አስተዉሎት፤  <> ብሔር  አልባ ከሆነ  አሀዳዊ ዘረኝነት ይሆናል

Celeberations of birra
Re-imagining Ethiopia putting the people but not the land and/or its geographic features at the center of our imagination! 

ክፍል ሦስት (የመጨረሻዉ)

ዛሬም አስቀድሜ የምለዉ ነገር አለኝ።የግድ ነዉ። 150 ዓመታት ቀላል አይደለም።ባርነት ለአንድ ቀንም ይከብዳል የኦሮሞ ብሔር (ሕዝብ) የራሱ የሆነ ፖለቲካዊ ማህበራዊና ባህላዊ  የማንነት  ገጽታዉን  ያካተተ የገዳ ሥርዓቱን ጨምሮ  ፈጣሪዉን የሚያመሰግንበት ባህላዊ የምስጋና ቀን  በዓሉን መልካ እሬቻ ፣ በአሃዳዊ ልሙጥ  <<ኢትዮጵያ /ኢትዮጵያዊነት>> ከፈረሰበት ጊዜ ወዲህ በሆራ ፊንፊኔ  ላይ ሊያከብር  የተቃረበበት ሰሞን ዉስጥ ሆኜ ለመጻፍ ብዕሬን ሳነሳ በእርግጥም ይህን ማስቀደሜ ትክክል ነዉ ።

ማንም ለኦሮሞ ሕዝብ የሰጠዉ ገጸ በረከት አይደለም ። ይህ ማንነትን የማስመለስ ሥራ  ለዘመናት በትዉልድ  የትግል ቅብብሎሽና  መስዋዕትነት  የተገኘ ዉጤት ነዉ። የእናት  አባቶቹን  አደራና ሀቅ  ያልዘነጋዉ  የኦሮሞ ብሔርትኛ ትዉልድ  ቄሮ  በኦሮሞ  ብሔር ቁመት ልክ  ተፈጥሮአዊ  ነፃነቱን  ለማስመለስ  ዓለምን  ያስደመመ ሰላማዊ  ትግል ታግሎ  ደምን ሕይወቱን ከፍሎ ያፀናዉ  ነዉ ።እሬቻ  በኦሮሚያ  እምብርት ፊንፊኔ  አዲስ አባባ  ላይ ባለፈዉ እሁድ  በተካሄደ  ሩጫ  ታስቧል።  በሰላም ተጀምሮ   በሰላም አልቋል  መልጽክት አለዉ።  ሃቅ የሆነ  የእውነት   ትንሳኤ በዚህ መልኩ ፍንትዉ  ብሎ  ለዓለም ሲቀርብ  ለሰዉ ዘር ሰብዓዊነት ሞገስ ይሆናል።

ይህ ብቻ አይደልም።  ጥሩ <<የመደመር>>  ጅማሬ  በአቃፊዉ የኦሮሞ  ሕዝብ  ፈጣሪን  የማመስገን  ኢሬቻ  በዓል  ዋዜማ  ላይ በተካሄደዉ  ሩጫ  የጭቁን  ብሔሮች መሳተፍ ታይቷል።  ይህ የሚደንቅ  የእውነተኛ  የሕዝቦች  ህብረትን  የመፍጠር  ግብዓት  ነዉ። ደስ ይላል  በቀጣዩ  የመልካ ሆራ  ፊንፊኔ  እሬቻ  በዓል  ላይም  ብሔር  ብሔረሰቦች  የባህላቸዉን  አልባሳት  በመልበስ  እንዲሳተፉ  ጥሪ ተደርጓል። በጣም ደስ ይላል።  የሕዝቦች እንድነት  በልሙጥ  ዘረኛ አሃዳዊነት  ፕሮፓጋንዳ አይመጣም።  የዚህ እኩይ  ዲስኩር  ምንጩ ይታወቃል።  ለመቶ ሃምሳ ዓመት  የነበረ ግዙፍ  ዲያቢሎሳዊ  አስተሳሰብ  ነበር ። ከእንግዲህ በብሔሮች  ህልዉና  እና በብሔርተኞች መራር ትግል  ዉጤት ላይ እያሾፈ  መቀጠል የለበትም። ኢምፓየሪቷን  የዉስጥ  ግጭቶችን  ጦርነቶች  ምንጭ ሆኖ ለዘመናት ሲያምሰን ከርሟል።  አሁን በቃ በኃይማኖት  በፖለቲካ  በአርት (የሙዚቃን ጨምሮ) … ወዘተ ሽፋን  መርዙን እየረጨ  ሰላምን እንዲያደፈርስ  ቀዳዳ መክፍት የለበትም። የሕዝቦች እስተዉሎትና  ንቃት እንዲዳብር  ይበልጥ መሰራት እንዳለበት  ይሰማኛል። የትኛዉም ብሔር  ለአሃዳዊ  ልሙጥ ዘረኝነት  ካባ ለመሆን  ራሱን ዝቅ ማድረግ  የለበትም።  እዉነተኛ ተፈጥሮአዊና  የብሔር ልዕልና  ለዚህ ዓይነቱ  የሰዉ ዘር ነቀርሳ  አመለካከት ተሸካሚ  ለመሆን  እልተፈጠረም ። ግልፅ ነዉ አሁን ወደ  ተከታዩ  ፅሁፌ  መጨረሻ ክፍል ልመለስ።  ባለፈዉ ሁለት ተከታታይ   ክፍል ለአንባቢ ላሳይ የፈለኩት  በአሃዳዊዉ <<ኢትዮጵያ /ኢትዮጵያዊነት>> ካባ ዉስጥ ያለዉን ፀረ የሕዝቦች እዉነተኛ አንድነት ባህሪ ነበር።  ዛሬም በዚሁ ነጠብ ላይ ነዉ የምጨምረዉ

የብሔር ጭቆና  በምንም መልኩ ቢታይ በታሪክ ዉስጥ ከፍታ አልነበረዉም። አይኖረዉምም ።ለዚህ ሩቅ መሄድ  ላያስፈልገን ይችላል በዚሁ ወር ዉስጥ በገሃድ አይተነዋል ።በጠ/ሚ/ር ዓብይ <<የመደመር /ህብር>> ራዕይ ሥር በመወሸቅ በቤተመንግሥት በተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ ታይቷል።  በሙሉ የዝግጅቱ ይዘትና ቅርፅ ውስጥ  የተገለጠዉ የሰዉ  ዘር ጠላትነቱ ነዉ።  በእርሱ ላይ ብዙ ተነግሯል። ጭቁን ብሔሮችም የልሙጥ አሃዳዊነት  <<ኢትዮጵያ /ኢትዮጵያዊነት>> ትክክለኛ ባህሪዉን ይብልጥ አዉቀዉታል።

 አሃዳዊነት የሰላም ጠንቅ ነዉ። አሃዳዊነት የብሔርች ጠላት ነዉ። የዚሀ ሥርዓት  <<ኢትዮጵያ /ኢትዮጵያዊነት>> በራሱ የመላዉ ኢትዮጱያ ብሔርች  አንስንት ደመኛ ነዉ ። በእርሱ ዉርድት  እንጅ ፣ንቀት እንጅ ፣ ሽብር እንጅ ፣ ጠብ እንጅ  ከፍታ የለም።

በዘፈን በሞሽሩት ያዉ ነዉ  ።ሥራዉ ነፃነትን መቃረን ነዉ።  በግጥም ቢያቅራሩበት ፈቀቅ የለም ።ያዉ የምቀኝነት ፖለቲካ  ከመሆን  አይሻለዉም።  ኃይማኖትን  እንደ ካባ ቢያለብሱት  ለዉጥ የለዉም ። ባህሪዉ ኃለ ቀር አስተሳሰብ  ነዉ ።በልዩነት ህብር ፊት መቆም እይችልም ።ለዘመኑ የብሔርች  ህብር  <<መደመር >> እንቅፋት እንጅ ግብዓት ለመሆን ያለተዘጋጀ  የዚህ አፍራሽ  ሥርዓት  ተሸካሚ  የፖለቲካም ሆነ  የአስመሳይነት  <<ሀይማኖት >> ቡድን እንቅስቅሴ በአንክሮ  እየተከታተሉ መግለጥ  የለዉጡ ባለቤቶች  ድርሻ መሆን አለበት ብዬ አምናለሁ።

አሃዳዊነት በህዝቦች  ወይም ብሔሮች የነፃነትና የለዉጥ ትግል ታሪክ የለዉጥ ጊዜን የመቀማት ልምዱ  ዛሬ የጀመረ አይደለም። ከራርሟል የ1966 ዓ.ም.  ወቅት  ዞር ብለን ካሰብን ይህንኑ የዛሬዉን  ድርጊቱ  ነዉ ።የምንገኘዉ  ልዩነቱ  በአዲሱ  ሔርተኛ ትዉልድ  ትግል እየተገኘ  ያለዉ  ለዉጥና  ጊዜዉ ከ1966 ዓ.ም.  በእጅጉ የተሻለና ልምድ  ያዳበረ መሆኑ ነዉ ።

በእርግጥ ሰሞኑን የአሀዳዊ ልሙጥ ዘረኝነት  አራመጆች  ዓይናቸዉን  ወደ ማርክሳዊ  ሌኒናዊ  ወደ ሆነዉ  የአስተሳሰብ ምንጭ  ሩስያ አንስተዋል  የድረሱልኝ የጥገኝነት ጥያቄን  ፖለቲካዊ  በማይመስል ሆኖም በትክክል ፖለቲካዊ በሆነ አቅጣጫ  አቅርበዋል።  ይህም <<ከፍታ>> በተባለለት  ታሪክ  ዉስጥ <<ዉርደት >> አመላከች ነዉ ።

በ20ኛዉ ክፍለ ዘመን ጅማሮ ላይ <<የሶሻሊስት  አብዮትና >> የራዕዩን  ግብ <<ኮሚኒዝም>> አድርጎ  በከፍተኛ  ደረጃ  ተነቃንቆ  እንደነበረ ታሪክ ይነግረናል።  ዝርዝር  ሁኔታ  ዉስጥ አልገባም  ከእኔ በላይ  በዚህ ላይ አሃዳዊያኑ <<ኢትዮጵያ /ኢትዮጵያዊነት>> አራማጆች ያዉቀታል።  እስከ ዉድቀቱ ማለቴ ነዉ ።

የሚደነቀዉ ግን  ይህ የዓለምን ወዛደሮች  በማሰባሰብ  ኢምፔሪያሊዝምን  አስወግዶ ዓለም አቀፍ  <<አንድነት >>  በእኩልነት  ላይ ለማምጣት  በተደረገዉ ሙከራ ዉስጥ  የብሔር  ጉዳይ ተራ  አጀንዳ አልነበረም።  የልሙጥ  <<ኢትዮጵያ /ኢትዮጵያዊነት>>  ሀይሎች  እዚህ <<መንደርተኝነት -ጎሰኝነት>>  ብለዉ በራሳቸዉ የጠበበ አመለካከት  ዉስጥ ልያሳንሱት እንደሚሞኩርት አልሆነም።  ሌኒን  <<የሶሻሊስት  አብዮትና  የብሐራዊ ነፃ አዉጪ  ትግሎች  ዘመን >>  በሚለዉ ሰፊ ትንተና ዉስጥ እነደ እነሱ ሸምጥጦ እልካደም  በዚያ ወቅት የነበረችዉ የሩሲያ ኦርቶዶክስ  በቴክርስቲያን በቆኖናዊ ትምህርቷ የብሔርችን ነፃነትና  ቋንቋ ለመርግም ሞክራለች ብዬ  አላስብም።  በቀጣይ ይህን ከታሪክ መፈተሽና  ማየት እንችላለን  አሁን ማለት የፈለኩት የብሔር ጥያቄ  በሶቭየት ህብረት /ሩሲያ  <<ከፍታ ዘመን>> ተራ ጉዳይ አልበረም። የሚለዉን ነዉ ።

የሚደንቀዉ 1969 ዓ.ም. የብሔርች ንቅናቄ ወደ ወጥ መስመር የገባበትና  አንድ እርምጃ ወደፊት የተራመደበትን ለዉጥ በግርግር ከእጁ  ያስገባዉ  ወታደራዊዉ ደርግ <<የብሔር ጥያቄን>> ን በቀጥታ በተፈጥሮአዊዉ እዉነታ ከመቀበል ይልቅ  በራሱ እይታ  አርትፊሻል ቅርፅ ሰጥቶ የኢትዮጱያን  አሃዳዊነት ለማስቀጠል  በመሞከሩ የመጨረሻ ዉጤቱን አይተናል።

ለደርግ አሃዳዊ   <<ኢትዮጵያ /ኢትዮጵያዊነት>> ሶቭየት ህብረት የቅርብ ወዳጅ ነበረች።  ይህች ሶቭየት ሩሲያ ደግሞ   የጀርባ ታርኳ ምን ነበር??… በቀጥታ እጠቅሳለሁ።  ከዛሬ አርባ ሁለት ዓመት  በፊት  ከተነበበዉ አዲስ ፋና መፅሔት  <<የታሪክ ዓምድ>>  <<ሩሲያ የመደብ ጭቆና  ብቻ  የሰፈነባት ሳትሆን የብሔረሰቦችም  እስር ቤት  ነበረች። ሩሳዊያን  ያልሆኑት  ቡዙዎቹ  ብሔረሰቦች  የተናቁና የተዋረዱ  ነበሩ ።የዛሩም መንግሥት ሩሲያዉያን  ሌሎች ሕዝቦችን እንዲንቋቸዉ አድርጓቸዋል።  በብሔርሰቦች መሀልም  ስምምንት እንዳይኖር መንግስቱ  በተለያዩ  ብሔረሰቦች  መሀከል ጠብ ይጭር  ነበር።>> (ገጽ 19/1969 ዓ.ም.  የወጣ)

እንግድህ ከጎርቫቾቭ በፊት  የነበረች ሩሲያ – ሶቨየት ይህች ናት። አሃዳዊነት በሶቨየት በአጭሩ ይህ ነዉ።  በብሔሮች መካከል ጠብ የሚጭርና ህዝቦችን የሚንቅ  ሥርዓት   ስለ <<አንድነት >> ዲስኩር በዓለም  አቀፍ  ደረጃ  በከፍተኛ  የብረትና  የኢኮኖሚ  አቅም ተደግፎ  ቢነሳም  ዉጤቱ የታየ ነዉ።  ዛሬ የሩሲያ  ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን  ይህን ይለፈችበትን  እዉነታ ታሪክ ተሞክሮ  ገፍታ የኢትዮጱያን አሃዳዊ ልሙጥ ፖለቲካን  በሀይማኖት ሽፋን ድጋፍ <<ትሰጣለች>> ብሎ የቋመጠ ቡድን በእርግጥ የሚያሳየዉ ተራ መቅበዝበዝን ነዉ።

ለአዲስቷ የሁሉም ነፃ ብሔሮች ህብር  ህብረት  ኢትዮጱያ የምትቀርበዉ ሩሲያ አይደለችም።  በፍፁም ። የሚቀርቡት በኢምፓየራዊ ጭፍልቃ ሥር የማቀቁት  ሁሉም ብሔሮች ናቸዉ።  ሩሲያ  የብሔሮች እሥር ቤት ነበረች። አሃዳዊት ኢትዮጱያ የብሔሮች እሥር ቤት ነበረች።      ይህ ግልፅ ነዉ ።የዛሩ መንግሥት  ከዉስጡ  የወጣዉ  የሩሲያ ብሔር ሌሎችን  የመናቅ  የዘረኝነት  ሰለባ  ዉስጥ ገብቷል ።ይህን የፈጠሩት ከሶቨየት ኢምፓየር  ነፃ የወጡት  ህዝቦች  አይደሉም።  ጠባቡ የዛሩ አገዛዝ እንጅ።  እዚህም እንደዛዉ ነዉ ።በቤመንግሥት  ዉስጥ በእኩይነቱና  በሰዉ ዘር ጠላትነቱ በላዩ ላይ ሊገጠምበት የሚገባዉ የዛሩ /የሩሲያዉ የብሔር ጭቆና አራማጅ ገዥ ታናሽ ወንድም  የሆነዉ የነፍጠኛዉ  ሥርዓት (አሀዳዊ <<ኢትዮጵያ /ኢትዮጵያዊነት>>) እንጅ በመደመር ሁሉን ለማቀፍ የመጀመሪያዉን እርምጃ የተራመደዉ የኦሮሞ የለዉጥ ኃይል ቄሮ  አይደለም።  ሁሉም ብሔሮች  አይደሉም። ከታሪክ መማር ብልህነት ነዉ።

በ1966 ዓ.ም.  የነበረዉን የፖለቲካ ቁማር  በልሙጥ አሃዳዊነት  ዙሪያ የተሰበሰቡ ቡድኖች  ሊጫወቱ  ሲሞክሩ የሚያሳፍር ነዉ።  የብሔር ጥያቄን  አረዳድና አፈታት ላይ ደርግ ፣ኢዲዩ ፣ ኢህአፓ፣ መኢሶን … ወዘተ  የነበሩ የፖለቲካ  ቡድንና ኃይላት  ዙሪያ  አስገራሚ ቁማርተኞች  እንደነበሩ  የታሪክ መዛግብታት ያስታዉሱናል ።ብሔርትኝነት ዛሬ  ባለዉ  የለዉጥ ትዉልድ  ንቃት ኅሊና  ደረጃ  ለዚያ ዘመኑ  የፖለቲካም ሆነ  <<የኃይማኖታዊ >> ካባ ቁማር የሚያመች አይደለም።  ብሔሮች ዛሬ ታግለዉ  ባመጡት  ለዉጥ  ዉስጥ የዉሸት እንድነትን  ሊኖሩት ቀርቶ ሊያስቡት  አይፈልጉም።

ከየብሔሩ  ግለሰቦችን በመያዝ  <<የብሔር ጨቋኝ  ገዥ መደብ >> በማቋቋም በአንድነት ስም  ሊፈናጠጠበት የሚፈልጉ  የሩሲያ  የዛሩ  መንግስት ወይም የአሃዳዊዉ የቀድሞዉ የነፍጠኛ ሥርዓት አፍቃሪዎችን  በራሱ ነፃነት ላይ እንዲፈናጠጡ የሚፈቅድ  ብሔር የለም። ይህ ነወ ግልፅ መሆን ያለበት ።

ኢትዮጰያዊነት  በዜግነት ደረጃ ከፍ የሚለዉ በነፃ  የብሔሮች  ብሔርትኝነት ከፍታ ላይ  በመደመር ነዉ። ኢትዮጱያ  እንደ አገር  በከፍታ መቀጠል  የምትችለዉ  በነፃ ብሔርች ይሁንታ ለጋራ ጥቅም  በጋራ  በመደመደር  ሲሆን ብቻ ነዉ።

እንኳን  የኢትዮጱያ ኢምፓየር ያኛዉም የሶቨየት ህብረት  ኢምፓየር  ቀድሞዉን  ያመነዉ በግድም እዉቅና የሰጠዉ የብሔርን ጥያቄ ነዉ።  የብሔርን ጥያቄ  እውቅና ሰጥቶ  የብሔርን ልዕልና  መካድ  ደግሞ  ፖለቲካ አይደለም ። ተራ ወሬ እንጅ … ከዚያዉ  መፀሔት ልጥቀስ  ታሪክ ከኋላችን የሚለዉ አተያዩን።

<<ጭቆና ትግልን ስለሚዎለድ የብሔረሰቦች ጭቆና  ባለበት ክፍለተ ሀገር  ከዚህ ጭቆና  ነፃ ለመዉጣት ብሔራዊ  የነፃነት  ትግሎችን  አስከትሏል። የብሔረሰቦች ጭቆና  የብሔረሰቦች ቅራኔ ባለበት  በማንኛዉም  አገር  ዉስጥ የተበዝባዥ መደቦች  ትግል ከብሔረሰቦች  ትግል  ተነጥሎ  ሊታይ አይገባዉም  ።>>

ይኸዉ  ነዉ። ጭቆና ትግልን ይወልዳል።  የብሔር  ጭቆና  አሃዳዊነትን ጠራርጎ የሚያስወግድ  የብሔር ነፃነት ትግልን  ወለደ  ተፈጠሮአዊ ነዉ። በግጥም የስድብ ጋጋታ  ወይም  በዘፈን  ቀረርቶ አይጨነግፍም።  አሁን በኢትዮጱያ ያለዉ መሬት የረገጠ   ሀቅ ነዉ።  ችግርችን  በብሔር ጥላቻ መፍታት አይቻልም።  ለትብብር አይጠቅምም ።ለአንድነት አይፈይድም።  ከቤተ-መንግሥት  እስከ የተከበሩ  ዓለም አቀፍ ኃይማኖቶች  ዙሪያ  በተንኮል መርመጥመጥ  የኋላ  ኋላዉ  ቅሌት ነዉ። ለሁላችንም ለዉጡን ካስገኘዉ  አዲስ ህብረ-ብሔራዊነት /ፌድራሊዝም/ የፖለቲካ  አስተሳሰብ ጋር መደመሩ አዋጪ  ይሆናል ።

በክፍል አንድ እና ሁለት በዚህች ብዕሬ  ያሰመርኩበት  ሀሳብ  የብሔርችን  ተፈጥሮአዊ እዉነታ  ከሙሉ  ነፃነት ጋር  መቀበል  የአገራዊ   ምስረታ  ፋይዳዉ ትልቅ መሆኑን ነበር። ዛሬም የምደመድመዉ ይህንኑ በማሰረገጥ ነዉ።  ከክፍል  አንድ ፅሁፍ  ይህን ደግሜ  ልበለዉ።

<< ዛሬ በተለይም እንደ እዉነተኛ የህዝቦች  የጋራ አገርና የብሔርች  ህብረት  ጉዳይ  ለአንድነትና ለሉዓለዊነት  ከፍተኛ ድርሻ ያለዉን  የኦሮሞ  ሕዝብ  በአባት አገሩ ላይ ሊኖረዉ የሚገባዉን  ሕጋዊ  መበቱን በተለያየ አቅጣጫ  የመዳፈር ስትራቴጂያቸዉ  የሚጠቁመዉ  የአገሪቱ ቀንደኛ   የችግር ምንጭ መሆናቸዉን ነዉ። >> የዛሩና የነፍጠኛዉ  ሥርዓት  ከኋላችን ናቸዉ።  የሚታወቁት ጥላቻን ብሔሮች መሀል  በመዝራት ነዉ።  የነርሱ <<አንድነት>> የህዝቦች  አይደለም።  የአንድነት ጠላት የሆነ  አፍራሽ  አስተሳሰብ ነዉ።  አንድን ብሔር  በንቀት  ሥነ ልቦና  አሳስተዉ  በዉስጡ  የሚሸሸጉበት ጊዜ አክትሟል ። ለጋራ አገር  ምሥረታ ጠቃሚዉን ክፍል  በመጠቆም ይህችም ብዕር የበኩሏን ብላለች።  አዋጪዉን  በክፍል እንድ ጠቁማለች።  እጠቅሳለሁ።

<<ብዙ ብሔር ብሔረሰቦች  በራሳዉ  የተፈጥሮአዊ  ቁመት  መጠን  በኢትዮጱያ  የቀድሞ ኢምፓየራዊ አገር  አመሰራረት ዉስጥ እንዳሉ  በግልፅና  በቁርጠኝነት  ማመን ነዉ   >>

አንባቢያን- ዛሬም በዚሁ  አስተሳሰብ  ይህን  የመጨረሻ ክፍል እቋጫለሁ በቅን ለዉጡን  ለማስቀጠል  አሃዳዊነትን እያጋለጥን  እንደ ብሔሮች  መቀራረብና  መወያየትን  መቀጠል ይኖርብናል።  ብሔር-አልበ  አመለካከት  ይከፋፍለናል።  ይበልጥ ያራርቀናል።  ለዉጡ  የመጣዉ  ልዩነትን ለማክበር ነዉ። ህብረትን  ለመፍጠር  ነዉ ። ቸር ክረሙ  መልካምና  የመልካም ሆራ ፊንፊኔ  እሬቻ በዓል!… አበቃሁ ።

ምንጭ፤ ጉላሌ ፖስት ቅጽ  01 ቁጥር 23 መስከረም 2012 ዓ.ም. በኤፍ .ቢ.ገዳ/ብሾፍቱ/

 

Author: 21st Century Library & Information Technology Network [Information & Knowledge Dissemination Platform By Mulugeta Woldetsadik, Librarian/Information Professional at Hawassa University, Ethiopia]

Mulugeta Woldetsadik, Librarian/Information Professional @ Hawassa University, , Sidama Region, Ethiopia

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: