ይህ አንደበቱ የተሸበበ ሽጉጥ – የኃይል ድርጊትን ለማውገዝ በኒውዮርክ ከተማ፤ ማንሃተን፤ ተርትልቤይ፤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት ትይዩ የቆመ፡፡

ይህ ኃውልት በዓለም ላይ እጅግ አስደናቂ ተብለው ከተመዘገቡት የሠው ልጅ አዕምሮ የወለዳቸው የኃውልት ጥበበ ቅርፆች ከቀዳሚዎቹ ይመደባል፡፡ ‹‹የሰው ልጆች አንደበት እንዳይሸበብ ፤ የሽጉጦ ች አንደበት ይሸበብ!!›› ነው የኃውልቱ ቀጥተኛ የነፃነት መ ል ዕ ክ ት ! !
“የሰው ልጆች እንደ ‹ሰው-ልጅ› እ ን ዲ ያ ስ ቡ ፤
የሽጉጦች አፈሙዞች ይሸበቡ፤ ከነጥይት መዝሙራቸው ያ ሸ ል ቡ ፤
ይክሸፉ፣ ይታሰሩ፣ ይደፈኑ፣ ይ ን ገ ር ገ ቡ ፤
ሰብዓዊነት፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ ክብር፣ ህይወት እንዲያብቡ!!”

በሀሳብ ውጊያ ውስጥ መጻህፍት ዋነኛ መሣሪያ ናቸው!
በነገራችን ላይ ብዙዎቻችን በስድብና በተራ መዘላለፍ ነው የምንዋጋው፡፡ ውሃ የሚያነሳ ሀሳብ ለ መ ሰ ን ዘ ር እ ን ች ገ ራ ለ ን ፡ ፡ ሀሳብ እንደ ቁምጣ ያጥረናል፡፡ ሀሳብ ሲያጥረን ደግሞ ወደ መሳደባችን እንገባለን፡፡ መቼ ነው ሰ ዎ ች ን በ ሀ ሳ ብ አ ሸ ን ፈ ን ‹‹በቃ ተሳስቻለሁ›› እንዲሉ የምናደርገው?
እ ን ደ ሀ ገ ር ይ ህ ን ማድረግ የሚያምን ማህበረሰብ መቅረጽ ስንጀምር ነው ማደግ የ ም ን ች ለ ው ፡ ፡ አናነብም፣ትልቁ ችግራችን ከእውቀት ነጻ መ ሆ ና ች ን ነ ው ፡ ፡ መማር ማለት ዲግሪ መያዝ አይመስለኝም፡፡ ትልቅ ዲግሪ ይዘን ሀሳባችን ግን ድግር የሆነብን ብዙ አለን፡፡

ዋናው የአስተሳሰባችን ምርጥነት ነው፡፡የዶለዶመ ጭንቅላት የሚሳለው በመጻህፍት ብቻ ነው፡፡ እስኪ ቤታችንን እ ን መ ል ከ ት ፡ ፡ ስ ን ቶ ች ነን ሸልፍ ያለን?
እስኪ እውነት እንናገር፡፡ ስ ን ቶ ች ነ ን ለ ል ጆ ች በልደታቸው ቀን መጽሐፍ ገዝተን የምንሸልመው?
በወር ስንት መጽሐፍ እንገዛለን ወይም እናነባለን?
አማን ያሰንብተን
Source: Link -Up, Library Newsletter, Volume 2, Issue 7, October 2017
You must be logged in to post a comment.