ABOUT
Affini is an independent media aiming to deliver intellectual ideas and alternative ways to create a strong Sidaama nation, promote its culture and language, advocate inclusiveness and coexistence, advance socio-political and economic development.

አፊኒ መጽሔት በዉስጧየሚከተሉትን
ርዕሰ ጉዳዮች አካታ ይዛለች
አቶ ጥራቱ በየነ ስለ ግርጃ ገጠመኙ እያጫወተን፣ በፖለቲካ አምዷ ከእሳቸው ጋር ለየት ያለ ቆይታ አድርጋለች፣
ስለ ሲዳማ ኢኮ-ቱሪዝም እና ብዝሃ-ሃብት ፣ እንዲሁም በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ውስጥ ስለ 32 ዓመት ቆይታቸው ከቀድሞው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ከፕ/ር ዮሴፍ ማሞ ጋር በእንግዳ አምዷ በርካታ ጉዳዮችን ይዛለች
በኢኮኖሚዋ አምድ በሲዳማ ክልል ግመልና የግመል ተዋፅኦ ስላለው አቅም እንዲሁም የመልማት አቅምን በመተንተን በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስተሩ በተገኙበት ኢንዱስትሪ ፓርክ ካስመረቁት አቶ ብሩ ወልዴ ጋር ጣፋጭ ውይይት ይዛለች
በትግል ገጽ የሲዳማ ወጣቶች በአንድ ድምጽ በፍቅር ከሚጠሩት ኤጄቶ ሳሙኤል ቃሜ ጋር የኋሊት አስጉዛን በሲዳሙ አፎ ድንቅ ቆይታ ተከስታለች
የኢዜማ አመራሮችን በሀዋሳ በአንድ አጋጣሚ አግኝታ ‘ጭምብላችሁን አውልቁ’ በማለት በዛ በፈታኝ ጊዜ ድምፅ የሆነችው የሲዳማ ሴቶች አልበገር ባይነት ምሳሌ የኑ በፉራ አምድ የህይወት ወጓን ታጫውተናለች፤
በማህበራዊ አምዷ ሁለገቡና ለተቸገሩት ፈጥኖ በመድረስ የሚታወቀው አርጋው አየለ (ትራምፕ) ስለ 96ቱ ልጆቹ፣ በደቡብ ኦሞ ከሞት ጋር ስላደረገው የፊት ለፊት ግጥሚያ እና ወደ #ሰላም_ባንክ (ከሀገረ አቀፍ ወደ አለም አቀፍ እያደገ ያለውን አስደናቂ ጫወታ ይዛለች።
በተጨማሪ በወርሃ ታህሳስ 2013 ዓ.ም በሞት ስላጣነው ተወዳጁ ጋዜጠኛና ሰብአዊ መብት ተሟጋች ሀብቴ ያዕቆብ የትግል ታሪክ እና ራዕይ ባለቤቱ፣ ዳያስፖራ ጓደኞቹ እና ወዳጆቹ የመሰከሩትን አጠናቅራለች።
Sidaamu Singapoore Di’ikkaka? የሚል መጠየቃዊ አጭር ፅሁፍ በውስጧ አክላለች።
እንድሁም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እና አነጋጋሪ ርዕሰጉዳዮችን ይዛ ወደ አንባቢዎቿ ደርሳለች።#አድራሻ ፦ሀዋሳ ቱሩፋት ዮሐንስ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ አፊኒ ቢሮ ስልክ : 0996858227
እንድሁም ወደ ሁሉም ሲዳማ ወረዳ ከታች ባለው ስልክ አማካይነት ማግኘት ትችላላችሁ።
አዲሰ አበባ፦ ልደታ ሲዳማ ኮሙኒቲ ቢሮ እና ቦሌ አትላስ ወ/ሮ ብርነሽ ሆቴል (SIDAMA INN)
እንድሁም በሁሉም ክ/ከተማ ለማግኘት ስልክ: 0911047683
Email ፦affinimedia@gmail.com
አፊኒ ሚድያና ኮሙኒኬሽን የህዝብ ሚድያ
Quqquxuni Agarraayiti Affini Maxaaficho Dikkote aana hossu.
Kala Xiraatu Beyyenehu Girja Hookkote xaandosire qummisanna Hala’lado Polotiku Hasaawa Hadhe kataffi yitewo
.Sidaamu Kalaqamu jironna Kalaqamu Turizime daafira hattono 32 Diro Jawa rosu Uurinshara keeshshewohu Prof. Yoseef Maammo Ledo Dancha hasaawa assinoyi.
Sidaamu giddo Gaala sirsa dandiinayitanna noota latate jilbba kala Birru Woldehu ledo hattono lowo rosicho cu’mishiishanna.
Sa’numota Sharrote doogo duumba qole leellishanna Kala Samueeli Belaynehu ledo Coommado Hasaawa amaddino.
IZEEMA Baragisiisinota sharrote wirsu gede albaani higasenni afantinota Beetto Yenu Tesfayeta Furra qoolinni hanqafino.
Sadaasi agani giddo hedeweelcho lubbameenna hongummo Rodiinke Habte Yaaqowihu daafira, galitesinna Baxillanosi ledo assinoyi Hasaawano amaddewo.
Hattono babbaxitewo hajubba aana la’oosheenna Titirsha haadhe nabbawaanosewa daggewo.#Teesso Affini Media and Communication
You must be logged in to post a comment.