እውቀትን ማስፋፋት ወይስ ደራሲን መበደል? By ‎Tewodros Shewangizaw – Law & Governance College Library Blog


 

 

Image may contain: text

 

የማንኛውም ሳይንሳዊም ሆነ ኪናዊ ፈጠራ ባለመብቶች ህጉ የማይፈቅድላቸውን መፅሀፍትን በስስ ቅጂ በኢንተርኔት ወይም በሌላ በማንኛውም ኤሌክትሮኒክ መንገድ መልቀቅ እውቀትን ማስፋፋት ወይስ ደራሲውን መበደል?

እውቀትን ለሁሉም በስፋትና በጥራት ማዳረስ ከጥንት ዘመን ጀምሮ የነበረ ሀሳብ እና ሙከራ ነው። ለብዙ ዘመናት ይህንን ሐላፊነት ተሸክመው ይኖሩ የነበሩት ቤተ መፅሀፍት ናቸው። ከጥንታዊው አሌክሳንድሪያ ጀምሮ እስከ ዘመናዊው የኮንግረስ ቤተመፃህፍት ድረስ ይሄንኑ ለማድረግ ሲሞክሩ ኖረዋል።

ከሀያኛው ክፍለዘመን በኋላ የዲጂታል አብዮት ተቀሰቀሰ። መፅሀፍት ለአንባቢዎች የሚደርስበት መንገድም በከፊል ተቀየረ። ቨርቿል ቤተመፅሀፍትም ማንኛውም ሰው የአለም እውቀት ሁሉ ተጠቅሎ በአንድ ቦታ እንዲገኙ አስቻለ። በዚህ ዙሪያ የሚሰሩ ፕሮጀክቶችም ብቅ ብቅ አሉ። ከነዚህም መሀል ፕሮጀክት ጉተንበርግ ፣ ጎግል ቡክስ ፣ ዘ ሚሊዮን ቡክ ፕሮጀክት ፣ ኢንተርኔት አርካይቭ እና ሊብገን ላይብረሪ ይገኙበታል።

እውቀት ለሁሉም ፣ መቼም ፣ የትም ማድረስ የሚለው ሀሳብ ታላቅ ህልም ፣ ቅዱስ ተግባር ነው። አስቡት እስኪ ግዜና ቦታ ሳይገድባችሁ የአለምን እውቀት ሁሉ በመዳፋችሁ ስር ማድረግ መቻል። ትልቁ ጥያቄ በማን ወጪ? የሚለው ነው። ደራሲዎች ሳይፈልጉ/ሳይችሉ ይህንን ሸክም እንዲሸከሙ እየፈረድንባቸው ነው።ቴክኖሎጂው ማንም እንዳሻው ሊጠቀምበት የሚችል ግኡዝ ነው። ደራሲዎች ለአመታት የለፉበትን የስራ ውጤት በሰከንዶች ለሚሊየኖች በነፃ እያዳረሰ የደራሲዎችን ልፋት በከንቱ እያስቀረው ያለ ማመዛዘን የተሳነው የሰው ልጅ ህሊና ነው። ስለዚህ አንድ መፅሀፍ ታትሞ ለደራሲው ተገቢውን ጥቅም ሰጥቶ እንደየሀገሩ ህግ መሰረት የሕዝብ ሐብት እስኪሆን ደረስ በህገወጥ መንገድ አግኝቶ መጠቀም ከሌብነት በምንም አይተናነስም። የጫነም ፣ ያወረደም የህሊና እዳ አለበት።

Advertisement
%d bloggers like this: