የሰበር ችሎት ውሳኔዎች ቅጽ 24 ዲጂታል ቅጂ ይፋ ተደረገ

The Federal Supreme Court of Ethiopia -የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት

 · የሰበር ችሎት ውሳኔዎች ቅጽ 24 ዲጂታል ቅጂ ይፋ ተደረገ**********************የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች ቅጽ 24 የዝግጅት ምእራፉን አጠናቆ ለፍርድ ቤት ማህበረሰብ፣ ለህግ ባለሙያዎች፤ ለህግ ት/ት ተማሪዎችና መምህራን እና ሌሎች ባለድርሽ አካላት ተደራሽ ተደርጓል፡፡ የሰበር ውሳኔዎች ቅጽ 24 ጂታል ቅጂ በፍርድ ቤቱ ቴሌግራም ገጽ The federal supreme court of Ethiopia (https://t.me/fscethiopiaPR/60) ላይ ይገኛል፡፡በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ የህግ ትርጉም የተሰጠባቸው የሰበር ውሳኔዎች ተደራሽነት ለማስፋት በፍርድ ቤቱ የጥናትና የህግ ድጋፍ ዳይሬክቶሬት በኩል የተዘጋጀ ሲሆን ቅጹ 80 ውሳኔዎችን ይዟል፡፡ ከነዚህም መካከል 22 ውሳኔዎች የፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግን፤ 5 ውሳኔዎች የቤተሰብ ጉዳይን፤ 3 ውሳኔዎች የአሠሪና ሰራተኛን፤ 12 ውሳኔዎች ንብረትን ፤ 6 ውሳኔዎች ንግድና ኢንሹራንስን፤ 3 ውሳኔዎች ውልን፤ 2 ውሳኔዎች ከውል ውጪ ኃላፊነትን፤ 2 ውሳኔዎች ግብርን፤ 16 ውሳኔዎች የወንጀል ሕግን፤ 5 ውሳኔዎች የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግን እና 4 ልዩ ልዩ ጉዳዮችን የተመለከቱ ውሳኔዎች ናቸው፡፡ቀደም ሲል ፍርድ ቤቱ አዘጋጅቶ ይፋ ያደረጋቸውን የሰበር ውሳኔዎች ቅጾች በህትመትና በበይነ መረብ እያሰራጨ ቢሆንም ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን የቅጂ (የሞራል) መብት ባላከበረ መልኩ በተለያዩ መንገዶች ቅጾቹ እየተዘጋጁና እየተሰራጩ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ተረድቷል፡፡ ይህ ተግባር ለውሳኔዎቹ (ለቅጾቹ) ተደራሽነት መጨመር የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ትልቅ እንደሆነ ቢታመንም የተሳሳተና ፍ/ቤቱ ማያውቃቸው ውሳኔዎች ሊካተቱበት ስለሚችሉ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው መሆኑን አዘጋጅ ክፍሉ አሳስቧል፡፡https://t.me/fscethiopiaPR/60የፌ/ጠ/ፍቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Advertisement

Author: Mulugeta Woldetsadik, Librarian/Information Professional at Hawassa University (HU), Ethiopia

Mulugeta Woldetsadik, Librarian/Information Professional @ Hawassa University, , Sidama Region, Ethiopia

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: