“የኦሮሞ ማንነት እና ታሪኩ” በታቦር ዋሚ


በእዉቁ የታሪክ ምሁር በአቶ ታቦር ዋሚ “የኦሮሞ ማንነት እና ታሪኩ” በሚል ርዕስ የተጻፈ የታሪክ መጽሃፍ ዛሬ ይመረቃል፡፡

መጽሃፉ በ684 ገጾች የተቀነበበ ሲሆን በዋናነት የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ግንባታ ያለዉን ታላቅ ሚና በስፋት ያወሳል፡፡ በመጽሃፉ የኦሮሞ ህዝብ ማንነት (ኦሮሙማ)፣ የኦሮሞ የገዳ ስርዓት፣ በኦሮሞ ህብረተሰብ ዘንድ የዉትድርና ሚና፣ በኢትዮጵያ የተካሄዱ ትላልቅ ጦርነቶችና የኦሮሞ ጀግኖች ተሳትፎን፣ በኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ እና በማህበራዊ ጉዳዮች የኦሮሞ ህዝብን ሚና በስፋት እና በጥልቀት ይዳስሳል፡፡ በመጽሃፉ በኢትዮጵያ በተደረጉ አዉደ ዉጊያዎች፣ የራስ ጎበና ዳጬ፣የራስ ወልደሚካኤል ጉዲና፣ የፊታዉራሪ ገበየሁ ጉርሙ፣ የዳጃዝማች ባልቻ ሰፎ፣ የቁሴ ዲነግዴ፣ የደጃዝማች ገብረማሪያም፣ የወረጃረሶዉ አቢቹ፣ የደጃዝማች ገረሱ Dhuኪ፣ የራስ አበበ አረጋይ፣ ሜጀር ጀነራል ጃጋማ ኬሎ፣ ደጃዝማች በቀለ ወያ፣ኮሎኔል አብዲሳ አጋ ደጃዝማች ገነነ በdhaኔ ፣ ፊታዉራሪ ጅማ ሰንበቴ፣ ሜጀር ጀነራል ሙሉጌታ ቡሊ፣ ሜጀር ጀነራል ደምሴ ቡልቶ፣ ሜጀር ጀነራል መርዕድ ንጉሴ እና የሌሎችም የጀግንነት፣ የጦር ሜዳ ዉሎ እና ለኢትዮጵያ አንድነት የከፈሉት መስዋዕትነት በዝርዝር ቀርቧል፡፡ በማህበራዊ ዘርፍ በስነ ጽሁፍ፣ በስነ ጥበብ በሙዚቃ የ እን ገብረ ክስርቶስ ደስታ ነገዎ፣ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን፣ አለቃ ተክለየሱስ ዋቅጅራ፣ ጥላሁን ገሰሰ፣ አሊ ቢራ፣ ኮሎኔል ሳህሌ ደጋጎ፣ በስፖርት ዘርፍ ሻለቃ ባሻ ዋሚ ቢራቱ፣ ሻምበል አበበ ቢቂላ ሻምበል ማሞ ወልዴ፣ ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ፣ አትሌት ጌጤ ዋሚ፣አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ፣ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ፣ የአትሌት መሰረት ደፋር የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ከፍ ብሎ እንዲዉለበለብ፣ የኢትዮጵያ ክብር በአለም አደባባይ ከፍ እንዲል ያደረጉትን ተጋድሎ እና አበርክቶ ይዘክራል፡፡ለህዝቦች ነጻነት እና እኩልነት የታገሉ እነ ጀነራል ታደሰ ብሩ፣ የመቶ አለቃ ማሞ መዘምር፣ ኮሎኔል አለሙ ቅጤሳ፣ ጀነራል ዋቆ ጉቱ ፣ ሃይለማሪያም ገመዳ ፣ መገርሳ በሪ፣ ሃይሌ ፊዳ፣ ነdhii ገመዳ፣ አገሪ ቱሉ፣ባሮ ቱምሳ፣ ዘዉገ ቦጂኣከ፣ ከበደ ብዙነሽ፣ኤሌሞ ቂልጡ፣ ጃራ አባ ገዳ ሃጂ አደም ሳዶ፣ሲሳይ ኢብሳ፣ ሼክ በክሪ ሳጳሎ፣ ጉተማ ሀዋስ፣ አቡነ ጴጥሮስ (መገርሳ በdhaaሳ)፣ ኦነስሞስ ነሲብ፣ አስቴር ገኖ፣ ቄስ ጉዲና ቱመሳ እና የበርካታ ጀግኖች ያልተነገሩ ገድሎችን ያነሳል፡፡

መጽሃፉ ስለ ኦሮሙማ (ኦሮሞነት፣ Oromoness) እንዲህ ይላል…“ኦሮሙማ የኦሮሞ ማንነት መሰረት ነዉ፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ሲናገር “ Oromummaan hundee Oromooti” ይላል፡፡ ኦሮሙማ በኦሮሞነት ማመን ነዉ፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ኦሮሞ የሚያሰኙት የማንነቱ መገለጫዎች በጋራ እንዲጠቀም፣ ባህሉ እንዲያድግ ጥረት ማድረግ ማለት ነዉ፡፡ … ኦሮሙማ የኦሮሞን ታሪክ፣ ባህል፣ ፖለቲካ ፣ ቋንቋ ማወቅ እና መገንባት ማለት ነዉ፡፡ ……ኦሮሙማ እንደ ርዕዮተ ዓለም የሰዉን ልጅ ነጻነት ማስከበር፣ የኦሮሞን የዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ራዕይ እና የብዝሃ ብሄር ዴሞክራሲን የሚጨምር ነዉ፡፡ ኦሮሙማ … በኦሮሞ ማህበረሰብ ዉስጥ ሰዉ ልጆች እኩልነት ጥረት ማድረግ… የኦሮሞን ቋንቋ ማሳደግ፣ የሃይማኖት እኩልነትንና ሌሎችንም ልዩነቶች መቀበልና ማወቅን ያካትታል፡፡…. (ከገጽ 60-63)መጽሃፉን ገዝታችሁ አንብቡት፣ በእጅጉ ታተርፉበታላችሁ!

መልካም ቅዳሜ

Source: 𝙠𝙪𝙨𝙝 𝙞𝙣𝙨𝙞𝙙𝙚𝙧 FB Page

ርዕስ – “የኦሮሞ ማንነት እና ታሪኩ”

ፀሀፊ – ታቦር ዋሚ

የገፅ ብዛት – 684

ሚያዚያ 2013 አዲስ አበባ.

(ቀጥሎ የምታነቡት ፅሁፍ እንደ መፅሀፍ ግምገማ/አቃቂር (book review) ባይታይ እመርጣለሁ። በመፅሀፉ ላይ ሙሉ ግምገማም ሆነ አቃቂር የመፃፍ ፍላጎቱም ጊዜውም የለኝም። መፅሀፉን እንዳነበበ አንድ ግለሰብ ያልተስማሙኝን ነገሮች ብቻ ነው ያሰፈርኩት።በዚሁ አጋጣሚም መፅሀፉን ገዝታችሁ እንድታነቡት እጋብዛለሁ።).–By Eyasped Tesfaye

የኦሮሞ ማንነት እና ታሪኩ የተሰኘው አዲሱ የታቦር ዋሚ መፅሀፍ በ 3 ዋና ዋና ክፍሎች የተከፈለ ነው።የመጀመሪያው የመፅሀፉ ክፍል በ 5 ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን -የሰው ልጆችን ክሳቴ (በዝግመተ ለውጥ መነፅር)-የኩሽ ህዝቦችን መነሻ – መገኛ እና ታሪክ -የኦሮሞ ማንነትን- በኦሮሞ Mythology የፍጥረት አጀማመር እንዴት እንደሚታይ- ገዳን – ዋቄፈታን – የኦሮሞን የታሪክ ፅንሰ ሀሳብን እና ፍልስፍናን-የፊንፊኔን ጥንታዊ እና ዘመናዊ ታሪክ-በኦሮሞ ህብረተሰብ ዘንድ ውትድርና ያለውን ሚና ወዘተ በወፍ በረር ለማስቃኘት ይሞክራል።የመፅሀፉ ሁለተኛ ክፍል እና ሰፊውን የመፅሀፉን ቦታ (ከገፅ 204- 520) የያዘው ክፍል ለኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ፀንቶ መቆም ከፍተኛ ውለታ ውለዋል የሚላቸውን ኦሮሞዎች በመዘርዘር ታሪካቸውን በአጭር በአጭሩ ያስቃኛል።በሁለት ምዕራፎች የተከፈለ ሲሆን በጦርነት እንዲሁም በፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ዘርፎችከጎበና ዳጬ እስከ አትሌት መሰረት ደፋር – ከራስ መኮንን ጉዲሳ እስከ ተፈሪ በንቲ በርካታ ኦሮሞ ግለሰቦች ለሀገረመንግስቱ የዋሉትን ውለታ ለማሳየት ይሞክራል።የመፅሀፉ ሶስተኛ ክፍል ሀገረ መንግስት እና የሀገረ መንግስት ግምባታ ምንድነው የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ይሞክራል። የኦሮሞ ብሄርተኝነት ጥያቄዎች እና ግቦች “እነኚህ” ናቸው በማለት ለመበየን ይሞክራል። “አብዮተኞች” የሚላቸውን ኦሮሞ ግለሰቦች ታሪክ በአጭሩ ለማስቃኘት ይሞክራል።.የመፅሀፉ የመጀመሪያ ክፍል ላይ የግል አስተያየት-.የመፅሀፉ የመጀመሪያው ክፍል በአጠቃላይ ከተቀረው የመፅሀፉ ክፍል በይዘትም በሀሳብም የተሻለ ነው። ሆኖም ግን ከታች ያልተስማሙኝን ነገሮች ነቅሼ አውጥቻለሁ።.የምንጭ አጠቃቀም ችግር በመፅሀፉ መግቢያ ላይ በደራሲው የተጠቀሱት ወጣት ባለስልጣን ምንጭ መጥቀስ በዛ የሚል አስተያየት ሰጥተውኛል ቢሉም ደራሲው በእኔ እይታ ግን መፅሀፉ በአጠቃላይ የምንጭ ጥራት እና እጥረት ችግር አለበት። ደራሲው በመግቢያው ገፆች ላይ እንደሚገልፁት በተለይ የመጀመሪያውን ክፍል የፃፉት በ ፕ/ር መኩሪያ ቡልቻ “Contours of the emergent and ancient oromo nation” እና በዶ/ር ገመቹ መገርሳ “sacred knowledge traditions of the oromo of the horn of Africa” መፅሀፎች ጫንቃ ላይ የተንጠለጠለ ነው።ከምንጭ እጥረት ባለፈ በተለያዩ ቦታዎች ላይ በምንጭነት የተጠቀሱት ግለሰቦች በተነሳው ርዕሰ ጉዳይ ላይ መሪ ሊቅ (Authority) ያልሆኑ እና ፅሁፎቻቸውም በምንጭነት ለመጠቀስ የማይበቁ ናቸው።ለአብነትም በመፅሀፉ የመጀመሪያ ክፍል እንዲሁም 3ኛው ክፍል ላይ “ብሄርተኝነት ምንድነው?” “ብሄርተኝነት እና ሀገረ መንግስትነት ምንድናቸው?” ወዘተ የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ በብቸኛ ምንጭነት የቀረበው አንዳርጋቸው ፅጌ እና “የአማራ ህዝብ ትግል ከየት ወዴት” የምትለው መፅሀፉ ናት።አንደኛ ብሄርተኝነት/Nationalism ላይ እድሜ ልካቸውን ምርምር ያደረጉ ሊቀ ጠበብት ባሉበት አለም አንዳርጋቸውን ዋቢ አድርጎ መጥቀስ አግባብ ካለመሆኑ ባሻገር አንዳርጋቸው ራሱ “ተሳስቼ ነው የፃፍኩት – በቂ እውቀት በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ባልነበረኝ ጊዜ ነው የፃፍኩት” እያለ በተደጋጋሚ የሚያንቋሽሸውን ፅሁፉን ብቸኛ ምንጭ አድርጎ ማምጣት ተገቢ ነው ብዬ አላስብም።በሌላ ቦታ ደግሞ (ገፅ 66) በማያዳግም መረጃ እና ማስረጃ ሊፃፍ የሚገባው የኦሮሞ ስነፍጥረት Mythology ላይ ምንጭ ተደርጎ ከተጠቀሱት አንዱበአንድ “ዛሬ” የሚል ስም በነበረው ጋዜጣ ላይ “አኑ ዋቆ” በሚል የብዕር ስም የወጣ ፅሁፍ ነው። ፀሀፊው ማነው? ማስረጃው ምንድነው? ምንም የሚታወቅ ነገር የለም። በርካታ ምንጮች ሊጠቀሱበት በሚችል ርዕሰ ጉዳይ ላይ በአንድ የቆየ ጋዜጣ ላይ በብዕር ስም የወጣን ፅሁፍ እንደ ምንጭ አድርጎ መጠቀም እጅጉን ግር የሚል ነገር ነው።። ይህ ማለት በአሁኑ ዘመን በአንድ ፌክ አካውንት ፌስቡክ ላይ የተለጠፈን ፅሁፍ ምንጭ አድርጎ ከመጠቀም አይለይም።በተመሳሳይ መልኩ በ 3ኛው የመፅሀፉ ክፍል ላይ ስለ ሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ቀጣይነት ለማስረዳት”አንድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር በአንድ ወቅት እንደተናገረው” የሚል ምንጭ ተጠቅሷል (ገፅ 522) ይህ የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ማነው? ምንድነው? መቼ ነው ይህንን የተናገረው? ምን መድረክ ላይ? ወዘተ የሚለው ግን በመፅሀፉ ላይ አልተመላከተም። እንዲህ ያለው ምንጭ አጠቃቀስ ምን ሊባል እንደሚችል አላውቅም።.የኢትዮጵያን ነባር እና ስሁት ብያኔ የማስቀጠል ችግር።.የመፅሀፉ አስኳል ለሆነው ሁለተኛው የመፅሀፉ ክፍል መድላድል የፈጠረው ከክፍል አንድ ጀምሮ በደራሲው ሲመላከት የቆየው “የኢትዮጵያ እንደ ብሄረ ሀገረ መንግስት የ ብዙ ሺህ አመታት ታሪክ ባለቤት” መሆኗ ነው።በደራሲው እምነት “ኢትዮጵያ ከሶስት ሺህ አመታት በላይ የዘለቀ የአገረ መንግስትነት ታሪክ አላት” (ገፅ 6)”ይህ የአገረ መንግስትነት ታሪክ ደግሞ እስከ ዘመናችን ድረስ እንዲዘልቅ ከማድረግ አኳያ የኦሮሞ ህዝብ ግንባር ቀደም ሚና ነበረው” (ገፅ 6)በዚህ መነሻ ላይ መድላድላቸውን ሰርተው የሚነሱት ደራሲው በመፅሀፉ ሁለተኛው ክፍል ላይ ኦሮሞዎች ለኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ፀንቶ መቆም ያደረጉትን ተጋድሎ ለማሳየት የበርካታ ኦሮሞ ግለሰቦችን ታሪክ እያነሱ ይሞግታሉ።በመሰረቱ ኢትዮጵያ እንደ ብሄረ ሀገረ መንግስት ለበርካታ ሺህ አመታት ኖራለች ብሎ ማሰብ ከኦሮሞ ብሄርተኝነት ፅንሰ ሀሳብ “ሀሁ” ዎች ጋር እንዴት ሊታረቅ እንደሚችል አላውቅም።አሁን ኢትዮጵያ በምትባለው አገረ ግዛት ስር በታሪክ የራሳቸው የመንግስትነት ታሪክ ያላቸው፣ የራሳቸው ነፃ አስተዳደር የነበራቸው፣ ህዝቦች እንደነበሩ ማመን እና ኢትዮጵያ እንደ ብሄረ አገረ መንግስት ለበርካታ ዘመናት መኖሯን ማመን እርስ በርስ የሚጋጩ ነገሮች መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል። .የመፅሀፉ ሁለተኛው ክፍል ላይ የግል አስተያየት:-.ቀደም ብዬ እንዳነሳሁት የመፅሀፉ ሁለተኛ ክፍል የተፃፈው ኢትዮጵያ አንደ አንድ አሀድ የብዙ ሺህ አመታት የአገረ መንግስትነት ታሪክ አላት የሚለውን መቅድም ልባዌ (presupposition) ይዞ ነው።በሁለተኛው ክፍል መግቢያ ላይ ደራሲው ስለ ሁለተኛው የመፅሀፉ ክፍል እንዲህ ይላሉ”ለኢትዮጵያ አገረ-መንግስት ግንባታና ህልውና ውድ ህይወታቸውን እየሰጡ፤ ኢትዮጵያን በመጠበቅና በማጠናከር ሂደት ኦሮሞዎች ዋልታና ማገር የመሆናቸውን ያህል የአገረ መንግስት ግንባታው ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መሰረቱ ግን ፍትህ ሲጎድለውና ጫናው ሲበዛ ነፃነቱን ፍለጋና እኩልነትን ለማግኘት ሲታገል ቆይቷል….የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄም እነዚህ ተሟልተውለት ታሪክን ባህሉ በአጠቃላይ ማንነቱ ታውቆለት በሰላም የጀመረውን የአገር ግንባታ በበለጠ ሁኔታ መቀጠል እንደሆነ በስፋት ይተርካል” (ገፅ 203)ደራሲው በሚያስቀምጡት ደረጃ በኢትዮጵያ አገር ግንባታ ላይ ኦሮሞ የአንበሳውን ድርሻ ይዞ ከነበረ የኦሮሞ ብሄርተኝነት መነሾ የሆኑ ጥያቄዎች በስህተት ላይ የተንጠለጠሉ ነበሩ ማለት ነው።የኢትዮጵያ የአገረ መንግስት ግንባታ ሂደት እጅግ እግላይ የነበረ – ባለቤት እና ባዳ፣ ገዢ እና ተገዢ፣ ጨቋኝ እና ተጨቋኝ፣ አስገባሪ እና ገባር፣ ጌታ እና ባሪያ የነበረበት መሆኑ ነው በየቦታው ላለው የብሄርተኝነት ጥያቄ ማቆጥቆጥ ዋናው ምክንያት እንጂ ኦሮሞን ጨምሮ ሁሉም ብሄሮች የተካተቱበት የአገር ግንባታ ቢኖር ኖሮማ እዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ ውስጥ ባልተገባ ነበር።(በመሰሩቱ የአድዋን ጦርነት ጨምሮ በአለም ላይ የብሄርተኝነት (ሀገራዊም ሆነ ንዑስ) ፅንሰ ሀሳብ ከመጀመሩ በፊት የተደረጉ ጦርነቶች ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች loyalty ለንጉሱ እንጂ ለ Nation አልነበረም። ምክንያቱም Nationalism በራሱ የቅርብ ጊዜ ክስተት ስለሆነ።)ደራሲው ኦሮሞ አገረ መንግስቱን በመገንባት ግንባር ቀደም ሚና እንደነበረው ለማሳየት በርካታ የኦሮሞ ስም/ደም አላቸው የሚሏቸውን ሰዎች በአስረጅነት በማቅረብ ይሞግታሉ።ደራሲው ያልመለሷቸው ሁለት ጥያቄዎች ግን የሚከተሉት ናቸው።1- እነዚህ የተዘረዘሩት ግለሰቦች ራሳቸውን እንደምን ነበር የሚያዩት (Self consciousness) እንዲሁም በዘመኑ ይኖር የነበረ ኦሮሞ እንደምን ነበር የሚያያቸው የሚለውን ነው።2- የተዘረዘሩት ግለሰቦች አደረጓቸው የተባሉትን ገድሎች የፈፀሙት በውኑ ደራሲው እንድናምን እንደሚፈልጉት ለኢትዮጵያ አገረ መንግስት ግንባታ በማሰብ ነበር ወይ?.ደራሲው የኦሮሞ ስም እና “ደም” አለው ያሉትን ሰው ሁሉ ለማካተት የሄዱቡት ርቀት የሚደንቅ ነው። ለምሰሌ ለአገር መንግስቱ ግንባታ አስተዋፅኦ ያደረጉ ኦሮሞዎች ብለው ስማቸውን ከዘረዘሯቸው እና ታሪካቸውን ካሰፈሩላቸው ሰዎች መካከል አንዱ “አለቃ ተክለኢየሱስ ዋቅጂራ” ናቸው።የአለቃ ተክለ ኢየሱስን “የኢትዮጵያ ታሪክ” የሚል መፅሀፍ ያነበበ ሰው አለቃ ተክለኢየሱስ “ጋ*” ብለው ለሚጠሩት ህዝብ የነበራቸውን ንቀት እና ጥላቻ በሚገባ ይረዳል።አለቃ ተክለ ኢየሱስ ጎጃም ተወልደው ያደጉ እና ራሳቸውንም በፅሁፎቻቸው ላይ ጎጃሜ ነኝ ብለው የሚያስተዋውቁ ግለሰብ ነበሩ። የአለቃ ተክለ ኢየሱስን ስራ እንደ ኦሮሞ ስራ ቆጥሮ መፃፍ ለምሳሌ በአሁኑ ሰአት ታምራት ነገራ የሚሰራው ስራ የኦሮሞን ህዝብ የሚወክል ነው ከማለት ጋር አንድ አይነት ነው።በደም እና በስም ቆጠራ ሄዶ የኦሮሞ ስም እና ደም ያላቸው ግለሰቦች የሰሩት ስራ ኦሮሞን ይወክላል ከተባለቢያንስ – ጣይቱ ብጡል፣ አፄ ሀይለስላሴ፣ ኮ/ል መንግስቱ ሀይለማሪያም ኦሮሞን ወክለው ነው አገር የገዙት ከማለት የሚገድበን ነገር የለም።ደራሲው በዚህ መልኩ – ጎበና ዳጬን፣ መኮንን ጉዲሳ (የአፄ ሀይለስላሴ አባት) ፣ አለቃ ተክለኢየሱስን፣ የደርግን ተፈሪ በንቲን፣ መርዕድ ንጉሴን፣ ደምሴ ቡልቶን እና ስፍር ቁጥር የሌላቸውን በርካቶችን ታሪክ በሰፊው አስፍረዋል።.የመፅሀፉ ሶስተኛ ክፍል ላይ የግል አስተያየት:-.በሶስተኛው ክፍል ላይ ደራሲው ሀገረ መንግስት ምንድነው? የሀገረ መንግስት ግንባታስ ምንድነው? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የሞከሩበት ነገር ግን አንዱንም ሳይመልሱ ያጠናቀቁበት ክፍል ነው። ከመፅሀፉ በሙሉ ያልተመቸኝ ይህ ሶስተኛው ክፍል ነው።ደራሲው ሀገረ መንግስት ምንድነው? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ 2 ምንጮችን ብቻ ተጠቅመዋል።እነኚሁም የጠ/ሚ አብይ አህመድ መደመር የሚለው መፅሀፍ እና የአንዳርጋቸው ፅጌ “የአማራ ህዝብ ትግል ከየት ወዴት” የምትለው አነስተኛ ክታብ።ደራሲው የጠ/ሚሩን መፅሀፍ ጠቅሰው የኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ግንባታ አንዳንዶች እንደሚሉት በቅኝ ግዛት እንዳልሆነ እና ብቻ ባህላዊ የግዛት ማስፋፋት እንደሆነ ለማስረዳት ሞክረዋል።ደራሲው የፈለጉትን ማመን መብታቸው ቢሆንም ቢያንስ ግን ለአንባቢው በመፅሀፋቸው ክፍል አንድ ላይ በሰፊው የተጠቀሙት የ ፕ/ር መኩሪያ ቡልቻ መፅሀፍ በዚህ ረገድ ምን እንደሚል ቢያስቀምጡ ጥሩ ነበር።”ባህላዊ የግዛት መስፋፋት” በሚለው መነሾ የተነሱት ደራሲው የኦሮሞ ብሄርተኝነት እንቅስቃሴን በዚሁ ማዕቀፍ ስር ብቻ ለመበየን ሞክረዋል።ደራሲው የኦሮሞ ብሄርተኝነትን እንደሚከተለው ይበይኑታል”የኦሮሞ ብሄርተኝነት አላማ የኦሮሞን ህዝብ ማንነት፣ ባህሉና ታሪኩ ታውቆ በእኩልነትና በጋራ ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ጋር በኢትዮጵያ አገረ መንግስት ውስጥ የነፃነትና የፍትህ ጥያቄዎች ተሟልተው…ለመኖር እንጂ ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ጋር በህብረት ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው የገነቧትን አገር ልማፍረስ እንዳልሆነ ለሁሉም ግልፅ ሊሆን ይገባል” (ገፅ 547).