ሌላው የኢትዮጵያ ታሪክ ገፅታ (ከ896 እስከ 1887) በሙሐመድአወል ሀጎስ


📚 የመፅሐፉ ሙሉ ርእስ፤ ሌላው የኢትዮጵያ ታሪክ ገፅታ (ከ896 እስከ 1887)

📚ፀሐፊ:- ተሾመ ብርሃነ ከማል

📚የታተመበት ጊዜ:-2013

📚 የገፅ ብዛት:-216 (ምስጋና፣ማውጫ፣መግቢያ እና ዎቢዎችን ጨምሮ)

📚 ዋጋው:-150 የኢትዮጵያ ብር

📚 አሳታሚ ድርጅት:-አልተገለፀም

እንደ መግቢያ

ጋሽ ቸሾመ ይህንን ድንቅ መፅሐፍ ኢዲት የማድረግ ሐላፊነት ሲሰጡኝ የተሰማኝ ደስታ አይሉት ጭንቀት አስታውሰዋለሁ። ነገር ግን በወቅቱ እኔ ባለሁበት ክልል በተፈጠረው ድንገተኛ ጦርነት ስለ መፅሐፉ አስፈላጊነት ሳልፅፍ ቀረሁኝ። ደስታው ይህንን ታሪካዊ ድንቅ መፅሐፍ የማረም እድል ከማግኘት የመነጨ ሲሆን ጭንቀቱ ደግሞ እውን እኔ ይህንን ስራ ለማረም በቂ እውቀት እና ልምድ አለኝ ወይ ከሚል የመነጨ ነበር።

ጋሽ ተሾመ መፅሐፋ መጀመሪያ ላይ”ሌላኛው የኢትዮጵያ ታሪክ ገፅታ” እና “የሐረር አሚሮች ሱልጣኖችና ኢማሞች የሕይወት ታሪክ” በሚሉ ሁለት ዓበይቴ ክፍሎች ከፋፍለው በአንድ መፅሐፍ ለማሳተም ነበር ፍላጎታቸው። ነገር ግን በኋላ ላይ ባደርግነው ተከታታይ የስልክ ውይይቶች መፅሐፉ ሁለት መፃሕፍት የሚወጣው እንደሆነ መግባባት ላይ በመድረሳችን በሁለት መፃሕፍት ለመታተም በቅቷል። (ስለ ሁለተኛው መፅሐፍ በሌላ ርእስ የምመለስበት ይሆናል።)

ከዚህ በፊት ለንባብ የበቁ የደራሲው ስራዎችጋሽ ተሾመ አንጋፋ ፀሐፊ ሲሆኑ ካሁን ቀደም 14 የሕፃናት መፃህፍት፣ 10 በኢትዮጵያ ሙስሊሞች እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ መፃሕፍት፣5 ለመድረክ የበቁ ተውኔቶች እንዲሁም 5 ለሕትመት የበቁ ጥናቶችና ምርምሮች አበርክተውልናል። እኝህ አንጋፋ ፀሐፊ ካሳተሟቸው መፃሕፍት የተወሰኑትን በስም ለመጥቀስ ያክል:

-1) ኢማም አሕመድ ኢብራሂም

2) የሰላም ፍኖት ለኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝቦች አንድነት

3) ኮናባ የተደበቀች የዓለም ቅርስ

4) ዓይን አብራዎቹ

5) ንግስት ፎራ

6) የዓለማችን ታላላቅ ሰዎችና ጥቅሶቻቸው

7) የዓፋር ታሪክ (ከሌሎች ጋር በመሆን)

የመፅሐፉ አጠቃላይ ጭብጥ

የሌላው የኢትዮጵያ ታሪክ ገፅታ አጠቃላይ ጭብጥ በመፅሃፉ መግቢያ ላይ እንዲህ ሰፍሮ እናገኛዋለን፦”

የእየአንዳንዳችን ታሪክ የሁላችንም ታሪክ ነው። የሁላችንም ታሪክ ደግሞ የአንዳችን ነው፤ ስለዚህም እኔም ያንተን ታሪክ ልቀበል፣ አንተም የኔን ታሪክ ተቀበል” ወደሚል አመለካከት መሸጋገር ይኖርብናል። ይህንን መሠረታዊ ጉዳይ፣ እስካሁን ሲደረግ እንደነበረው ወደ ጎን መተው በመላው ኢትዮጵያ ታሪክ ያለውን የህልውና ባህርይን ያናጋል”

በመሆኑም “የይፋት፣ የመኽዙሚ፣ የወላስማ፣ የአዳል፣ የሐረር ወዘተ ሱልጣኔት ታሪክ የኢትዮጵያ ታሪክ ሌላው ገፅታ ነው” ይላሉ ጋሽ ተሾመ። ፀሐፊው ስለመፅሐፉ መሠረታዊ ዓላማ በመፅሐፉ መግቢያ ላይ እንዲህ ሲሉ አስፍረዋል፦”

የዚህ መፅሐፍ መሠረታዊ ዓላማ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የአንድነት ታሪክ ማውሳት ወደ ቀዳማዊ አንድነታቸው ተመልሰው ጥንታዊ ታሪካቸውን እንዲያድሱ፣ የሕዳሴ እንቅስቃሴያችን በብሔራዊ እርቅ ላይ ሳይሆን በብሔራዊ የሕዝቦች ታሪክ እርቅ ላይ የተመሠረተ መሆኑን እንዲገነዘቡ፣ ወደ ታሪክ እርቅ የሚወስዱት መንገዶች ከብሔራዊ ከሚወስዱት መንገዶች የተሻሉ ሰላማዊና ፍትሐዊ መሆናቸውን አውቀው በጋራ እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ ነው።” (ገፅ 5)

ባጭሩ እንደ ፀሐፊው እምነት የመፅሐፉ መሠረታዊ ዓላማ ህዝቦች ወደ ብሔራዊ የታሪክ እርቅ እንዲመጡ ጥሪ ማድረግ ነው።

ጋሽ ተሾመ “ሌላውን የኢትዮጵያ የታሪክ ገፅታ ለመመልከት ስንችል ሀገሪቱ ያለ ምንም ጥርጥር የኛ የኢትዮጵያውያን ሁሉ ትሆናለች። ሀገር ማለት እኛ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ነን። የኢትዮጵያውያን ማንነት ከዚህ ውጭ ሊመደብ አይችልም።” የሚል ፅኑ እምነት አላቸው። (ገፅ 7)

መፅሐፉ ከጥናት ወሰን (scope of study) አንፃር ስንመለከተው ሦስት መሠረታዊ ጉዳዮችን ይሸፍናል:-

➡መጀመሪያ የዛሬይቱን ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ጅቡቲና ሱማሊ በተወሰነ የጊዜ ገደብም ግብፅንና ሱዳንን የሚያካትተው ጥንታዊ የኢትዮጵያ ታሪክን ይዳስሳል

➡በሁለተኛው ክፍል ደግሞ ኢትዮጵያ የገጠማትን የእርስበርስ ጦርነትና በእርሰበርስ ጦርነት ምክንያት የገጠማትን ውድመት ተዳስሶበታል

➡በሶስተኛው ደግሞ የባሕር ላይ ጠብታ የሚል ፅንሰ ሐሳብ በመጠቀም ሌላው የኢትዮጵያ ታሪክ ገፅታ conceptually ለማቅረብ ሞክረዋል።ትንሽ ስለ የውሃ ጠብታ ጽንሰ ሐሳብ የዚህ መፅሐፍ ፀሐፊ መፅሐፋቸውን የቀረፁበት (frame) ያደረጉበት ምሁራዊ አተያይ (perspective) የውሃ ጠብታ ጽንሰ ሐሳብ ሲሉ ሰይመውታል። ፀሐፊው “የትልቋን ኢትዮጵያን ሁለት ገፅታ ለማየት ትንሿን የውሃ ጠብታና የምታስከትለውን ውጤት መመልከት ጠቀሚነት አለው” ይላሉ። ጋሽ ተሾመ እንዲህ ይላሉ ባህር ላይ የምትወድቅ የውሃ ጠብታ ከትልቁ ባህር ትልቅነት አንፃር ስንመለከታት እጅግ አነስተኛ ናት ነገር ግን ትንሿ ጠብታ እየሰፋች ስትሄድ እንመለከታለን። ጠብታዋ ቀለበቶች እየሰራች ባህሩን ታዳርሳለች (ገፅ 6 እና 121)። በውሃ ጠብታ የሚመሠለው ሌላው የኢትዮጵያ የታሪክ ገፅታም የመጀመሪያው ቀለበት በምስራቅ ኢትዮጵያ ሐረር ከተማ ላይ ይጀምርና ሌሎች ቀለበቶች እየሰራ በሠሜን እስከ ትግራይ፣ ኤርትራና ጎንደር ፣ በምስራቅ ደግሞ እስከ ጅቡቲና በርበራ፣ በደቡብ እስከ ሱማሊ፣ ባሊና አርሲ እየሰፋ ይሄዳል።(ገፅ 6)መፅሐፉ በሶስት ክፍሎች ተዋቅሮ የቀረበ ሲሆን

ክፍል ❶ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክና ትርክት የሚመለከት ሲሆን የመፅሐፉ ጥናታዊ ዳሪ የቀረበበት ነው። በዚህ ምዕራፍ ላይ ደራሲው የተለመደው (በተደጋጋሚ ሲነገር የምንሰማው) ወደ ሰሜን የሚያደላው የኢትዮጵያ ታሪክ እንዳለ አቅርበውታል።

ክፍል ⓶ ሁለት ላይ “የጋራ የሆነው የኢትዮጵያ ታሪክ” ሲሉ የሚገልፁት የኢትዮጵያ ረጅም የባሕር ንግድ ታሪክ ተካቷል።

ክፍል ⓷ ላይ እስካሁን ሳይነገር የቆየው የኢትዮጵያ ሌላ ገፅታ ታሪክ በዝርዝር ቀርቧል። (I can say this is the missed link in Ethiopia history)። ደራሲው በዚህ መፅሐፍ ላይ አምስት የቀለበት ዙሮች አቅረበዋል፤

❶ የመጀመሪያው ቀለበት ጀበርቲ እና ጀበርቲነት ሲሆን ይህ ቀለበት እስልምና በኢትዮጵያ እንዴት እንደትፋፋ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ሂደት ነው።

⓶ ሁለተኛው የቀለበት ዙር ደግሞ የንግድ መስመር ሲሆን ሙስሊሞች እንዴትና ምን ያህል የንግድ መስመሩ ተቆጣጥረውት እንደነበሩና ወደ ሀገሪቱ አራት አቅጣጫ እስልምናን እንደዘረጉበት የሚያመላክት ቀለበት ነው።

⓷ዓዲ ከቢረ ሦስተኛው የጠብታ ቀለበት ዙር ነው።

⓸ ኢስላማዊ ባህል፣ ቅርስና ቱሪዝም አራተኛው የጠብታ ቀለበት ዙር ሲሆን በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ኢስላማዊ ቅርሶች ሙስሊሙን ህብረተሰብ በማስተሳሰር ያላቸው ሚና የሚያሳይ ቀለበት ነው።

⓹ የመጨረሻው የጠብታ ቀለበት ዙር ደግሞ ኢስላማዊ አንድነት የሚያመለክት ነው። ደራሲው ለስራቸውን ማጣቀሻ የሚሆኑት ከ30 በላይ የሚሆኑት ማጠቃሻዎች ተጠቅመዋል። በተለይ እነደነ ቸሩሊ፣ሃበርላንድ እና ሌሎች አንትሮፖሎጂስቶች ያደረጓቸውን የመስክ ጥናቶች በዋቢነት ተጠቅመዋል።እንደ መደምደሚያ ጋሽ ተሾመ በዚህ ሌላው የኢትዮጵያ ታሪክ ገፅታ በተሰኘው መፅሐፋቸው ላይ በተደጋጋሚ ከምንሰማቸው፣ በታሪክ ትምህርት መፃሕፍት ላይ ጎልተው ተጠቅሰው ከምናያቸው የኢትዮጵያ ታሪክ ውጭ ያሉ የተረሱ፣ የተዘነጉ እና የተተዉ የኢትዮጵያ ታሪክ ፅፈውልናል። ግማሹ የኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ሌላ ግማሽ በመጨመር የኢትዮጵያ ታሪክ ሙሉ ምስል እንዲይዝ ሲጥሩ ይስተዋላል። ከለመድናቸው የአክሱም፣ የጎንደር፣ የሰሎሞናዊ ዘመነ መንግስት ውጭ ያለው የኢትዮጵያ ታሪክ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እንዲወከል (represent) እንዲሆን ምሁራዊ ጥሪ ያደርጋሉ። የኢትዮጵያ ህዝቦች ወደ ብሔራዊ የታሪክ እርቅ (በታሪክ ላይ መስማማት) መምጣት አለባቸው ሲሉ በፅኑ ይከራከራሉ። ይህ መፅሐፍ ታሪክን አቅቦ ከማስቀመጥ (documentation) በተጨማሪ የታሪክ ተመራማሪዎች ከተለመደው የኢትዮጵያ ተሪክ ገፅታ ውጭ ያለው ሌላው ታሪካችንን እንዲመራመሩ እንዲፈትሹ ያነሳሳል ብዬ አስባለሁ። የዚህ መፅሐፍ ደካማ ጎኖች የምዕራፎች አደረጃጀት እና የዋቢ መፃሕፍት አጠቃቀስ ላይ ነው። ምዕራፎች በወጉ አልተደራጁም። ዋቢ ስራዎች አጠቃቀስ ላይ ቸልተኝነት ይታያል ይህ መስተካከል አለበት።

Advertisement

FAO e-learning course “Introduction to forest and landscape restoration


Sign up for the new FAO e-learning course Introduction to forest and landscape restoration (FLR).


This course aims to introduce the key concepts and steps of FLR. The course presents the benefits of FLR and important aspects to consider when implementing, managing and monitoring FLR, as well as barriers and success factors.  


Anyone with an interest in FLR may sign up.  Access the course through the FAO e-learning Academy by clicking here


Giorgio Maria Millesimi
Forest and Landscape Restoration Mechanism 
Forestry Division  Food and Agriculture Organization of the United Nations     Tel:  +39 3661182096www.fao.org/in-action/forest-landscape-restoration-mechanism/en/  

Statement by President Joe Biden on the Crisis in Ethiopia


የአሜሪካ መንግስት ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ከነጩ ቤተንግስት በቀጥታ ቆፍጠን ያለ ትእዛዝ ሰጥቷል።

1• ባስቸኴይ የተኩስ አቁም ስምምነት ተደርጎ ጦርነት እንዲቆም።

2• የአማራ ሃይል እና የኤርትራ ሃይል ባስቸኴይ ትግራይን ለቆ እንዲወጣ።

3• ሁሉን አቀፍ ንግግር ተደርጎ ብሔራዊ መግባባት ላይ እንዲደረስ ሁኔታዎች እንዱመቻቹ።

ይህ ትእዛዝ በቀጥታ ከፕረዚደንቱ እንዲወጣ በጽናት ለታገሉት የትግራይ ልጆች ይህ ከፍተኛ የድፕሎማሲ ድል ነው። በወታደራዊ ትግል ጊዜያዊ ማፈግፈግ ቢያሳዩም በዲፕሎማሲ ዘንድ በጽናት፣ በቁርጠኝነት እና በህብረት በመቆም የበላይነትን አሳይተዋል። ትግራይ ከፈራረሰችበት ፍርስራሽ ወጥታ እንደገና በክብር ቆማ በልጆቿ የምትተዳደርበት ጊዜ ሩቅ አይደለም።

Universities grappling with mandatory COVID-19 vaccines issue as fall return to campus approaches


%d bloggers like this: