Hawalle IIllishinke!! እንኳን ለሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!!!  Happy Fichee Cambalaalla!!_2021


Fichee-Chambalaalla The New Year Celebration is one of the interesting holidays typical to the Sidama Nation of Ethiopia

#Hawalle_IIllishinke!!#እንኳን_አደረሳችሁ_አደረሰን!!!  #Happy_Fichee_Cambalaalla!!

Hawalle Sidaamu Diru Soorro Ayyaanira Fichee-Cambalaallate Keerunni Illishino’ne; Iillishinonke!


መላው የሲዳማ ማህበረሰብ እንኳን ለሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል ፊቼ-ጫምባላላ በሰላም አደረሳችሁ!

[MULUGETA] Library & Information Service : 21st Century Information Retrieval & Dissemination Network wishes a Happy Fichee-Cambalaalla, New Year, to all Sidaama people and Ethiopians. The New Year festival, therefore, enhances equity, good governance, social cohesion, peaceful co-existence, and integration among all peoples and the diverse ethnic groups in Ethiopia.

***ስለ ፍቼ-ጨምበላላ በዓል በጥቂቱ***

የሲዳማ ህዝብ ዘመን መለወጫ የሆነውና በ UNESCO ደረጃ በማይዳሰሱ የአለም ቅርሶች ተርታ የተመዘገበው የፍቼ ጨምበላላ በዓል በቀዘቀዘ መልኩም ቢሆን እየተከበረ ነው። *****

የፍቼ በዓል የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ነው። በሲዳማ ዓመት የሚቆጠረው የጨረቃ እና የከዋክብት ዑደት በመከተል ሲሆን ዑደቱን በመመልከት ፍቼ የሚከበርበትን ቀን የማሳወቅ ኃላፊነት ያለባቸው አያንቶዎች (Traditional Astronomers) ናቸው።

በፍቼ ጨምበላላ ወቅት የሚከናወኑ በርካታ በዓላዊ ክንውኖችን ቅድመ- ፍቼ እና ድህረ- ፍቼ ክንዋኔዎች በሚል መክፈል ይቻላል።

በቅድመ- ፍቼ በዓሉ (ፍቼ) የሚውልበትን ቀን የመቁረጥ(ላላዋ)፣ ስለቀኑ ከሀገር ሽማግለዎች ጋር መምከር(ፋጆ)፣ በዓሉ የሚከበርበትን ቀን ሕዝብ በሚሰበሰቡበት ማወጅ(ላላዋ)፣ ጭሜሳዎች ስላላፈው ዓመት በሰውና በእንስሳ ስለተፈፀመ በደል ንስሃ እየገቡ የሚፆሙበት (ኡሱራ)፣ የፍቼ ቀን መቃረቡን ማብሰሪያ የጭሜሳዎች ቄጣላ (ሳፎተ ቄጣላ)፣ ወጣቶች ለበዓሉ የሚያስፈልጋቸውን ልብስና ቁሳቁስ ሟሟላታቸውን እየገለፁ የሚከውኑት ቄጣላ(አድቻ ቄጣላ) እና ከፍቼ ዕለት በፊት የሚከናወን ሁሉን አቀፍ ዕርቅ (አራራ) ዋነኞቹ ክንውኖች ናቸው።

የፍቼ ዕለት (ፊጣራ) በመባል የሚታወቅ ሲሆን በዕለቱ ከ9:00 ወይም 10:00 ሰዓት ገደማ ደጅ ላይ በአግድም በእርጥብ እንጨት መሿለኪያ (ሁሉቃ) ተሠርቶ ሰውና የቤት እንስሳት በዚያ የሚሾልኩበት፣ ከአሮጌው አመት ወደ አዲሱ የመሸጋገር ተምሳሌት ይከናወናል። ከ12:00 ሰዓት ጀምሮ ደግሞ ቡሪሳሜ በሻፌታ ተዘጋጅቶ በወተት በጋራ ይበላል። ቡሪሳሜ በጋራ የመቋደስ ሥርዓት መጀመሪያ በጎሳ መሪ ወይም ጭሜሳ ቤት ይሆንና እንደየ እድሜ ቅደም ተከተል በዙር ሁሉም ቤት ይደረሳል።

በማግሥቱ ቀኑ ጫምባላላ በመባል የሚታወቅ ሲሆን ይህ ቀን ለልጆች፣ ለከብቶች፣ለዱር እንስሳትና ለተፈጥሮ ልዩ ቀን ነው።በጫምባላላ ዕለት ልጆች ከቤት ቤት እየዞሩ “አይዴ ጫምባላላ!” እያሉ እናቶች “ኢሌ ኢሌ” ብለው ቡሪሳሜ እያበሉአቸው ቀኑን ሲቦርቁ ይውላሉ። ከብቶችም ጥሩ ግጦሽ ወዳለበት የሚሰማሩበት፣ በአርጩሜ የማይመቱበት ዕለት ነው። የዱር እንስሳት የማይታደኑበት፣ የዛፍ ቅርንጫፍ የማይቆረጥበት ዕለትም ነው – ጫምባላላ።

ከጫምባላላ ዕለት ቀጥሎ ሁሉም ጎሳ በየጉዱማሌው ደስታውን፣ ቅሬታውን፣ ሃዘኑን፣ ተስፋውን በአጠቃላይ ስሜቱን በቄጣላ፣ በፋሮና ልጃገረዶች በሆሬ ክዋኔ ለሁለት ሳምታት የሚገልፁበት ጊዜ ይሆናል። የፍቼ ማሳረጊያ ዕለት ፊቺ ፉሎ ይባላል ። በዚህ ዕለት ሁሉም ሰው ወደ ታላቁ ጉዱማሌ ይከትማል። በዕለቱ የአባቶች ቄጣላ፥ የወጣቶች ፋሮና የልጃገረዶች ፋሮ ክዋኔ ልዩ ነው።

እንኳን ለሲዳማ ህዝብ ዘመን መለወጫ ፍቼ ጨምበላላ በዓል አደረሳቹ፣ አደረሰን!!

Hawalle Sidaamu Diru Soorro Ayyaanira Fichee-Cambalaallate Keerunni Illishino’ne; Iillishinonke!

Advertisement

Librarians leading together to change the world


“Librarians leading together to change the world” – Read the article by Loida Garcia-Febo in InfoToday Europe 👉https://bit.ly/2SpWJ1O

“We are living in historic times! Cohesive library leadership at national and global levels is important to bring transformative change that benefits communities deeply impacted by COVID-19 and to establish a vibrant future for global libraries”, writes international library consultant Loida Garcia-Febo.

%d bloggers like this: