ልብ ጠጋኝ ዶ/ር ፈቀደ አግዋር የጻፈው እና “የልብ ጠጋኙ ማስታወሻ” የተሰኘው መጽሐፍ ነሐሴ 29 ቀን 2013 ዓ.ም. ተመርቋል

በግላቸው 326 ገደማ የልብ ቀዶ ጥገናዎችን ያደረጉት ኢትዮጵያዊ ሐኪም
ዶ/ር ፈቀደ አግዋር

በ4 ዓመታት ውስጥ ነው 326ቱን የልብ ቀዶ ጥገናዎች ያደረጓቸው

ዶ/ር ፈቀደ አግዋር “የልብ ጠጋኙ ማስታወሻ” መጽሐፍ ምረቃ

በ17 ታሪኮች የተዋቀረው መጽሐፉ፤ ከታካሚዎቹ አንደበት የተሰባሰቡ ታሪኮች ተካተውበታል

ኢትዮጵያዊው ልብ ጠጋኝ ዶ/ር ፈቀደ አግዋር የጻፈው እና “የልብ ጠጋኙ ማስታወሻ” የተሰኘው መጽሐፍ ዛሬ ነሐሴ 29 ቀን 2013 ዓ/ም ተመረቀ።

መጽሐፉ ዶ/ር ፈቀደ ልብ እና ሳንባ ቆመው ባደረጋቸው የቀዶ ጥገና ህክምናዎች ዙሪያ የሚያጠነጥን ሲሆን ገጠመኞቹ ተካተውበታል።

በ17 ታሪኮች የተዋቀረም ነው። ከታካሚዎቹ አንደበት የተሰባሰቡ ታሪኮችም ተካተውበታል።

• በኢትዮጵያ ልብ እና ሳንባ ቆመው የሚሰጠው ቀዶ ህክምና              

ስራውን ሌሎች ሊማሩበት፣ ሊነሳሱበት እና ዋቢ አድርገው በግብዓትነት ሊጠቀሙት እንደሚችሉ በማሰብ መጽሐፉን ጻፍኩት ብለዋል ዶ/ር ፈቀደ በምረቃ ስነ ስርዓቱ።

መጽሐፉ የኢትዮጵያ የልብ ቀዶ ጥገና ህክምና ታሪክ የተሰነደበት እንደሆነም ነው የገለጹት። “ከአሁን በኋላ የእኔ ሳይሆን የኢትዮጵያ ታሪክም ነው” ብለዋል።

ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ትርፍ ህክምናውን በነጻ ለመስጠት በእሳቸውና በአጋሮቻቸው የተቋቋመውን ‘ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ’ን ለመደጎም እንደሚውልም ነው የተናገሩት።

ዶ/ር ፈቀደ ከአሁን ቀደም ከአል ዐይን አማርኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ በግልና በቡድን 326 ቀዶ ጥገናዎችን ማድረጋቸውን መግለጻቸው የሚታወስ ነው።

231 ገጾች ያሉት “የልብ ጠጋኙ ማስታወሻ” ዛሬ የዘርፉ ሙያተኞች፣ የህክምናው ተጠቃሚዎች እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በአዲስ አበባ ተመርቋል።

Advertisement

Author: Mulugeta Woldetsadik, Librarian/Information Professional at Hawassa University, Ethiopia [21st Century LIS Network: Information_Knowledge Retrieval & Dissemination Platform]

Mulugeta Woldetsadik, Librarian/Information Professional @ Hawassa University, , Sidama Region, Ethiopia

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: