የመጽሐፍ ምረቃ ጥቆማ ‘’ያልታሰበው የሕይወቴ ፈታኝ ጉዞ እና የኢትዮጵያ አብዮት ተሳትፎዬ’’ በሌ/ኮ ብርሃኑ ባይህ አሳታሚ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ


  • የመጽሐፍ ምረቃው ቀን፡- ሐምሌ 15 ቀን 2013 ዓ.ም
  • ሰዓት፡- ከቀኑ 8፡00
  • ቦታ፡ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ጽሕፈት ቤት ቅጥር ግቢ

ይህ መጽሐፍ በደርግ ዘመነ መንግሥት እስከ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ድረስ በተለያዩ ከፍተኛ ኃላፊነቶች ያገለገሉት የሌ/ኮ ብርሃኑ ባይህ እንግዳ ግለ-ታሪክ ነው፡፡ ሌ/ኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ የደርግ አባል በነበሩበት ዘመን የተለያዩ የመንግሥት ሐላፊነት፤ ሥልጣን የነበራቸው ሲሆን የደርግ መንግሥት በፈረሰበት ወቅት ጣልያን ኤምባሲ ውስጥ ከተጠለሉት ጥቂት የደርግ ባለሥልጣናት አንዱ ናቸው። ስለሆነም ደርግ ከሥልጣን ከወረደበት ከግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ጀምሮ ለሠላሳ ዓመታት ያህል ጣልያን ኤምባሲ ውስጥ በጥገኝነት ይገኙ ነበር፡፡መጽሐፉ ከዚህ በፊት ያልተነገሩ እና ከተነገሩትም መሐል በአዲስ አተያይ እና በስፋት የቀረቡ የታሪክ መረጃዎችን የያዘ ሲሆን የኢትዮጵያ አካዳሚ ፕሬስ ከሌሎች የህትመት ውጤቶቸ በተለየ በርካታ ታላላቅ ምሑራንን በአሰናጅነት አስተባብሮ ለሕትመት ያበቃውና ሰፊ የታሪክ ክፍተትን እንደሚሞላ እንዲሁም አሻሚዎቹንም እንደሚያጠራ የታመነበት ነው፡፡

@ Ethiopian Academy of Sciences

Advertisement

ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተሠጠ መግለጫ ። ሐምሌ 12/2013 ዓ.ም


%d bloggers like this: