የሰዉ ልጆች እይታ ወይም ዓይን ሁልጊዜ ከተለመዱ ክስተቶች ወይም ነገሮች ይልቅ አዳዲስ እና ወጣ ባሉ ያልተለመዱ ከስተቶቸ ላይ የማረፍ ፍጥነቱ ከፍተኛ ነዉ።

በዚሁ ላይ በመንተራስ በሀዋሳ ከተማ መዝናኛ ቦታዎችና ጎዳናዎች ላይ በጎ ያልሆኑ እና በጎ የሆኑ መስለዉ ከታዩኝ እይታዎቼ መካከል ከበዙዎቹ በጥቂቱ በሁለት ነገሮች ዙሪያ እይታዎቼን በመጠኑ ላካፍላቸሁ ወደደኩ እነርሱም ፤
- በእንግሊዘኛ ቋንቋ የፊደላት አጻጻፍ ግድፈት የሚታይባቸዉ የማስታወቂያ ጽሁፎች በጥሩ የጽሁፍ አጣጣል ተከሽነዉ በየአደባባዩና ጎዳናዎች ላይ ለሕዝብ እይታ የሚቀርቡበት ምክንያት ሆን ተብሎ በማወቅ ወይስ ባለማወቅ? ይህ ዲርጊት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሀዋሳ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም የኢትዮጵያ ከተሞች ሁሉ መታየት ከጀመረ ዉሎ አድሮ ሰነባብቷል ።ለማንኛዉም ጉዳዩ ……ን ጥያቄ ዉስጥ የሚያስገባ መሆኑ ከሁላችንም የተሰወረ አይደለም።

2. የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ወጣቶች የዕለት ኑሮአቸዉን ለመደጎም ሲጣጣሩ ማየት ያስደስታል። በእዉነቱ ሊበረታቱ ይገባል።

በምን መልኩ߹ ምንም እንኳ የአንዳንዶቹ መጻሕፍት ዋጋ ዉድ ቢሆንም ቢያንስ ከእነዚህ ወጣቶች አቅም በፈቀደ መጠን የሚሸጡትን መጻሕፍት ገዝቶ ማንበብና ሌሎችም ገዝተዉ እንዲያነቡ ማስተዋወቅ ወጣቶቹን ከመጥቀም ባሻገር የንባብ ልምድ እና ባሕልን ከማዳበር አንጻር መጠነኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረዉ ለሁላችንም ግልጽ ነዉ።
የእኛዎቹ መጻሕፍት አዟሪዎች ሊበረታቱ ይገባል
ይህ ከታች የምታዩት ምስል በ1930ዎቹ በእንግሊዝ ለንደን ከተማ ተንቀሳቃሽ ቤተመፅሐፍት በነበረበት ጊዜ የተነሳ ፎቶ ነው፡፡”በቃ ይናገራል ፎቶ ሳይጨምር ሳይቀንስ” ማለት ይህ ነው፡፡


በሙሉጌታ ወ/ጻ