-born, Kenya-raised American development finance expert, is now making waves in the global private sector.”

“Born at Adama in Ethiopia in 1993, arriving in the Netherlands as a refugee when she was 15 years old, and taking Dutch citizenship in 2013, Sifan has defied her circumstances, her lean appearance, and somewhat pained expression to wear down the most formidable opposition.”

“Mid this year, [Timnit] said she was raising money to launch an independent research institute based on her work at Google’s Ethical Team and taking in what she had achieved as the founder of Black in AI, a community of black AI researchers.”

Source:http://100.newafricanmagazine.com/

Notable African deaths of 2021: From ‘Ethiopia’s Elvis’ to mega pastors

Source: https://www.bbc.com/news/world-africa-59702842

What is politics? by Professor Christina Boswell FBA


“Political contestation is as much about cultural identity and recognition, as it is about allocating material resources.”Professor Christina Boswell FBA discusses how we can begin to define politics in one of our top 10 blogs:

We often refer to something as being ‘political’, or ‘all about politics’, to mean it boils down to a power struggle between people or groups. The idea is that politics is a process of maneuvering to assert rival interests.[…]

Books Do Furnish a Civilization: Libraries and their glories


The True University of these days is a collection of books.

—Thomas Carlyle

Digital Nation Australia 2021


Good Things Foundation Australia’s Digital Nation Australia 2021 report brings together the latest research and insights from government, community, and academia to help build an understanding of the digital inclusion landscape in Australia and inform initiatives that could close the digital divide for all.

The digital divide is a significant issue in modern Australia, particularly with the rapid pace of digitization brought forward by the COVID-19 pandemic. Digital technology has become an essential requirement for work, study, accessing essential services, and connecting with family and friends.

The positive news is that the digital divide is slowly improving in Australia and that initial research points to more people being active online than they were before the COVID-19 pandemic.[…]

Smartphones are making us stupid – and maybe a ‘gateway drug’


Family matters: Adults as much as children can fall victim to smartphones and their negative effects, including poor social interaction.

Neuroscience research shows that smartphones are making us stupider, less social, more forgetful, more prone to addiction, sleepless and depressed, and poor at navigation – so why are we giving them to kids?

Recent mobile phone bans in Victorian state schools have had some parents and kids up in arms, despite a study showing that 80 percent of Australians support the ban. Many private schools are now implementing phone and device bans in schools – but they too face fierce opposition. […]

%d bloggers like this: