ንባብ ለምን . . . ንባብ ለምኔ? በታደለ ለገሰ (ከሀዋሳ) — Law & Governance College Library


ንባብ በግለሰብም ሆነ በማሕበረሰብ ሕይወት ዉስጥ ትልቅ ቦታ ሊኖረዉ የሚገባ መሰረታዊ ክህሎት ነዉ። የሰዉ ልጅ ስብዕናዉን የሚቀርፅበት እና የማንነቱና የምንነቱ መገለጫ የሁኑትን በህላዊ ትረካዊ እና ሥነ ጥበባዊ ቅርሶቹና ዕሰቶቹ እንዳይጠፉ ለቀጣዩ ትዉልድ ጠብቆ የሚያቆይበት የሚያስተላልፍበትም ዓይነ ተኘ መሳሪያም ነዉ። ማንብብ የማይችል ግለሰብም ሆነ ማህብረሰብ አካባቢዉን የማወቅና የመግለጽ ብቃቱ በመስማትና በማየት ላይ ብቻ […]

via ንባብ ለምን . . . ንባብ ለምኔ? በታደለ ለገሰ (ከሀዋሳ) — Law & Governance College Library

Advertisement

ንባብ ለምን . . . ንባብ ለምኔ? በታደለ ለገሰ (ከሀዋሳ)


       ንባብ በግለሰብም ሆነ በማሕበረሰብ  ሕይወት ዉስጥ ትልቅ ቦታ ሊኖረዉ የሚገባ መሰረታዊ ክህሎት ነዉ። የሰዉ ልጅ ስብዕናዉን  የሚቀርፅበት እና  የማንነቱና የምንነቱ መገለጫ  የሁኑትን በህላዊ  ትረካዊ እና ሥነ ጥበባዊ ቅርሶቹና ዕሰቶቹ እንዳይጠፉ  ለቀጣዩ ትዉልድ ጠብቆ የሚያቆይበት የሚያስተላልፍበትም ዓይነ ተኘ መሳሪያም  ነዉ።  ማንብብ የማይችል ግለሰብም ሆነ ማህብረሰብ  አካባቢዉን የማወቅና  የመግለጽ ብቃቱ በመስማትና በማየት ላይ ብቻ የተመሠረተ በመሆኑ  ለማንኛዉም የፈጠራናም ሆነ የእዉነታ ጽሁፍ ዕዉቆቶች እንግዳና ባይትዋር ይሆናል።  ስለ ሕይወትና ስለ ተፈጥሮ … ስለ ከባቢያዊና ዓለም  አቀፍ ኩነቶች ያለዉ ግንዛቤ ዉስንና  የተዛባ ይሆናል ።

     የዳበረ የንብብ ልምድ በቋንቋ የመጠቀም ብቃታችንን ከማሳደጉም በላይ ሂሳዊ አስተሳሰብና ማዛናዊ የሆነ ግንዛቤ እንዲኖረን ያደርጋል። የዳበረ የንባብ ልምድ የሌሎችንም ሀሳብና ስሜት በቀላሉ ለመረዳትና  ከማንኛዉም አቅጣጫ ለሚሰነዘሩ አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ አስተያየቶች ምክንያታዊና በሳል߹ ቁጥብና ገላጭ በሆኑ ቃላት ፈጣን ምላሽን መስጠት የሚያስችል ብቃትና ክህሎት ያስታጥቀናል።  ንባብ በአንድ ጉዳይ ላይ ትኩረትን ሰብሰቦ የማሰብና የማሰላሰል ጠቃሚ ልምድና ብቃትን ያጎናጽፈናል ታላላቅ ሳይንቲስቶችና ኢንጂነሮች߹   ሰመ ጥር ደራሲያን߹  ጸሐፌ ተዉኔቶች߹  ሰዓሊያን ߹ ገጣሚዎች እና ባለቅኔዎች ወዘተ የሚፈጠሩበት በዳበረ የንባብ ምንባዊ ዓለም ዉስጥ ነዉ። ምንባዊ ወደ ሆነዉ የንባብ ዓለም ዉስጥ ስንገባ ߹ ግዑዙንና ገሀዱን ዓለም ጥለን߹  በታላቅ ፀጥታና ተመስጦ߹  በስፍራና በጊዜ በመይለካ ና በማይወሰን ߹ ጥልቅነቀ የትየለሌ ወደሆነዉ የዕዉቀትና የጥበብ ዓለም ውስጥ እንገባለን ።

      ከዚህ ምናባዊ የንባብ ዓለም ከምናገኘዉ ድንቅ ትኩረትና የተመስጦ ተሞክሮ ߹ በህይወት ጉዞአችን ዉስጥ ሊያጋጥሙን የሚችሉትን ተግዳሮቶችና ፈተናዎች እነዴት መወጣት እንደምንችል እንማራለን።  ዉስብስብ ችግሮችን  የመፍታት ብቃታችንን እናሳድጋለን። ከንባብ ጋር የሚኖረን ጥብቅ ትስስርና ቁርኝት ለሕይወትና ለተፈጥሮ የምነሰጠዉን  ዋጋና ክብር በእጅጉ ይጨምራሉ።  የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት߹ የዳበረ የንባብ ልምድ ያላቸዉ ግለሰቦች߹  የንባብ ልምድ ከሌላቸዉ ግለሰቦች ይልቅ በሦስት እጥፍ የተፈጥሮ እንክብካቤና የበጎ አድራጎት (ሰባአዊ) ድርጅቶች በሚያደርጓቸዉ እንቅስቃሴዎች ዉስጥ ንቁ ተሳታፊዎች ናቸዉ። ይህ ዓይንቱ ንቁ ተሳትፎ አንባቢያንን በጎ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ከማድርጉም ባይ ለግለሰቦችም ሆነ  ማህበረሰቦች ደህንነት በእጅጉ ተቆርቋሪና ኃላፊነት የሚሰማቸዉ ዜጎች እንዲሆኑ አስችሏችዋል። ንባብ ጭንቀትንና ዉጥረትን በማስወገድ ዘና እንድንል ይረዳናል። በንባብ አዉድ ዙሪያ የተካሄዱ የተለያዩ ጥናቶች ጭንቀትን እንደሚቀንስ ደርሰዉበታል። ለስድስት ደቂቃ ፀጥ ብሎ ማንበብ የልብ ምትን  ያረጋጋል ።  የተኮማተሩ የአካሎቻንን ጡንቻዎች ዘና እንደሉ ያደርጋል።

     ንባብ እራሳችንን ለማሰደስትና ለማዝናናት ያስችለናል። በደራሲያን በጸሐፌ ተዉኔቶችና በገጣሚያን የፈጠራ ሥራዎች ዉስጥ የምንገኛቸዉ ገጸ ባህሪያት በተሳሉበት ምናባዊ ዓለም ዉስጥ የሚያደርጉት ልብ አንጠልጣይ እንቅስቃሴ߹ ለአእምሮአችን  ምናባዊ ፍሰሀን ያጎናጽፈዋል ። ንባብ ከማዝናናትም ባሻገር የሕይወት ክህሎታችንን በማሳደግ ያስደንቀናል ።

      ንባብ ከፊልምና ከቴሌቨዥን ከምናገኘዉ መረጃዎች ይልቅ የአስተሳሰባችንን አድማስ የማስፋትና ምናባዊ እይታችንን የማሳደግ ብቃት እንዳለዉ የተለያዩ መረጃዎች ያመላክታሉ።  የሚያሳዝነዉ ግን አስቂኝ ፊልሞችና የቴሌቨዥን ፕሮግራሞች ከሌሎች ነገሮች ጋር ተዳምረዉ ንባብ በብዙ ሰዎች ሕይወት ዉስጥ ቦታ እንዲነፈገዉ ምክንያት ሆነዋል።  አንድ ሰዉ አዘዉትሮ ቴሌቨዥን የሚመለከትና እምብዛም የማያነብ ከሆነ߹ የማንበብ ችሎታዉ ብቻ ሳይሆን በትክክል የማሰብና የማመዛዘን እንዲሁም ሀሳቡን አቀነባብሮ የመግለጽ ችሎታዉ ሊቀንስ እንደሚችል በጥናት ተደርሶበታል።  ማር ዎልፍ የተባሉ ጸሐፊ߹  “የአንባቢ አእምሮ ታሪክና ሳይንስ” (The Story & Science of the Reading Brain) በተሰኘ መጽሐፋቸዉ እንዲህ ብለዋል።  “ሲታነብ ለማሰብ ወይም አንድን ነገር ለማሰላሰል ጊዜ ይኖርሃል።  የማሰቢያ አፍታን  ታገኛለህ ።  በሌላ በኩል ፊልም ወይም ቴሌቭዥን ስትመለከት አልያም ሬዲዮ ወይም ቴፕ ስታዳምጥ ወደ ዉስጥህ የማየትና የማሰብ ጊዜን አታገኝም ። ይህ የንባብ ሂደት ዉስጥ የምታገኘዉ አፍት  የማሰብና የማስታወስ ችሎታህን በእጅጉ ያዳብረዋል። “

         ለማጠቃለል  በተፈጥሮ ሳይንስ߹ በማህበረሰብ  ሳይንስ በፍልስፍና߹ ታሪክ߹ በስነ-ጥበብና በሌሎችም ዘርፎች ያለን ዕዉቀት ሊሰፋና ሊያድግ የሚችለዉ በንባብ ነዉ። ንባብ በዕዉቀትና በጥበብ የተካነ߹ ማንነቱንና ምንነቱን የተረዳ߹ ሁሉን ጠያቂና ተመራማሪ߹ በየተሰማራበት የሙያ መስክ ስኬታመ የሆነና እራሱንም ሆነ ሀገርን የሚጠቅምና የሚያሳድግ߹ ደስተኛና የተረጋጋ  ሕይወት ያለዉ ዜጋ እንዲኖረን ያስችለናል። ከታሪክ ሂደት መረዳት እንደሚንችለዉ߹ መጪዎችን ዘመንና ትዉልድ መቆጣጠርና መምራት የሚችሉት በፈርጣማ ጡንቻዎቻቸዉ የሚያስቡ አምባገነኖች ሳይሆኑ  በዳበረ የንባብ ልምድ የበለፀገ አእምሮና ብሩህ አስተሳሰብ ያላቸዉ አንባቢ ማህበረሰቦች ስለመሆናቸዉ አንዳችም ጥርጥር ሆነ ብዥታ ሊኖረን አይገባም።  እናም እናንብብ! አሁንም እናንብብ! እናንብብ! ግን እንዴትና  ደግሞም ለምን?

      ሀሮልድ ብሩም የተባሉ ጸሐፊ “ለምንና እንዴት ማንበብ አለብን?” (How to read and why) በተሰኘዉ መጽሐፋቸዉ߹ እንዴት ማንበብ እንዳለብን ሲያብራሩ ߹ “ስታነብ ለምታነበዉ  ጽሁፍ ልብህ ክፍት ይሁን ߹ የምታነባቸዉን ፊደላት በፍቅር በእርጋታናበጽሞና በዉስጠኛዉ ጆሮህ እያዳመጥክ በጸጥታ አንብብ። ስናነብ ትክክለኛ የልብ ዝንባሌ ሊኖረን ይገባል። ስናነብ ትክክለኛ የልብ ዝንባሌ ከሌለን ወደ ተሳሳተ ድምዳሜ ልንደርስ እንችላለን።ስናነብ እራሳችንን በባለታሪኮቹ ዉስጥ አድርገን ስሜታቸዉን ለመጋራት እንችል ዘንድ በፍቅርና በወዳጅነት መንፈስ ሆነን እናንብብ።” ጸሐፊዉ ለምን ማንበብ እንዳለብን ሲገልጹም߹  የምናነበዉ ምክንያታዊነታችንን ለማሳደግ እንዲያም ሲል አጠቃላዩን ንቃተ-ህሊናችንን ለማዳበር እናም ደግሞ ከህመማችን ለመፈወስ  መሆን አለበት። ማንነታችንን ካለገኘንና እራሳችንን መሆን ካልቻልን߹ለሌላዉ ምን መሆን እንችላለን? ሲሉም ይጠይቃሉ። ምክራቸዉን እንስማ ߹ ጥያቄያቸዉንም ለመመለስ እንዘጋጅ።

       አመለካከት ማንኛዉንም ድርጊት ለማድረግም ሆነ ላለማድረግ የመገፋፋት ሀይል አለዉ። ለአንድ ድርጊት የሚኖረን አዎንታዊ አመለካከት߹   ለድርጊት የሚያነሳሳን ሲሆን አሉታዊ-አመለካከት ደግሞ ያንን ድርጊት በንቃት እንዳናከናዉን  ተነሳሽነታችንን  እንደሚቀነስዉ በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች ያመላክታሉ። በዚህ ሀሳብ መነሻነትም-  ለንብብ ያለንን ተነሳሽነት  የሚወስነዉ  ለንባብ ባለን አዎንታዊ ወይም አሉታዊ  አመለካከት ላይ የተመሰረተ ነዉ ማለት ይቻላል።

       በዘርፉ የተካሄዱ የተለያዩ ጥናቶች ߹  በልጆች የማንበብ ልምድ ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ከመፍጠር አንጻር ግንባር ቀደሙን ሚና የሚጫወቱ ወላጆች ና መምህራን መሆናቸዉን ይገልጻሉ።ወላጆች የልጆቻቸዉን የንባብ ልምድ ከማዳበር አንጻር ሁለት ወሳኝ ሚናዎችን ይጫወታሉ።  እንድም “ድርጊት ከቡሁ ቃላት ይልቅ ይናገራል” (action speaks louder than words) እንዲሉ የዳበረ የንባብ ልምድ ያላቸዉ ወላጆች መኖሪያ߹    በተለያዩ ጋዜጦች߹   መጽሔቶችና መጽሐፍት የተሞላ እንደመሆኑ߹   የንባብ ጠቀሜታን በተመለከተ ለሕፃናት ግልጽ መልዕክትን  ( ያለምንም ንግግርና ገለጻ ) ማስተላለፍ ይችላሉ። በዚህ ሂደት  ዉስጥም ወጣቶች  የንባብ ባህልን ከቤተሰቦቻቸዉ  ይወርሳሉ ማለት ነዉ። እናም ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ  ሁኔታዎችን ለመከታተል ߹ አዳዲስ ነገሮችን ለመማር ወይም ለመዝናናት  ከሌሎች ዘዴዎች ይልቅ ንብብን ምርጫቸዉ ያደርጋሉ።  በሌላም በኩል ወላጆች ባካበቱት የንባብ ልምዳቸዉ አማካኝነት ለልጆቻቸዉ አዝናኝና አስተማሪ ድርሳናትን በማንበብ በልጆቻቸዉ የንባብ አመላካከት ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖን ማሳደር ይችላሉ።

      ከወላጆች ቀጥሎ የህጻናትና የወጣቶችን የንብብ ባሕል በማሳደግ ረገድ ጉልህ ሚና መጫወት የሚችሉት  መምህራን እና ት/ቤቶች  ናቸዉ። ተማሪዎች እንዲያነቡ የሚያበረታቱ መምህራንና በባለሙያ የሚታገዙና በአግባቡ የተደራጁ ቤተ – መጻሕፍት  ያላቸዉ ት/ቤቶቾ ዉስጥ የሚማሩ ወጣቶች  ከሌሎች ይልቅ በእጅጉ የተሻለ የንብብ ልምድ እንደሚኖራቸዉ ይታመናል።

       ይሁንና እስካሁን ድረስ የወጣቶቻችንን የንባተቸብ ልምድ በተመለከተ ሰፊና የተቀነቀጀ አገር አቀፍ ጥናቶች መደረጉን እርግጠኛና ባልሆንም በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚገ\ልጹት ከሆነ  ወጣቶቻችን ለንብብ ያላቸዉ አጠቃላይ አመለካከት በአብዛኛዉ አሉታዊ እንደሆነ አመላካች ናቸዉ።

        ፕሮፈሰር አለም እሼቴ በቅርቡ በአዲስ አበባ ወጣቶች  ላይ ያካሄዱት የጥናት ዉጤት ይህንኑ እዉነት ፍንትዉ አድርጎ ያሳየናል። ፕሮፈሰሩ ወጣቶች ለምን እንደማያነቡ ላቀረቡላቸዉ ጥያቄ  ከሰጧቸዉ ሰበቦች መካከል እስቲ ጥቂቱን ለአብነት ያህል እንመልከተዉ ፦

  • ንባብን ከቤተሰቤ አልለመድኩትም በአካባቢዬ ብዙ ቤተመጻሕፍት ስለሌለ አንብብ አንብብ አይለኝም።
  • ይሄ የአዉሮፓ እግር ኳስ እያለ በየት በኩል ላንብብ ።
  • ትላልቅ መጻሕፍትን ሳይ ተስፋ ስለሚያስቆረጡኝ አላነብም ።
  • የሚሰለቹ መጻሕፍት በመብዛታቸዉ ምክንያት አላነብም።
  • በጊዜ ማጣት ምክንያት አላነብም ።
  • ለምን እንደማላነብ ራሴም ምክንያቱን አላዉቅም።
  • መጽሐፍ የማላነበዉ ለዓይኔ ስለምፈራ ነዉ

       ወጣቶቹ  ላለማንበባቸዉ የጠቀሷቸዉን ሰበቦች  ጠቅለል አድርገን ስንቃኛቸዉ߹ ለወጣቶቻችን የንባብ  ችግር  ዋነኛዉ ምክንያት߹ የንባብ ፍላጎት ማጣት ሆኖ እናገኛዋለን።  

ለዚህም ከወጣቶች የንባብ ልምድ ጋር ተያያዥነት ባላቸዉ የጥናት  ድርሳት እንደ ምክንያት  የሚጠቀሰዉ የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች ጫና߹  ( እዚህ ላይ የእነ ቃና߹  የእነ ዲኤስ ቲቪ߹ የእነ ኤምቢሲ߹ የእነ ኤምቲቪ ወዘተ … ቻናሎች ለአብነት ይጠቀሳሉ። ) በተጨማሪም በሉላዊነት ሳቢያ߹  ገደብ ያልተበጀላቸዉና ከምዕራቡ ዓለም በብርሃን ፍጥነት እየተሰራጩ ያሉ የአሉታዊና መጤ ጎጂ ልማዶች መስፋፋትና ወረራ ߹ እንዲያም ሲል ወላጆች߹ መምህራንና ት/ቤቶች የንባብን ባህል ከማዳበር አንጻር መጫወት የሚገባቸዉን ሚና በአግባቡ መጫወት አለመቻላቸዉ ነዉ።   

       በመጨረሻም በተለይ ሕፃናቱንና ወጣቶችን ወደ ንባብ ባህልና ልምድ ለማምጣት ሁላችንም የድርሻችንን ማድረግ እንደሚገባን መዘንጋት የለብንም።

እናንብብ !  እናንብብ!

 

 

በሀዋሳ ከተማ መዝናኛ ቦታዎችና ጎዳናዎች ላይ ትዝብት እና አድናቆት — Law & Governance College Library


የሰዉ ልጆች እይታ ወይም ዓይን ሁልጊዜ ከተለመዱ ክስተቶች ወይም ነገሮች ይልቅ አዳዲስ እና ወጣ ባሉ ያልተለመዱ ከስተቶቸ ላይ የማረፍ ፍጥነቱ ከፍተኛ ነዉ። በዚሁ ላይ በመንተራስ በሀዋሳ ከተማ መዝናኛ ቦታዎችና ጎዳናዎች ላይ በጎ ያልሆኑ እና በጎ የሆኑ መስለዉ ከታዩኝ እይታዎቼ መካከል ከበዙዎቹ በጥቂቱ በሁለት ነገሮች ዙሪያ እይታዎቼን በመጠኑ ላካፍላቸሁ ወደደኩ እነርሱም ፤ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የፊደላት አጻጻፍ […]

via በሀዋሳ ከተማ መዝናኛ ቦታዎችና ጎዳናዎች ላይ ትዝብት እና አድናቆት — Law & Governance College Library

በሀዋሳ ከተማ መዝናኛ ቦታዎችና ጎዳናዎች ላይ ትዝብት እና አድናቆት


የሰዉ ልጆች እይታ ወይም ዓይን ሁልጊዜ ከተለመዱ ክስተቶች ወይም ነገሮች ይልቅ አዳዲስ እና ወጣ ባሉ ያልተለመዱ ከስተቶቸ ላይ የማረፍ ፍጥነቱ  ከፍተኛ ነዉ። 

Picture9
በሀዋሳ ፍቅር ሐይቅ ፊደል የወጣቶች መዝናኛ ማህበር  አካባቢ መጻሕፍት እያዞሩ  ከሚሸጡ ወጣቶች መካከል       በከፊል                   

በዚሁ ላይ በመንተራስ በሀዋሳ ከተማ መዝናኛ ቦታዎችና ጎዳናዎች ላይ በጎ ያልሆኑ  እና በጎ የሆኑ መስለዉ ከታዩኝ እይታዎቼ መካከል ከበዙዎቹ በጥቂቱ በሁለት ነገሮች ዙሪያ እይታዎቼን በመጠኑ ላካፍላቸሁ ወደደኩ እነርሱም ፤

  1. በእንግሊዘኛ ቋንቋ የፊደላት አጻጻፍ ግድፈት የሚታይባቸዉ የማስታወቂያ ጽሁፎች በጥሩ የጽሁፍ አጣጣል ተከሽነዉ በየአደባባዩና ጎዳናዎች ላይ ለሕዝብ እይታ የሚቀርቡበት ምክንያት ሆን ተብሎ በማወቅ ወይስ ባለማወቅ? ይህ ዲርጊት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሀዋሳ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም የኢትዮጵያ ከተሞች ሁሉ መታየት ከጀመረ ዉሎ አድሮ ሰነባብቷል ።ለማንኛዉም ጉዳዩ ……ን ጥያቄ ዉስጥ የሚያስገባ መሆኑ ከሁላችንም የተሰወረ አይደለም። 
Picture8
Well Come instead of Welcome 

     2.  የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ወጣቶች የዕለት ኑሮአቸዉን ለመደጎም  ሲጣጣሩ ማየት ያስደስታል። በእዉነቱ ሊበረታቱ ይገባል።

Picture3999999999999999999999999999999999
በሀዋሳ ከተማ ጎዳናዎች ላይ መጻሕፍት እያዞሩ ከሚሸጡ ወጣቶች መካከል በከፍል    የመጻሕፍት ሱቅ         በደረቴዎች          

በምን መልኩ߹ ምንም እንኳ የአንዳንዶቹ መጻሕፍት ዋጋ ዉድ ቢሆንም ቢያንስ ከእነዚህ ወጣቶች አቅም በፈቀደ መጠን የሚሸጡትን መጻሕፍት ገዝቶ ማንበብና ሌሎችም ገዝተዉ እንዲያነቡ  ማስተዋወቅ ወጣቶቹን ከመጥቀም ባሻገር የንባብ ልምድ እና ባሕልን ከማዳበር አንጻር መጠነኛ አስተዋጽኦ  እንደሚኖረዉ ለሁላችንም ግልጽ ነዉ። 

የእኛዎቹ መጻሕፍት አዟሪዎች ሊበረታቱ ይገባል 

ይህ ከታች የምታዩት ምስል በ1930ዎቹ በእንግሊዝ ለንደን ከተማ ተንቀሳቃሽ ቤተመፅሐፍት በነበረበት ጊዜ የተነሳ ፎቶ ነው፡፡”በቃ ይናገራል ፎቶ ሳይጨምር ሳይቀንስ” ማለት ይህ ነው፡፡

23244331_1649557518435860_2973408189495091275_nMobile
 የኛመጽሀፍ አዟሪዎች ሱቅ በደረቴ ሲሆኑ   የእንግሊዞቹ ደሞ ሱቅ በጄርባየ ከነሼልፉ ነበሩ  ማለት ነዉ                                  ለማንኛውም                                 ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል የሚለውን እነሱ የተረዱት ከረጅም ጊዜ በፊት እንደነበር የሚጠቁም ፎቶ ነው።
888888888888888888888888888888888888888888888888888888888
በሀዋሳ ከተማ ጎዳናዎች ላይ መጻሕፍት እያዞሩ ከሚሸጡ ወጣቶች መካከል በከፊል የመጻሕፍት        ሱቅ በደረቴዎች        

 በሙሉጌታ ወ/ጻ

Digital innovation benefits the 1% by giving rise to “winner-take-all” markets-Law Librarian Blog


via Digital innovation benefits the 1% by giving rise to “winner-take-all” markets

The Right to the City: Free Ebook Download


Book reviews: Do-it-yourself democracy, smarter states — The GOVERNANCE blog


In the current issue of Governance, Robert Chaskin reviews Do-It-Yourself Democracy by Caroline W. Lee. Lee’s analysis is “unsettling,” Chaskin says, showing how deliberative processes can be designed “in ways that legitimize cost cutting and retrenchment and that promote participant alignment with state or corporate requirements for austerity. Read the review. And Scott Fritzen reviews Smart Citizens, Smarter State by Beth Simone Noveck. The book […]

via Book reviews: Do-it-yourself democracy, smarter states — The GOVERNANCE blog

%d bloggers like this: