COMMENTARY: Making #technology work for #democracy – what gives? BY: Raul Cordenillo PUBLISHED: 27/09/2017 | GLOBAL -College of Law & Governance Studies Library Blog


technology-792175_1920 

Advances in technology, particularly information communications technologies (ICTs), have arguably helped to improve the way we do things, if not revolutionised our lives. Increasingly, our computers, tablets, smartphones and other similar gadgets have become indispensable in our day-to-day routines.

ICTs allow access to networked and comprehensive information, and the capability to process and compute this information in contexts that are relevant to our day-to-day chores, habits and even basic needs. We can look up apartments available on the market; what clothes are in fashion and on sale; how much is the ideal budget for a family of four; and where can you buy a reasonably priced meal.

At the same time, ICTs brings with them a corresponding set of challenges and vulnerabilities. Tech can be buggy and cannot address all our needs without further enhancement or (re)development, thus, not fulfilling what they ought to do. The networked information that we access can be hacked and used for manipulation or other illegal means without the appropriate cybersecurity measures in place. While they do have their uses, they should be handled with prudence.

It is these same advantages and disadvantages that ICTs bring to democracy, making it easy for citizens and the electorate at large to connect with their candidates and politicians in deciding the direction of the country. These days, with a push of a button, it is entirely possible for you, me or any citizen to access online the profiles of candidates for an election. You can interact with your candidate of choice through your mobile phone via SMS or through social media channels like Twitter. It is also possible to vote for them electronically. In the same manner, it is entirely possible for politicians to be in touch with their constituency through email or even an application on a smart phone. It is even possible for the politician to give a blow-by-blow account how her day was in parliament and how she lobbied for the rights of minorities in her district.

On the other hand, technology used in a democracy can be abused. Private information and even election results can be hacked to unduly influence electoral outcomes. Voting machines can facilitate voting, as well as canvassing but security measures have to be put in place to safeguard their integrity. If this is not ensured, rather than easing the disconnect between citizens and politicians and ultimately building confidence in a functioning democracy, ICTs can be used to foment doubt and mistrust in democratic institutions and processes. 

International IDEA is well aware of what ICTs bring and the risks that accompany them. A personal account of these views is given by the Secretary-General of International IDEA in his interview, where he also talks about the programming priorities of International IDEA in this field.

In this 2017 third quarter newsletter of International IDEA, we present articles that look at how technology can help democracies function better and, at the same time, highlight challenges that could arise. In Election technology: precondition for transparent elections or pretext for questioning electoral integrity?, we look closely at the use of ICTs in elections and the prospects for their use in the future, including what safeguards should be in place. We look deeper into this issue in the case of Europe (In Europe’s upcoming elections, cyber security is the show to watch) and in the case of Africa, particularly Kenya (Kenya: the potential and limitations of electoral technology). While it can be said that the two continents are at different stage of democratic transition and consolidation, there are common technology challenges that have similar fundamental solutions, particularly that of trust in the integrity of the ICT systems themselves.

In embracing the potentials of ICTs, International IDEA has built three systems to allow for better oversight of electoral and democratic practices. In The role of digital technologies in identifying and avoiding risks, we stress the importance of risk management in the conduct of elections and put forward how International IDEA’s Electoral Risk Management Tool help Elections Management Bodies mitigate violence in elections. In Fighting political corruption and organised crime with early warning and graphic information systems, we present how Geographic Information System (GIS) technology can be used to map out threats of political corruption and thereby, facilitate the identification of measures to mitigate them. Finally, in How technology can make party and candidate financial data more transparent, we present the use of an integrated online and disclosure system to oversee the use of money in politics. Democracies can use these tools, which are public goods, to rectify or improve their policies. As to whether they will be effective, depends on the context, as well as the implementation.

As we incorporate ICTs in our lives more and more – some faster than others – we become more aware of the safeguards that we need to put in place to make them work for us. All of these risks may make us think twice before utilising them. One thing for sure though, technology is here to stay and it is advancing rapidly. It is no longer just a matter of joining the bandwagon, it is a reality that we are confronted with. The challenge therefore is for democracies to make technology work for them, depending on their respective contexts and needs, and with the appropriate safeguards and security measures.

Advertisement

….ያልተዘመረለት አባ ጅግሳ(አብዲሳ አጋ) ………VS ኢትዮጵያዊነት………………..,


ለአብዲሳ አጋ ያልሆነችው ኢትዮጵያ ለማን ልትሆን ነው??? ….ያልተዘመረለት አባ ጅግሳ(አብዲሳ አጋ) ………VS ኢትዮጵያዊነት………………..(በጉማ ኦሮሚቲቻ)


(በዚህ ታሪክ የአብዲሳን ጀብዱ መተረክ አይደለም ያሻኝ)
.
አብዲሳ አጋ እምዬ ብሎ ካለላት ኢትዮጵያ ምን ነበር ያተረፈው? እስቲ በጥቂቱ እንየው፡፡
.
በኢጣልያ ተራሮች ላይ የተለያዩ ሀገር አርበኞችን አሰባስቦ ለ4 አመት ያህል ፋሽስቶችን አይቀጡ ቅጣት ሲቀጣ፣ስሙ ከመግነኑ አንጻር የኢጣልያ ጎረምሳዎች ፊታቸውን ጥቁር ቀለም እየተቀቡ እና መሳሪያ እየያዙ ጨለማ ለብሰው በየ ቤቱ እየገቡ” እኔ ሜጀር(ሻለቃ) አብዲሳ ነኝ”በማለት ዘረፋ ያካሂዱ ነበር፡፡ በመጨረሻም የያዛትን ሬጅመንት አሰልፎ በድል ግርማ ሮም ሲገባ የኢትዮጵያን ባንዲራ ሰቅሎ ነበር፡፡ ቀጥሎም ዜግነቱን ለእንግሊዝ ወይንም ለአሜሪካ መንግስት እንዲያዛውር እና ባለበት የሻለቃ(ሜጀር)ማእረግ በሰራዊቱ ውስጥ እንዲቀጥል ሲጠየቅ”እንቢኝ “በማለቱ እንግሊዞች ከኢጣልያ ሹማምንት በመሻረክ “በአንኮና አውራጃ በሳንባሪኖ ወረዳ ላይ 32 ባላባቶችን ገድለሀል” ተብሎ 32 አመት ተፈረደበት፡፡


በአንድ የእንግሊዝ ፊልድ ማርሻል ማእረግ ባለው ሰው አማካይነት ይግባኝ ተጠይቆ ወደ ገንዘብ እነዲቀየርለት $18,000 ሲበየንበት በእንግሊዝ ዋስትና $7,000 ሀገሩ ገብቶ በየወሩ እንዲከፍል ተበየነበት፡፡ይህም የሆነው” አንቢኝ ለኢትዮጵያዊነት”ማለቱ ነው፡፡
.
ቁም ነገሩ ቀጣዩ ነው(ኢትዮጵያስ ለዚህ ጉምቱ ጀግና ምንነበር ያበረከተችለት እስቲ በጥቂቱ እንየው፡፡)
.
1,ግርማዊው ንጉሰ ነገስት ያን በኢጣልያ ምድር ላይ ነግሶ የነበረ ደቦል አምበሳ በገነት ጦር ትምህርት ቤት እንደ አዲስ ወታደር የጦር ታክቲክ እንዲማር ልከውት ፀጉሩን ተላጭቶ ከምልምል ወታደሮች(አዲስ ወታደሮቸች) ጋር እንዲሰለጥን አደረጉት፡፡
.
.በወቅቱ ንጉሰ ነገስቱ ወደ ሀገር ቤት ከተመለሱ ቦሀላ የኢትዮጵያ ወታደሮችን እያሰለጠኑ የነበሩት የእንግሊዝ መኮንኖች ነበሩ፡፡የአብዲሳ አጋን ታሪክ ልቅም አድርገው የሚያዉቁ ብቻ ሳይሆን በኢጣልያ በረሀዎች የተለያዩ ሀገራትን የነጻነት ተዋጊዎች ሲመራ እና ሲያዛቸው የነበረውን፣ የሰራቸውን ጀብዱዎችም ጭምር የሚያወቁት ያ…ሜጀር ማእረግ የተሰጠው ሰው ዛሬ ከምልምል ወታደሮች ጋር ጸጉሩን ተላጭቶ ተሰልፎ ቢመለከቱ ከሀዘናቸው የተነሳ ሜጀር ካዴት (ምልምሉ ሻለቃ)እያሉ ነበር እሚጠሩት፡፡
.
2,አብዲሳ ስልጠና ላይ እያለ የእንግሊዝ መንግስት የከፈለለትን ገንዘብ እንዲመልስላቸው በህግ ሲጠይቁት የወለዳቸው 2ልጆቹ እና መላው ቤተሰቡ በችግር አየተሰቃየ ይከፍል ስለነበር “ለምን ተፈጠርኩ” እስከማለት ደርሶ ነበር፡፡
.
3,ከማሰልጠኛው በምክትል መቶ አለቃ ማእረግ ተመርቆ ሲወጣ ከነበሩት 154 ሰልጣኞች 6ኛ ደረጃ ሁኖ የተመረቀ ቢሆንም ከእርሱ ጋር ተመርቀው የወጡት መኮንኖች ከ1939-53 አ.ም ባሉት አመታት የሻለቃ ማእረግ ላይ ሲደርሱ የኦሮሞው ልጅ አብዲሳ አጋ ለ14 አመታት በመቶ አለቃ ማእረግ ታግዶ ነበር የኖረው፡፡(ምናልባትም በዚህች ሀገር ታሪክ ይህን ያህል አመት ማእረግ የተነፈገ ይኖራል ብየ አልገምትም)
.
በኢጣሊያ በረሀዎች ነግሶ ለነበረው አባ ጅግሳ፣በዘመነ አጼውም ከኦጋዴን ክልል እንዳይወጣ የተበየነበት ሚመስለው ምስኪኑ ሰው ኢትዮጵያዊነቱ የከፈለችው ዋጋ ይሄ ነበር፡፡ የስራ ድልድል ላይ ጭምር ወደ 3ኛ ክፍለጦር እስታፍነት ቢላክም አብዲሳ የሚለው ስም ብቻ ለአፄያውያን አይመችም እና ወደ ኦጋዴን በረሀው ተመልሶ ተልኳል፡፡
.
1956 ኦጋዴን ቶጎ ውጫሌ ላይ የሶማሊ ተስፋፊ ወታደሮች በሙሉ ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቀ እና በሜካናይዝድ የሚታገዝ ብርጌድ ጦር ወረራውን ሲከፍት በቦታው ላይ የነበረውን የኢትዮጵያ ሰራዊት የሚመራው አብዲሳ አጋ በቁጥር ከ300 የማያልፉ(አንድ ሻለቃ የማይሞላ ጦር) ወታደሮችን እና አሮጌ ጠመንጃዎችን በመያዝ ነበር ወደ መከላከል የገባው፡፡
.
ከ5-11ባለው ሰአት ውስጥ እልህ አስጨራሽ ውግያ ከተደረገ የሶማሌውን ሙሉ ብርጌድ ድል አድርጎ ከሙት የተረፈውን ከ900 በላይ የጠላት ሀይል(አንድ ሙሉ ሻለቃ) ሲማርክ የሸሹት አንዳችም መሳሪያ ይዘው አላመለጡም፡፡
.
ከተማረኩት መሳሪያዎች ውስጥ መድፎች፣ የአይሮፕላን ማውረጃ፣ Ptr እና BRDM ታንኮች፣የታንክ መስበሪያ ….. .እያልን መቁጠር ብንጀምር መጨረሻው ይረዝማል፡፡ አብዲሳ ግን በኦጋዴን በረሀ ከጠላቱ እየተናነቀ የእንግሊዝ መንግስት ከእስር እንዲለቀቅ የከፈለለትን ገንዘብ የህጻናት ልጆቹን ጉሮሮ አስርቦ እየከፈለ ቢጨርስም ኢትዮጵያ ግን ለአብዲሳም ሆነ ለሌሎች ብዙ አብዲሳዎች ዛሬም ያልከፈለችው ብዙ እዳ አለባት፡፡
.
ግርም ከሚሉኝ ነገሮች ውስጥ ደግሞ በአብዲሳ ዙርያ የተጻፉት ሁሉም ጽሁፎች የሌተና ኮሎኔል ማእረግ በንጉሱ እንደተሰጠው ነው የዘገቡት፡፡በጣም አሳፋሪ እና ከእውነት የራቀ ጉዳይ ሲሆን አብዲሳ ከሞተ ቦሀላ ነበር ደርግ ይሄ መሆን እንደሌለበት በማለት የኮሎኔል ማእረግ የሰጠው፡፡
.
አንድ ልቤን የነካኝ የዛሬ አመት የሶማሊ ክልል የኦሮሞ ተወላጆችን ሲያፈናቅል ለነዛ ለተፈናቀሉት ወገኖች የደረሱለት የራሱ ወገኖች ብቻ ነበሩ፡፡
.
አብዲሳ አጋ በምትለው ትንሽየ መጽሀፉ ላይም ” እኔን ከእዳ ለማውጣት አለንንልህ ያሉኝ ..” በማለት የዘረዘራቸውን ስሞች መልከት አደረኩ
.
ብላታ dheሬሳ አመንቴ
,ተሊላ ኢብሳ
,ይልማ dheሬሳ
,ደስታ ሮሮ,
ሳራ አያና,
ለሚ ቢርቢርሳ
,dheሬሳ ዳንኬ,
ኦላና ናትናኤል,
የሺእመቤት dheሬሳ…..እያለ ይቀጥላል፡፡
.
.
ለአብዲሳ ያልሆንሽ ኢትዮጵያ 👎

የአብዲሳ አጋ ¬አስገራሚ ታሪክ – ያልተዘመረለት የኢትዮጵያ ጀግና !! ( በስሜነህ ጌታነህ)

12565539_10154030230809587_3444113549569280299_nአብዲሳ አጋ በ1928 ዓ/ም የጣልያን ወረራ ወቅት ተማርኮ ወደ ጣልያን ከተወሰደ በኋላ ብርድ ልብሱን ቀዳዶ በመቀጣጠል በመስኮት አምልጦ በርካታ ጀግንነቶችን የፈጸመ የኢትዮጵያ ወታደር ነው። ኮሎኔል አብዲሳ አጋ የተወለደው በ1912 ዓ.ም ፣ ወለጋ ነበር።

በ12 ዓመቱ አባቱ በንዴት ወንድማቸውን በመግደላቸው ሲታሰሩ አብዲሳ አባቱን ለማስፈታት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ቢያደርግም ሳይሳካ በሞት ተቀጥተዋል። በኋላም በ14 ዓመቱ የኢትዮጵያን ጦር በመቀላቀል ሀገሩን ማገልገሉን ሀ ብሎ ጀመረ። አብዲሳ ጦሩን ከተቀላቀለ ከሁለት አመት በኋላ የአድዋን ሽንፈት ለመበቀል የዛተው ፋሺስት ሙሶሎኒ በድጋሚ ኢትዮጵያን ሲወር ሀገሩን ለመከላከል በ16 ዓመቱ ወራሪውን ጦር መዋጋት ጀመረ።

ውጊያ ላይ ባጋጠመው የመቁሰል አደጋ ህክምና ላይ ከቆየ በኋላ አዲስ አበባ ውስጥ ፒያሳ አካባቢ በሚገኝ ቤት በቁም እስር ላይ ነበር። በኋላ ጣልያን ኢትዮጲያን እንዲያስተዳድር በሾመችው ግራዚያኒ ላይ የመግደል ሙከራ ከተደረገ በኋላ አብዲሳ አጋ እና ሌሎች 37 የሚሆኑ የቁም እስረኞች ተጠርጣሪ ተብለው በከባድ ስቃይ እስር ቤት ከቆዩ በኋላ በወቅቱ የጣልያን ግዛት በነበረችው በሶማሊያ በኩል ወደ ጣልያን ተወስዶ በሲሲሊ ደሴት በሚገኝ እስር ቤት እስረኛ ተደረገ።

አልሸነፍ ባይነት መለያው የሆነው አብዲሳ ሁሊዮ ከተባለ ዩጎዝላቪያዊ የጦር እስረኛ ጋር በመተባበር ከባድ ጥበቃ ከሚደረግበት እስር ቤት ለማምለጥ ማሰላሰል ጀመረ። ተሳክቶለት ቢያመልጥ እንግዳ አገር እንደሚጠብቀው ቢያውቅም በነጻነቱ የማይደራደረው አብዲሳ የተሰጠውን የብርድ-ልብስ ቀዳዶ በመቀጣጠል በመስኮት በኩል አመለጠ።

ከዛ በኋላ ግን ሽሽት አልነበረም የጀመረው አብዲሳ። ከጥቂት ቀናት በኋላ በማታ ወደ እስር ቤቱ በመመለስ ጠባቂዎቹ ላይ ጥቃት በመፈጸም እስረኞቹን በመሉ ነጻ ማውጣት ችሎ ነበር። ያመለጡት እስረኞች ከእስር ቤቱ ጠባቂዎች በወሰዱት መሳሪያ በመታገዝ የአማጽያን ጦር ያደራጁ ሲሆን ጦሩን እንዲመራም የመረጡት ጀግናውን አብዲሳን ነበር። ከዛም የተለያዩ የጣልያን ወታደራዊ ሠፈራዎች ላይ ጥቃት በመፈጸም ወራሪዎቹ ጣልያኖች ኢትዮጵያ ውስጥ ከነበረው የአርበኛ እንቅስቃሴ ያልተናነሰ ጥቃት በሀገራቸው ያጋጥማቸው ጀመር።

በአብዲሳ ጦር እጅግ የተረበሹት ጣልያኖችም በርካታ ስጦታዎችን ቃል በመግባት ውጊያውን እንዲያቆም እና የነሱን ጦር እንዲቀላቀል ለምነውት ነበር። አብዲሳ ግን ከፋሺስት ሥርዓት ጎን እንደማይቆም በማስረገጥ ጥያቄውን ውድቅ አደርጎ ጣልያኖችን በሀገራቸው ማስጨነቅ ቀጠለ።

በወቅቱ እየተጋጋለ የመጣው የጀርመን ናዚ ሥርዓት ሁለተኛው የዓለም ጦርነትን ሲጀምር ፋሺስት ሙሶሎኒ ከጀርመኖች ጋር ሲያብር እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና አሜሪካን ጨምሮ በርካታ የምዕራብ አገሮች የሕብረት ጦር መስርተው የሙሶሎኒን ጦር መውጋት ጀምረው ነበር።

በወቅቱ ይህ የሕብረት ጦር የአብዲሳን ዝና በመስማታቸው ጣልያንን ለማዳከም ለአብዲሳ ጦር የቁሳቁስ ድጋፎች ማድረግ ጀመሩ። በድጋፉ በመጠናከር ፋሺስቱን ሰራዊት ማርበድበድ የቀጠለው አብዲሳ የጣልያን ጦር ተሸንፎ ዋና ከተማዋሮም በአሜሪካን እና እንግሊዝ የሚመራ ጦር እጅ ስር ከወደቀች በኋላ የሚመራቸውን ከተለያዩ አገር የወጡ ወታደሮች በሙሉ ክንዳቸው ላይ የኢትዮጲያን ባንዲራ እንዲያስሩ በማድረግ የሃገሩን ባንዲራ እያውለበለበ ሮም ከተማ ሲገባ በአለም አቀፉ ህብረት ጦር ትልቅ አቀባበል ተደርጎለት ነበር።

ከዛም በኋላ ከተጨማሪ ወታደሮች ጋር በአለም አቀፉ ህብረት ስር የሚመራ ጦር መሪ በመሆን ጀርመንን ለማሸነፍ በሚደረገው የመጨረሻ ውጊያ ላይ ተሳትፎ ግዳጁን በሚገባ በመወጣት የኢትዮጲያን ባንዲራ ከእጁ ሳይለይ በርካታ የጀርመን ከተሞችን ነጻ ማውጣት ችሎ ነበር። ከጦርነቱ መገባደድ በኋላም የእንግሊዝ፣ የካናዳ እና የአሜሪካ መንግሥታት ጦራቸውን ተቀላቅሎ እንዲቀጥል በርካታ ጥቅማ ጥቅሞችን አቅርበውለት ነበር። አብዲሳ ግን ኢትዮጵያ ምንም ያህል ድሃ ብትሆንም ሕዝቡን እና መንግሥቱን ጥሎ እንደማይሄድ አስረግጦ በመናገር ጥያቄውን ሳይቀበል ቀረ።
ተቀላቀለን የሚለውን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ያልተዋጠላቸው አንዳንድ የሕብረት ጦሩ አባላት ሁለተኛ የዓለም ጦርነት ካበቃ በኋላ በወንጀል ከሰው አብዲሳን እስር ቤት አስገብተውት ነበር። በኋላም እስሩ ወደ ገንዘብ ቅጣት ተቀይሮ ገንዘቡ ተከፍሎ አብዲሳ ለዓመታት ወደተለያት ሀገሩ በክብር ተመለሰ። ከዛም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በክብር ከተቀበሉት በኋላ በጊዜው የመከላከያ ሚኒስቴር ወደነበሩት ራስ አበበ አረጋይ መርተውት ነበር።

ሚኒስቴሩ ውደመሩት ወደ ሆለታ ወታደራዊ ሠፈር የገባው አብዲሳ አነስ ባለ ወታደራዊ ቦታ የተወሰነ ጊዜ ከቆየ በኋላ ለጉብኝት የሚመጡ የውጭ ሀገር የጦር መሪዎች ስለ ዝናው ሲያወሩ የሰሙት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ወደ ቤተ መንግሥታቸው በማምጣት በኮሎኔልነት ማዕረግ የንጉሡ ጠባቂ ሆኖ አድርገው ሾሙት። እስከ ንጉሣዊ ሥርዓቱ መውደቅ ድረስ በቦታው ያገለገለው አብዲሳ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

 
 

ከ ” አልወለድም ” መጽሐፍ ከ ገጽ ፻፵፭ እስከ ፻፵፱ ድረስ የተቀነጨበ ፤ [ ባለቅኔ ገጣሚ እና ደራሲ አቤ ጉበኛ ] — College of Law; Governance & Development Studies Library


”…. በአኹኑ ዘመን ፡ ማንኛውም ሕዝብ ፡ የሚመካው ሥልጡነ ሕዝብ [ democracy ] በሚባለው ፡ ታላቅ የአስተዳደር እምነት እንደኾነ ፡ በኹሉም ዘንድ የታወቀ ነው ። የሥልጡነ ሕዝብ [ democracy ] ትርጉሙ ደግሞ ፡ ነፃ አስተዳደር [ የሕዝብ የበላይነት ] የሚል ፤ መንግሥታዊ አቋም ፡ መኾኑ ይታመናል ። ነገር ግን ፡ ልዩ ልዩ በኾኑ ፡ መንግሥታዊ […]

via ከ ” አልወለድም ” መጽሐፍ ከ ገጽ ፻፵፭ እስከ ፻፵፱ ድረስ የተቀነጨበ ፤ [ ባለቅኔ ገጣሚ እና ደራሲ አቤ ጉበኛ ] — College of Law; Governance & Development Studies Library

ከ ” አልወለድም ” መጽሐፍ ከ ገጽ ፻፵፭ እስከ ፻፵፱ ድረስ የተቀነጨበ ፤ [ ባለቅኔ ገጣሚ እና ደራሲ አቤ ጉበኛ]


abe222222222222222222222”…. በአኹኑ ዘመን ፡ ማንኛውም ሕዝብ ፡ የሚመካው ሥልጡነ ሕዝብ [ democracy ] በሚባለው ፡ ታላቅ የአስተዳደር እምነት እንደኾነ ፡ በኹሉም ዘንድ የታወቀ ነው ።
የሥልጡነ ሕዝብ [ democracy ] ትርጉሙ ደግሞ ፡ ነፃ አስተዳደር [ የሕዝብ የበላይነት ] የሚል ፤ መንግሥታዊ አቋም ፡ መኾኑ ይታመናል ።

ነገር ግን ፡ ልዩ ልዩ በኾኑ ፡ መንግሥታዊ አስተዳደሮች [ political systems] የልዩ ልዩ አህጉር ሕዝቦች ኹሉ ፡ የየራሳቸውን አስተዳደር ብቻ ፡ እውነተኛ ሥልጡነ ሕዝብ [ democracy] እያሉ ይናገራሉ ።
ከዚህም በላይ ፡ ለሌሎች ሕዝቦች ፡ ዋቢዎች [ ምሳሌዎች ነን ] በማለት ፡ በሌላው አገር ሕዝብ ላይ ፡ የነቀፋ ድምጽ ያሰማሉ : ይኹን እንጂ አንድ ሰው ፡ በእውነተኛ መንገድ : ጉዳዩን ተመልክቶ ፡ እውነተኛውን የሥልጡነ ሕዝብ [ የ democracy] ድንጋጌ በሥራ ላይ ያዋለ እንዳለ ፡ ለመረዳት ቢፈልግ ፡ ይኽንን አጣርቶ ለማወቅ ካለመቻሉም በላይ ፡ በየቀበሌው የሚነጉደውን : ራስን የማሞገስ እና ሌላውን የመንቀፍ ነጎድጓድ : ዦሮውን አደንቁሮ : መንገዱን እንደሚያሳጣው : ጥርጥር የሌለበት ጉዳይ ነው ።

በአኹኑ ዘመን ውስጥ ሥልጡነ ሕዝብ ነን [ democrat’s] ነን የማይል የለም : በሌሎች አገር ገብተው : የሌሎችን ሀብት እና ርስት ቀምተው : የሚገኙት ተስፋፊዎች [ colonialist’ s] እንኳ ሳይቀሩ ፡ሳያፍሩ ሥልጡነ ሕዝብ ነን ሲሉ ይሰማሉ ።

የሥልጡነ ሕዝብ ሥርዓት [ democracy ] ያለው በየት አገር እንደኾነ : ሊያውቅ የሚችል ግን : ተጠቃሚው ሕዝብ ራሱ ብቻ እንጂ : አንዳንድ የሥነ መንግሥት ሰዎች [ politicians ] የሚያወሩትን ወሬ በመስማት ብቻ ፡ አንድ የውጪ ሕዝብ የአንድን አገር አስተዳደር ሊያውቅ አይችልም ።

የመሪዎች ዲስኩር ብቻ ፡ ለአንድ ሕዝብ ጥቅም እና ታላቅነት በቂ ቢኾን ኖሮ : በመላው ዓለም ውስጥ : በጭካኔው ተመሳሳይ በሌለው ጥብቅ ጭቆና [ dictatorship] ሕዝቡን ያሰቃይ የነበረው ፡ የደቡብ አፍሪቃው የፈረንጆች መንግሥት ጠቅላይ ምሉክ [ prime minister] የደቡብ አፍሪቃ ተወላጆች በሥልጡነ መንግሥት [ በ democracy] መንገድ ነው የሚተዳደሩት በማለት ሁልጊዜ ይጮኽ ነበር ።

ነገር ግን : ማንኛውንም ሕዝብ : በአንድ አገር የሚደረገውን ነገር በሙሉ ለማወቅ ባይችልም : አንዳንድ በግልጽ የሚሠራባቸውን ጭቆናዎች ለማወቅ ስለማይቸግራቸው ፣ የሥልጡነ ሕዝብ [ democracy] ገናና ስም ፡ ገና በስም ብቻ እንዳለ እና በሥራ ላይ እንዳልዋለ : ለማመን የሚያግደው ነገር አይገኝም ።

ለመኾኑ ፡ የሥልጡነ ሕዝብ ሥርዓት በየትኛው አገር ክፍል ይገኛል ? ብለን ብንጠይቅ የሚሰጡንን መልሶች : ከብዙ በጥቂቱ ብንናገር የሚከተሉት ይመስሉኛል ።

የምዕራብ አውሮጳ አገራት ስለራሳቸው ሲናገሩ”’ ፣ የሥልጡነ ሕዝብ ሥርዓት democratic system of government በትክክል የሚሠራው በእኛ አገር ነው ፡ ሕዝባችን የወደደውን ለመምረጥ : የወደደውን ለመጣል መብት አለው ።

እንዲኹም አንድ ሰው : የሚፈልገውን ዓይነት ሥራ ፡ ለመሥራት ፡የመሰለውን አስተያየት ለመግለጽ ፡ የወደደውን እምነት እና ፍልስፍና ለመከተል : በሥራ እና በችሎታ ከታናሽ ደረጃ ተነስቶ :ወደ ታላቅ ደረጃ ለመድረስ : መሰናክል እና ጭቆና : የለበትም : የሚታዘዘው እና የሚተዳደረው በሕግ እንጂ በጉልበት አይደለም “” : ይላሉ

እንደዚሁም የኃብረተሰባዊነት [ communism] ፍልስፍና ተከታይ የኾኑትን አገሮች ስለራሳቸው ሲናገሩ “” የሥልጡነ ሕዝብ [ የ democracy] አላማ “” የሕዝብ ለሕዝብ “” የሚል ምሥጢረ ያለበት ሲኾን : የሕዝብ የኾነውን የአገር ጠቅላላ ሀብት እና ጥቅም : እኩል ተከፋፍለን : የምንተዳደር : ወገኖቻችንን አደህይተን ባለጠጎች [ capitalist] መኾንን የማናውቅ : የማንፈልግ ፡ ለአገራችን እኩልነት የምናስብ : እኩል የምንሠራ : በአገራችን ሀብት እኩል የምንጠቀም : እኩልነት ያለን ሕዝቦች ነን ይላሉ ። “””

እርስ በእርስ ያለውን የመነቃቀፍ ጣጣ ስንመለከትም : ምዕራባዊያን ኃብረተሰባውያኑን [ communist] የኾኑትን ሲተቹ : በጭቆና ሥር ተቀጥቅጠው : በብረት መጋረጃ ተከበው የሚኖሩ : በገዛ ሕይወታቸው የማያዝዙ : ተጨቋኞች የሚበዙባቸው እንደኾኑ ሲናገሩ : ኃብረተሰባውያኑ ደግሞ በበኩላቸው የምዕራብ ሕዝቦችን : በጥቂት ጃውሳ ባለሀብቶች [ capitalists] : የአገራቸው ሀብት ተዘርፎ : ብዙኃኑ በድህነት የሚንገላቱ የበዙበት መኾኑን በመግለጽ : ኹለቱም [ ምዕራባውያኑም ኃብረተሰባውያኑም ] ሥልጡነ ሕዝብን የምንከተለው እኛ ነን እያሉ የየራሳቸውን መንገድ ያሞግሳሉ ።

ከዚኽም በቀር ደግሞ : ተስፋፊ ወራሪዎች [ colonialists ] ደግሞ : ሥልጡነ ሕዝብ ሥርዓትን [ democracy system ] የምንከተለው እኛ ነን እያሉ ሰሚን ኹሉ ያስቃሉ ።

በአጠቃላይ በዓለም የሚገኙ ሕዝቦች ኹሉ : የሥልጡነ ሕዝብ ስም በመላው ዓለም እንደገነነ በየአገሩ የሚነዛውን ወሬ ይሰማሉ : ነገር ግን እውነተኛው ሥልጡነ ሕዝብ [ እውነተኛ democracy] በዚኽ ክፍለ ዓለም ያለው ነው ብለው : ለመፍረድ የሕሊና ሙግት ይገጥማቸዋል ።ይህ የሚኾንበትም ምክንያት : “” እውነተኛው ሥልጡነ ሕዝብ ሥርዓት “” በየት እንዳለ ተለይቶ ሰለማይታወቅ ነው ።

በእውነት ” የሥልጡነ ሕዝብ “” ሥርዓትን የሚከተል ቢኖር እራሱን ሱልጥነ ሕዝብ ነን [ democrat’s] ነን ከማለት ይልቅ
የሰውን ዘር እኩልነት : እንዲኹም ነጻነት እና ወንድማማችነት :ለማክበር የሚያሳየውን ሰላማዊ ሥራ ማስቀደም ነበረበት ።

ሥልጡነ ሕዝብ ለመባል ፡ የሰውን ዘር ማክበር እንጂ : እኔ ሥልጡነ ሕዝብ ሥርዓት እከተላለኹ [ democrat ] ነኝ ፤ ሌሎች ደግሞ በኃይል የሚገዙ ጨቋኞች [ dictators] ናቸው ማለት ብቻ በቂ አይኾንም ።

23658430_1501058886630651_2935919646889583161_n
ባለቅኔ ገጣሚ እና ደራሲ አቤ ጉበኛ 

 
%d bloggers like this: