ሐሙስ መጋቢት 9 ቀን 2013 ዓ.ም በዶ/ር ደምስ መጽሐፍ ‹‹ኮርፖራቶክራሲ እና…›› ምረቃ ላይ በኢትዮጵያ ሆቴል ተገኝታችሁ ለታደማችሁ ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን፡፡ በወ/ሮ ማርታ ኃይለማርያም ፕሮግራም መሪነት፣ በፕሮፌሰር በላይ ስመአኒ እና በአዲስ አበባ ዩኒቭርስቲ የዶክትሬት ትምሀርት እጩ መኮንን መንገሻ የቀረቡት ትችቶችና ምክረ ሐሳቦች፣ በታዳሚው የተነሱት አስተያየቶች እጅግ በጣም ገንቢና ታዳሚውንም ያረኩ እንደነበር ተረድተናል፡፡ ዶ/ር ደምስንም ለበለጠ ተጨማሪ የመፃፍ ሥራ የሚያነሣሣቸው እንደሚሆን ይታመናል፡፡
የሸገር ሬድዮ በኤፍ.ኤም 102.1 እሁድ መጋቢት 5 ቀን 2013 ዓ.ም. ጠዋት ከ2-3 ሰዓት በነበረው የምዕራፍ ፕሮግራም ከዶ/ር ደምስ ጋር አድርጎት የነበረውንና ለሕዝብ የቀረበውን በአዲሱ መጽሀፍ ላይ የተደረገውን ቃለ መጠይቅና ምላሽ እርሶም ያዳምጡት ዘንድ ልከልንዎታል፡፡
የሸገር ሬድዮ ስለ ኮርፖራቶክራሲ አዳማጩ ግንዛቤ ይኖረው ዘንድ ላደረገው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡
መልካም ጊዜ
ነቃ ሕይወት በየነ
መርሀ-ግብር ሥራ አስኪያጅ
ደማር ኢትዮ-አፍሪክ