Nagaasoo Gidaadaa (PhD) eenyu turan? – ተስፋዬ ገብረአብ ፣ ሌንጮ ለታ ና ገብሩ አስራት ስለ ዶ/ር ነጋሶ


safe_image NG

Umurii ganna 76 jiraatan keessaa gara caalu siyaasa Oromoofi Itoophiyaaf kennan, Dr. Nagaasoon.

Oduu kana irraa waa’ee isaanii ni hubattuu dubbifadhaa 👉👉https://bbc.in/2ZDz65b

_106648778_ddddd

የተወለዱት በምዕራብ ኦሮሚያ ደምቢዶሎ ከተማ ነው ። የመጀመሪያ ድግሪያቸውን በያኔው ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ ከሠሩ ጥቂት ዓመታት በኋላ ወደ ጀርመን አቀኑ። ከተማሪዎች እንቅስቃሴ ጀምሮ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የህይወት ዘመን ተሳትፎ አድርገዋል ሊባል ይችላል።

ለበርካታ ዓመታት ከኖሩባት ጀርመን ሲመለሱ የአሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ኦህዴድን ተቀላቀሉ። የቀድሞ ፕሬዝደንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ህልፈት ባለፈው ቅዳሜ ነበር ለዓመታት ከኖሩበት ከወደ ጀርመን የተሰማው።

ዶ/ር ነጋሶን አንዳንዶች በእጅጉ በመርህ እንደሚያምን ፖለቲካኛ ሌሎች ደግሞ ለፖለቲከኛ የሚሆን ስብእና የሌላቸው አድርገው ይስሏቸዋል።

ዶ/ር ነጋሶ -የጋጤኛው ማስታወሻ “የታሰረ አንበሳ”

ብዙዎች በአፃፃፍ ችሎታው በተደነቁበት የጋዜኛው ማስታወሻ መፅሃፉ ተስፋዬ አብረአብ ዶ/ር ነጋሶን ቤተ መንግስት ውስጥ እንደታሰረ አንበሳ ገልጿቸዋል። ኋላ ግን ኢህአዴግን ተለይተው የተቃውሞ ፖለቲካውን በመቀላቀላቸው እሳቸውን የሚያይበት መንገድ መቀየሩን ተስፋዬ ይናገራል።

የታሰረ አንበሳ ያላቸው ምንም እንኳ አቅም ቢኖራቸው ህወሃትን ያገለግሉ ስለነበር እንደሆነ “የጋዜጠኛው ማስታወሻ የታሰረው አንበሳና በኋላ በህዝብ ጉዳይ ላይ በሰፊው የተሳተፉት ዶ/ር ነጋሶ የተለያዩ ናቸው” በማለት ያስረዳል።

ኋላ ላይም ዶ/ር ነጋሶና ተስፋዬ ይገናኙ እንደነበር ተስፋዬ ይናገራል። የሚገናኙት በኢሜልና በስልክ የነበረ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ በአንድ ፎረም ላይ ዶ/ር ነጋሶ ሊያቀርቡት በነበረ ፅሁፍ ምክንያት እንደነበር ያስታውሳል።

ዶ/ር ነጋሶ የማስታወቂያ ሚኒስትር ሳሉ በወቅቱ የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት መምሪያ ሃላፊ ለነበረው የተስፋዬ አለቃው ነበሩ። እሱና ሌሎች ባልደረቦች ያናግሯቸው የነበረው እንደ ጓደኛ እንደነበር፣ ራሳቸውን ከፍ የማያደርጉ ፣ አክብሩኝም የማይሉ ሰው እንደነበሩ ይናገራል።

“ሚኒስትር እያሉ ከመኪና ወርደው ሱቅ ላይ ሲጋራ ገዝተው የሚሄዱ ሰው ናቸው” ሲልም ያክላል።

በጋዜጠኛው ማስታወሻ ‘የታሰረ አንበሳ’ ያላቸው እንደ እሳቸው ያለ ጥሩ የታሪክ ምሁር፣ ቅን እና ጥሩ ስብእና ያለው ሰው እንዴት ከዚያ “ሰው በላ” ስርዓት ጋር አብሮ ይሰራል በማለት እንደሆነም ይገልፃል።

ህገመንግሥቱ መከበር አለበት የሚል አቋም እንደነበራቸው ይህ ብቻም ሳይሆን ሊከበር ይችላል ብለው ያስቡም እንደነበር የሚናገረው ተስፋዬ “ይህ ቅንነታቸውን ያሳያል ።ይህ ቅንነታቸው ደግሞ ከፖለቲካ ሰው የማይጠበቅ ነበር ” ይላል።

‘ኢህአዴጉ’ ዶ/ር ነጋሶ እና ‘ኦነጉ’ ሌንጮ

አቶ ሌንጮ ለታና ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉት አንድ ላይ ነው። አብሮ አደጎች ነበሩ ማለት ይቻላል።

የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሳሉ ብዙ አፍሪካ ሃገራት ከቅኝ ገዢዎቻቸው ነጻነታቸውን የተቀዳጁበት ወቅት ስለነበር የራስን መብት በራስ ስለመወሰን ብዙ ጊዜ ያወሩ እንደነበር አቶ ሌንጮ ያስታውሳሉ።

አቶ ሌንጮ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አሜሪካ ሲያቀኑ ዶ/ር ነጋሶ ደግሞ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲን ተቀላቀሉ። በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ዶ/ር ነጋሶ የተማሪዎች ንቅናቄ ተሳታፊ እንደነበሩ አቶ ሌንጮ ያስታውሳሉ።

እኛ የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን ስንመሰርት እሱ ለትምህርት ጀርመን ነበር። በወቅቱ የታሪክ ትምህርት ለማጥናት ነበር የሄደው።

“አንተ ውጪ ሃገር ሄደህ ታሪክ ተማር እኛ ታሪክ ሰርተን እንጠብቅሃለን ብዬው እንደነበር ከብዙ ጊዜ በኋላ አስታውሶኛል። እኔ ግን ረስቼው ነበር።”ይላሉ አቶ ሌንጮ

እንደ አቶ ሌንጮ አገላለፅ ዶ/ር ነጋሶ በጣም እልኀኛና በአንድ ጉዳይ ላይ አቋም ከያዙ ወደኋላ የማይሉም ናቸው። ምን ይደርስብኛል ብለውም አያስቡም።”ለዚህም ይመስለኛል ከኢህአዴግ ጋር የተለያየው።”ይላሉ።

“ፕሬዝዳንት በነበረበት ወቅት ለስራ ወደ ውጪ ሃገራት ሲሄድ ብዙ ጊዜ ተገናኝተን እናወራ ነበር። ያው እኔ ኦነግ እሱ ደግሞ ኢህአዴግ። ነገር ግን በሃሳብ ብቻ ነበር እርስ በርሳችን የምንታገለው።”

ነጋሶ ጊዳዳ

“በኢህአዴግ ክፍፍል የወሰደው አቋም ታሪካዊ ነው”

በወቅቱ ትግል ላይ የነበረው ህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ ህወሃት ነጋሶን ጀርምን ሃገር ሳሉ እንዴት እንደቀረበና እንዳነጋገራቸው የቀድሞ የህወሃት ማእከላዊ ኮሚቴ አባልና የአረና ፓርቲ መስራች አቶ ገብሩ ገ ያስታውሳሉ።

ዶ/ር ነጋሶ ኦህዴድ ፤ አቶ ገብሩ ደግሞ ህወሃት ሆነው ብዙ ጊዜ በማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባዎች ይገናኙ ነበር። ሁለቱም ኢህአዴግን ለቅቀው በመውጣ እንደገና በተቃዋሚ መስመር ሰልፍ ላይም እንደገና ተገናኝተዋል። እናም አቶ ገብሩ ዶ/ር ነጋሶን በእነዚህ ሁኔታዎች ሁሉ አይተዋቸዋል።

ዶ/ር ነጋሶ ከኢህአዴግ ከተለዩ በኋላ ደምቢደሎ ላይ ተወዳድረዋል የአንድነት ፓርቲ ሊቀ መንበር ሆነውም አገልግለው ነበር።

“አቋም ያለው ቅን ሰው ነው። ብቻውንም ቢሆን ላመነበት ነገር እንደሚቆም ያረጋገጠ ሰው ነው” በማለት ይገልጿቸዋል አቶ ገብሩ ዶ/ር ነጋሶን።

በተለይም በኢትዮጵያና በኤርትራ ጦርነት ከዚያም ኢህአዴግ ውስጥ መከፋፈል ተፈጥሮ በነበረበት ወቅት የያዙትን አቋም ከዚያም ኢህአዴግ አምባገነን ሆኗል ብለው ድርጅቱን የለቀቁበትን ሁኔታ አቶ ገብሩ ያስታውሳሉ።

በጥቅሉ “ላመነበት ነገር ቆሞ ያለፈ ሰው ነው” በማለት ነው የሚገልጿቸው።

ኢህአዴግ ከባድ መከፋፈል ውስጥ በነበረበት በዚያ ወቅት ድርጅቱ አምባገነን እየሆነ አደገኛ መንገድ ላይ መሆኑን ብዙዎች ሊሞግቷቸው ይቅርና ሊያናግሯቸው በሚፈሯቸው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፊት በግልፅ መናገራቸው ዶ/ር ነጋሶን በፖለቲከኞች በህዝብ ዘንድም ከፍተኛ ነጥብ ያሰጠ እርምጃ ነበር።

“እኔ እንኳን ስብሳባው ላይ አልነበርኩም ግን ጓደኛዬ አምባሳደር አዋሎም ነግሮኛል። መለስ መንግስቱ የጦር መኮንኖችን አሸንፎ የተናገረውን የሚመስል ነገር ሲናገር ልክ መንግስቱን መሰልከኝ ብሎ በድፍረት ተናግሮታል” ይላሉ። በርግጥም ይህ የዶ/ር ነጋሶ ህይወትና የፖለቲካ እርምጃ ላይ በተፃፈውና “ዳንዲ” በተሰኘው መፅሃፋቸው ላይ የሚገኝ ሲሆን በተባለው ስብሰባ ላይ ተገኝተው የነበሩት አምባሳደር ገነት ዘውዴ ‘እንዴት መለስን ከመንግስቱ ጋር ታመሳስለዋለህ’ ብለው ስለማልቀሳቸውም ተፅፏል።

አቶ ገብሩ ያ ጊዜ አቶ መለስ ዜናዊ በዶ/ር ነጋሶ ላይ ቂም በመያዝ እስከ መጨረሻው ሊያጠቋቸው የወሰኑበት እንደሆነ ያምናሉ። ከዚያ በኋላ በዶ/ር ነጋሶ ላይ የሆነውም የዚህ ማረጋገጫ ነው ይላሉ።

በተቃራኒው ዶ/ር ነጋሶ ብዙ በደል ባደረሱባቸው የኢህአዴግ ሰዎች ቂም እንዳልነበራቸው አቶ ገብሩ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ።

አቶ ገብሩ ራሳቸውም ብዙ በደሎች ቢደርሱባቸውም ገለልተኛ ካልሆነ ስርዓት ፍትህ አገኛለው ብለው ባለማመን ወደ ህግ አልሄዱም። “እሱ ግን ፍርድ ቤት እየሄደ ይሟገት ነበር” በማለት እንደ ቀድሞ ፕሬዝዳንትነት የሚገባቸውን መብት በሚመለከት በሁለት ፍርድ ቤቶች አሸንፈው እንደነበር ይናገራሉ።

“ነገሩ ኋላ የፖለቲካ ውሳኔ ነው የሆነው። የተፃፈለትን ደብዳቤ አሳይቶኝ ነበር አሁንም እጄ ላይ አለ” ይላሉ።

ብዙዎች ‘ዳንዲ፡ የነጋሶ መንገድን” ካነበበሩ በኋላ የዶ/ር ነጋሶ ስብእና የፖለቲከኛ ዓይነት አይደለም የሚል አየስተያየት ሰንዝረው ነበር። አቶ ገብሩ በዚህ አስተያየት በተወሰነ መልኩ ይስማማሉ። ነገር ግን ለሳቸው ችግሩ የዶ/ር ነጋሶ ስብእና ሳይሆን የኢትዮጵያ ፖለቲካ አካሄድ ብልጣብልጥነትና አድርባይነት መሆኑ ነው።

“የመርህና የዓላማ ፖለቲካ የሚያራምድ ሰው በአገራችን ፖለቲካ ቦታ የለውም ይላሉ። እሱ ደግሞ ግልፅ፣ የዋህና ቀጥ ብሎ የሚሄድ ነው” ይላሉ።

“ዶ/ር ነጋሶ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተንኮል መጠን መሳያ”

የ ‘ዳንዲ’ ፀሃፊ አቶ ዳንኤል ተረፈ ለመፅሃፉ ከዶ/ር ነጋሶ ጋር ለሶስት ወራት ቃለ ምልልስ አድርጓል።

ቁሳዊ ነገር ላይ ብዙ ጉጉት የላቸውም የሚላቸው ዶ/ር ነጋሶ የኢትዮጵያ የተንኮልና የሴራ ፖለቲካ ልክ ማሳያ ናቸው ሲልም ይደመድማል።

ኑሯቸው እንደ ቀድሞ ፕሬዘዳንት ሳይሆን እንደ ተራ ግለሰብ እንደነበር የአደባባይ ምስጢር ነው። ህልፈታቸውን ተከትሎ ብዙዎች እንዴት በተለያየ አጋጣሚ እንዳገኟቸው ማህበራዊ ድረ ገፅ ላይ ፅፈዋል።

አንድ ሰው ታክሲ ላይ እንዳገኛቸውና መኪናቸው ጋራጅ ገብቶ እንደሆነ ጠይቋቸው እሳቸውም መኪና የለኝም ብለው በቀጥታ እንደመለሱለትና እሱም ምን ያህል እንደሚያከብራቸው እንደገለፀላቸው በትዊተር ገፁ ላይ አስፍሯል።

አቶ ዳንኤል እንደሚለው ደግሞ ላመኑበት ነገር እንደ ተራ ሰው ከመኖር በላይ ሁሉ ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ ነበሩ ይላል።

ይኖሩ ከነበረበት የሚያፈስ ቤት እንዲለቁ ደብዳቤ ተፅፎላቸው እንደነበር በማስታወስ ” የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጎዳና ተዳዳሪ ሊሆኑ ነው የሚል ፅሁፍ ፍትህ ጋዜጣ ላይ ሲወጣ ነው መልሰው ነገሩን የተውት” ይላል።

እሱ እንደሚለው ውሳኔአቸው የሚያስከፍላቸውን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል የስነ ልቦና ዝግጅት ነበራቸው ዶ/ር ነጋሶ።

እንደ አቶ ገብሩ ሁሉ ገዳይ ጀግና በሚባልበት ፣ ተንኮለኛና ሴረኛ አሸናፊ ሆኖ በሚወጣበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ የዶ/ር ነጋሶ እንደ ገራገር መታየታቸው የሚገርም አይደለም ይላል ዳንኤል።

በኢህአዴግ ሂስህን አውርደህ መቀጠል ፣ ተራ አባል ሆኖ መቀጠል ፣ መሄድ የሚሉ ሶስት ምርጫዎች ሲቀርቡላቸው በመህር ላይ ቆመው ከድርጅቱ ለመልቀቅ የወሰኑ ፖለቲካኛ መሆናቸውን የሚናገረው ዳንኤል “ጥንቁቅ ፖለቲካኛና የሚያምኑበትን ለማድረግ ወደ ኋላ የማይሉ ናችው” ይላል።

የዶ/ር ነጋሶ ሁለተኛ መፅሃፍ በመጠናቀቅ ላይ እንደነበር ዳንኤል ይናገራል። ስነዳ ላይ እጅግ ጎበዝ ናቸው የሚላቸው ዶ/ር ነጋሶ ለቤተ መፃሀፍት የሚሆኑ መፅሃፍት፣ ጋዜጦችና በርካታ ፅሁፎች እንዳሏቸውም ይናገራል።

“ኢህአፓ የበተነው ወረቀት፣ መኢሶን የፃፈው ፅሁፍ ና አንድ ጊዜ ብቻ የታተማ የቀረች መፅሄት እና የአሁኑ መፅሄትና ጋዜጦች እያንዳንዱ እትም የሚገኘው ዶ/ር ነጋሶ ቤት ነው” ይላል።

Via https://www.bbc.com/amharic/

Advertisement

Research4Life – GOALI Promotion & Awareness Training has been Conducted at Hawassa University, Ethiopia, April 19,2019


AS-267463768379441@1440779740176_l.png

DSC_0172
Partial view of Hawassa University, Main Campus

April 19, 2019 Events

Snapshot Photographs were taken during GOALI Promotion & Awareness Training.   

Asfaw Genfetao (Dr.),

CLG Post Graduate Coordinator while addressing the audiences & invites CLG Dean to open the training program. 

IMG_20190419_030209[1]
Tsegaye Tuke (Assistant Professor), CLG Dean,
While he has made an opening Speech to the audiences about the benefits of  GOALI training & pinpoints that the current trends of teaching and learning process is supported not only by print media (physical books) but also inclusive of Electronic Resources and finally addresses an official opening of the training.    
IMG_20190419_030533[1]
Dr.S.Sivakumar  (Associate  Professor),
at CLG, School of Governance & Development Studies Post Graduate Program Coordinator, while addressing the audiences at the session of the training about why it is important to access Scholarly scientific journals and as whole e-resources. 

PowerPoint Presentation By  the Librarian, Main Campus, Hawassa University

IMG20190419090946

IMG20190419091941
Mulugeta W/Tsadik, Librarian, at Hawassa University While Presenting to the audience

IMG20190419091957.jpg

CLG Post Graduate Students Practically started to  access GOALI together with   Librarian  

College of Law & Governance Library

After Powerpoint Presentation by  the  Librarian

Capture LIB.JPG

ለሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ መምህራን፣ ሠራተኞችና ተማሪዎች በሙሉ/Dear All! The forum planned to be held Thursday(10/08/2011) on Ethiopia and Pan-Africanism is postponed due to unnoticed conditions. Sorry for that and will inform you of the change soon.


Dear All! The forum planned to be held Thursday(10/08/2011) on Ethiopia and Pan-Africanism is postponed due to unnoticed conditions. Sorry for that and will inform you of the change soon.

 

Africa Map       Ethiopian Flag

የአፍሪካ ሕብረት 50ኛው  ዓመት ክብረ-በዓል በተከበረበት ወቅት ባሳለፈው ዲክላሬሽን ቁጥር 3(21) አባል ሀገራት የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ አንድነት ምስረታ ሰንደቅ ዓላማን ከሀገራቸው ሰንደቅ ዓላማ ጋር ጎን ለጎን እንዲያውለበልቡ እና የአፍሪካ ሕብረት መዝሙርን ከሀገራቸው ብሔራዊ መዝሙር ጎን ለጎን እንዲዘመር እንዲያደርጉ ውሳኔ ተላልፏል፡፡

በአገራችን በኩል ውሳኔውን ተግባራዊ ለማድረግ የሕግ ማዕቀፍ ስለሚያስፈልግ ረቂቅ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ም/ቤት ቀርቧል፡፡ ረቂቅ አዋጁ በሚኒስትሮች ም/ቤት ከታየ በኋላ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በያዝነው ዓመት ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ስለሆነም አዋጁ ከመፅደቁ በፊት ጉዳዩ የሀገራችን ህዝብ እንዲገነዘበው ለማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ለዚህም በቅድሚያ የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰቦችን መድረስ ቢቻል በቀጣይ ለሚደረግ እንቅስቃሴ አመቺ ይሆናል የሚል እምነት ተይዟል፡፡

በዚሁ መሠረት በኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዘጋጅነት የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች፣ መምህራንና አስተዳደር ሠራተኞች በጉዳዩ ዙሪያ ጥልቅ ውይይት እንዲያካሂዱ መድረክ ተሰናድቷል፡፡

መድረኩ የሚካሄደው ሚያዚያ 10/2011 ዓ.ም (ሐሙስ ጠዋት 2፡30 ጀምሮ) በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ለግማሽ ቀን ስለሆነ ሁሉም የሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ ማህበረሰብ (በተለይም የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች) መድረኩ ላይ እንድትሳተፉ አጥብቀን እናስታውቃለን፡፡ በዕለቱም ለዚህ ዝግጅት ሲባል የመማሪያ ክፍለ-ጊዜዎች የጧት መርሃ-ግብር አይኖርም፡፡ አንድም ሰው እንዲቀር አይጠበቅም፡፡

ስለ አፍሪካችን በጋራ እንወያይ!!

Source: Via Kedir Daro,

CLG Institutional Transformation Work Coordinator

Update: GOALI – Promotion & Awareness Training Organized By College of Law & Governance Academic Affairs Office has been conducted at Hawassa University, Ethiopia, April 19,2019.


AS-267463768379441@1440779740176_l

GOALI Promotion and Awareness Training Program  

Organized By

College of Law & Governance

See the source image

Capture latest T

Capture0000000000000000000000000000000

Standard Poster 1 Promotion & Awareness Training
 Standard Poster 1
Standard Poster 2 Promotion & Awarnesss Training
Standard Poster 2
A foldable brochure with key information about GOALI A New Research4Life Programme
GOALI Brochure
A foldable brochure with key information about GOALI A New Research4Life Programme 2
GOALI Brochure

 A foldable brochure with key information about GOALI A New Research4Life Programme.

April 19, 2019 Events

Snapshot Photographs were taken during GOALI Promotion & Awareness Training.

Asfaw Genfetao (Dr.),

CLG Post Graduate Coordinator while addressing the audiences & invites CLG Dean to open the training program.

IMG_20190419_030209[1]

Tsegaye Tuke (Assistant Professor), CLG Dean,
While he has made an opening Speech to the audiences about the benefits of  GOALI training & pinpoints that the current trends of teaching and learning process is supported not only by print media (physical books) but also inclusive of Electronic Resources and finally addresses an official opening of the training.     

IMG_20190419_030533[1]
Dr.S.Sivakumar  (Associate  Professor),
at CLG, School of Governance & Development Studies Post Graduate Program Coordinator, while addressing the audiences at the session of the training about why it is important to access Scholarly scientific journals and as whole e-resources. 

PowerPoint Presentation By CLG Head Librarian Main Campus, Hawassa University

IMG20190419090946

IMG20190419091942
Mulugeta WTsadik.,  Librarian while presenting to the audience  

IMG20190419091957

After Powerpoint Presentation CLG Post Graduate Students Practically started to  access GOALI together with CLG Head Librarian at their Reading  Room inside CLG Library

Capture LIB

How Libraries help researchers, practitioners and citizens reach SDG3


IFLA Researtch

#Libraries make major contributions to health#research, support health professionals in their work, and give citizens the information they need to live healthier lives.

As the focus of health policies moves from cure to#prevention and #HealthPromotion, the role of #libraries has never been greater.

For #WorldHealthDay2019, read our new article:http://bit.ly/2WRVG7H

#WorldHealthDay #Lib4Dev #SDG3 #wellbeing

Learning Environments Research: An International Journal-Over 10 million scientific documents at your fingertips


Image may contain: text

Learning Environments Research Volume 22 Number 1 is now available online https://link.springer.com/journal/10984/22/1…

There are 3 types of doctorate degrees


No photo description available.

There are 3 types of doctorate degrees: earned doctorate, rationed out doctorate & stolen doctorate. The first is real, the second is nominal & the third is criminal. That is why z 1st is dubbed true doctorate, z 2nd is touted honorary doctorate & z 3rd is called pop-up doctorate. The 1st is thus nurtured in mind, z 2nd is grabbed from air n the 3rd mushroomed from nowhere. It follows that z 1st is predicated on the study, z 2nd on Maundy n z 3rd on parody. In fine, z 1st is based on verity, z 2nd on vanity n z 3rd on vacuity.
Borrowing Freedom chapter 27, page305

There is a significant increase in human libraries in the US!!


human libraries 22.jpg

%d bloggers like this: