
የታሪክ ንቅለ–ምልከታ~~~~~~~~~
እነሆ ቀኑም ደርሷል፣
ሁሉም በአላህ ፍላጎት ሆኗል።ከሁለት ቀን በሇላ መከፋፈል ይጀምራል! *ታሪክ ለሰው ልጅ አስፈላጊ መሳሪያ ነው። የትላንቱን ተረድቶ ዛሬውን አገናዝቦ ነገውን የሚተልምበት ነው። 16ኛው ክፍለ ዘመን በዓለም ታሪክም ቢሆን ከፍተኛ ለውጥ የታየበት ዘመን ነው። የአሰሳ (Exploration) ዘመን በመሆኑ አሜሪካኖች በአውሮፓ አሳሾች ስር የገቡበት ነው። በቀይ ባህርና በህንድ ውቅያኖስ የፖርቹጋሎችና የኦቶማኖች መንግስታት የሚሻኮቱበት ዘመን ነው። ኢትዮጵያም የጂኦፖለቲካዊ ተቋዳሽ በመሆኗ የስልጣን ሽግግር የታየበተ ዘመን ነው። የመካከለኛውን ዘመን ታሪክ የሚያጠና ተመራማሪ እየቀነሰ በመጣበት ወቅት ወጣት ተመራማሪዎች የ16ኛው ክፍለ ዘመን እንደገና በአዲስ መልክ እንድናየው እያስገደዱን ነው። ይህም መጽሐፍ አስፈላጊውን መረጃና ማስረጃ በማቅረብ የተዛነፈውን ትርክት ለማስተካከል በሚደረገው እንቅስቃሴ የድርሻውን ያበረክታል። ወደ ተሻለ የታሪክ ግንዛቤ ለሚደረገው ጉዞ የፈር ቀዳጅነትን ስፍራ ይዟል። ለታሪክ አረዳድም ደራሲው የግሉን ምልከታ አጋርቶናል፤ አኪያሄዳችንም የጎራ መለየት ሳይሆን የተሻለ ትንታኔና ግንዛቤ እንድናበለፅግ አቅጣጫውን ያስረዳል። መልካም ንባብ ይሁንላችሁ!!
ረ/ፕ አህመድ ዘከሪያ (የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህርና የታሪክ ተመራማሪ)
You must be logged in to post a comment.