ርዕስ፦የዘመኑ ጥሪ ፤ ይህም ትዉልድ ያልፋል ከመቶ ዓመት በኃላ ሁሉም ያንቀላፋል ስም ግን ….?
ፀሐፊ፦በገበየሁ ፍቃዱ አዲሱ
ገጽ ብዛት፦260
የታተመበት ዓ.ም. ፦2006
የታተመበት ቦታ ፦ ባሕርዳር߹ ኢትዮጵያ
አሳታሚ፦ኃይሉ ማተሚያ ቤት
ዋጋ፦49.99
ዕለተ ሰኞ ሰኔ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. ከረፋዱ 11 ሰዓት በኃላ በሰፈረ ሳላም በኩል ሽቅብ ወደ ሀዋሳ ፒያሳ በእግረ ስጓዝ በአጋጣም የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሕዝብ ቤተመጻሕፍት ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ማስተዋል መጻሕፍት መሸጫ መደብር ጎራ አልኩና ለሽያጭ የተደረደሩትን መጻሕፍት ርዕሶች መቃኘት ስጀመር ለሽያጭ ከቀረቡት መጻሕፍትመካከል
ማስተዋል የመጻሕፍት መደብር
የዘመኑ ጥሪ ፤ ይህም ትዉልድ ያልፋል ከመቶ ዓመት በኃላ ሁሉም ያንቀላፋል ስም ግን ………..? የሚል መጽሐፍ ላይ ቀለቤ አረፈና መጽሐፉን አንስቼ ገለጥ ሳደረገዉ የክብር ስፖንሰር ሀዋሳ ዩነቨርሲቲ የሚል ከፊት ሽፋን የመጽሐፉ የዉስጥ ገጽ ላይ ካነበብኩ በኃላ መልካም ብዬ ስለመጻሐፉ ፍንጭ ጠቋሚ አሰተያየቶች ለማወቅ በመጽሐፉ የጀርባ ሽፋን ላይ የተሰጡትን አስተያየቶቸ ካነበብኩ በኃላ መጽሐፉ ያዘለዉን ፍሬ ነገር እና የሚያስተላልፈዉን መልዕክት ለማወቅ መጽሐፉን ለማንበብ ወሰነኩና መጽሐፉን ገዛሁት፤
በመጽሐፉ የጀርባ ሽፋን ላይ ስለመጽሐፉ የተሰጡ አስተያየቶች እነደሚከተሉ ናቸዉ፤
የመጽሐፍ ጥራት በከቨሩ በገበሩ አይወሰንምና ዉስጥ ገብታችሁ ፍረዱ::ፕሮፈሰር ዮሰፍ ማሞ የ ሀ ዋ ሳ ዩ ኒ ቨ ር ሲ ቲ ፕሬዚዳንት የነበሩ ይህ መጽሐፍ ለቨዚነስ ታስቦ የተደከመበት ሳይሆን ከተፈጥፘዊ የአእምሮ ምጥ በራሱ ፈንቅሎ የወጣና ትዉልድን ለማትጋት ፈጣሪ በሰዉ ላይ አድሮ ያዘጋጀዉ የዘመንሽልማትነዉ::ዶ/ ር በላይሁን ክብረት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሪፈራል ሆስፒታል ኃላፊ የነበሩ መጽሐፉ በእዉነት አንጀት ያርሳል:: ለሁለንተናዉ ለ ዉ ጥ ያ ነ ሳ ሳ ል : : እዉቀትንም በቃላት እያጣፈጠ ያጎርሳል:: በዚህ ላይ ወቅቱንና ነባራዊ ሁኔታዉን በጥልቀት የ መ ረ መ ረ ነ ዉ : : የአገላለጽ ብስለቱ ከወጣት ገበየሁ ዕድሜ ጋር ሲነጻጸር አጀብ የሚያስብል ነዉ:: ፕሮፈሰር ንጋቱ ረጋሣ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቢዚነስና ልማት ም/ፕሬዚዳንት የነበሩ መጽሐፉ በአንድ በኩል እስት የላሰ አርበኛ ነዉ:: አገላለፁና ድምፀቱ እ ያ ማ ለ ለ ለ ለ ዉ ጥ ያነሳሳል:: በሌላ በኩል ደግሞ ኮሜዲ ነዉ:: ግርምትንእየፈጠረናእጢን እየኮለኮለ ያስፈነድቃል :: ጋዜጠኛ አንተንህ ደምሰዉ በአዲስ አበባ አዲስ ክፍለ ከተማ የዝክረ እትዮጵያ አዘጋጅ
በመጽሐፉ የጀርባ ሽፋን ላይ ስለመጽሐፉ የሰፈሩ የተለያዩ የግል አስተያየቶች እንደተጠበቁ ሆነዉ ። እንደሚታወቀዉ አንዳንድ መጻሕፍት እንኳን ዘመን ሊሻገሩ ወራት እና ዓመታትን ሳይስቆጥሩ ለወረት ያህል ለ አ ፍ ታ ተ ነ በ ዉ ወ ዲ ያ ዉ ኑ ከነመጻፋቸዉም ይረሳሉ ወይም በዘመነኛዉ አካሄድ ደግሞ soft copy ከሆኑ ከኮምፒየተራችን ላይ delete ተደርገዉ ወደ recycle bin የሚላኩ መሆናቸዉን ከማንኛዉም አንባቢ የተሰወረ አይደለም ::
አንዳንዶቹ ደግሞ ለምሳሌ ከሀገር በቀል ደራሲያን ሥራዎች አልወለድም – በአቤ ጉበኛ ߹ እሳት ወይ አበባ- የዓለም ሎሬት ፀጋዬ ገ/ መድህን߹ ኦሮማይ – በበዓሉ ግርማ እና ፍቅር እሰከመቃብር- በአዲስአለማየሁ…..ወዘተ
ከፈረንጆቹ ደግሞ የሼክስፕር ሥራዎቸ ዘመን ተሻጋሪ ናቸዉ::
የንባብ ተሞክሮችንን መለዋወጥ፣ ያነበብናቸዉን መጽሐፍት ለሁሉም አንባቢዎች መጠቆም፣ ባነበብናቸው ላይ መወያየት ወዘተ….የምንመኝውን ትውልድ ለመፍጠር መንደርደሪያዎች ናቸው። ስለሆነም በLink—Up Library Newsletter አማካይነት “የዘመኑ ጥሪ ፤ ይህም ትዉልድ ያልፋል ከመቶ ዓመት በኃላ ሁሉም ያንቀላፋል ስም ግን ………..?” በሚል ርዕስ የዛሬ አራት ዓመት ገደማ በገበየሁ ፍቃዱ አዲሱ የተጻፈ መጽሓፍ እንዲታነቡ ላስተዋዉቃቸሁ ወደደኩ ።
እዚህ ላይ የመጽሐፉም ፀሐፊ ሆነ አንባቢዎች ልብ እንድትሉ የመፈልገዉ አንኳር ነጥብ እኔ እንደ ቤተ-መጻሐፍት ባለሙያ መጽሐፉን ማስተዋወቅ ሲሆን መጽሐፉን አንብቦ የመገምገሙ እና የግል ግንዛቤ ላይ የመድረሱ ጉዳይ የአንባቢዉ ፋንታ መሆኑን ነዉ ።
ከቡዙ በጥቂቱ ከመጽሐፉ ዉስጥ የተቀነጨቡ
ፕሮፈሰር ዮሰፍ ማሞ
ፕሮፈሰር ንጋቱ ረጋሣ
ፐሮፈሰር ፍቅሬ ደሳለኝ
ደ/ር በላይሁን ክብረት
አቶ አያኖ በራሶ(PhD Candidate) በአሁኑ ወቅት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት
እና
ሌሎችም በዚህ መጽሐፌ
በምስጋና አምዴ ሥር
የጠቀስኳችሁ ሁሉ በዚህ ዘመን
ኢትዮጵያ
አምጣ ከወለደቻቸዉ ልጆቿ መካከል
ጥቂቶቹ ናችሁ::
ገበየሁ ፍቃዱ አዲሱ (የመጽሐፉ ፀሐፊ)
ኢትዮጵያዊነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ይተነትናል ። ገጽ 12
በተለይም የአፍሪካዉ ንፍቀ ክበብ። አንዱ በሌላዉ መቃብር ላይ የአበባ ጉንጉን ለማስቀመጥ ተፍተፍ ይላል። አንዱ ሌላዉን ለመቸንከር ሚስማር ያቃብላል። ገጽ 74
በሀሳብና በስሜት መራራቅ߹ በቅናትና ጥላቻ መጠዛጠዝ߹ በተንኮልና ሴራ መጠላለፍ߹ በጎጥና በሰፈር መተራረድ ነግሷል። በሄዱበት ሁሉ በሰዉ ቁመት ልክ ገደል የሚቆፍር ተበራክተዋል። ገጽ 75
ሀይማኖቶችም የበጎነት አብዮትን ማስፈን አልተቻላቸዉም። ለነገሩ ሀይማኖቶች ምን ያህሉ ወደ አዳራሽ ገባ የሚለዉ ነዉ የሚያስጨንቃቸዉ። ሀይማኖቶች ሁሉ የሰዉ ልጅ ፈጣሪ ዘንድ መድረስ የሚችለዉ በእኛ መንገድ ብቻ ነዉ ይላሉ።
ታዲያ የጨረታ ዉድድር በመሰለ በዚህ አስተምሮም ትዉልድ ግራ ከመጋባት ዉጭ እንዴትስ አደብ ሊገዛ ይችላል? ዩኒቨርሲቲዎቻችንም የብሔርተኝነት߹ የፅንፈኝነት߹ የሴሰኝነትና የሱሰኝነት ጣቢያ እየመሰሉ ባሉበት በዚህ ወቅት በጎ መሆን ፈተና ዉስጥ ቢገባስ ምን ይደንቃል? ገጽ 78
የሕግ የበላይነት ከሰዎች የበላይነት በተቃራኒ የቆመ ነዉ። ሀ ና ለ በሕግ ፊት እኩል ናቸዉ። ጉልበት ያለዉም ጉልበት የሌለዉም ሀብት ያለዉም ሀብት የሌለዉም ጭምር። ተግባራቱን ስንመረምር ግን ስልጣን አልያም ባለሀብት ላይ ሄዶ ይነገራገጫል። ሁሉም እንስሳ እኩል ናቸዉ አንዳንዶቹ ደግሞ የበለጠ እኩል ናቸዉ (ጆርጅ ኦርዌል)። ገጽ 84
ዳኛ ተከሳሹን ጥፋተኛ ነህ አይደለህም? ሲለው ተከሳሹ መልሶ ያሴራችሁብኝን መረጃ መቼ ሰማሁ? ብሎ መለሰ የምትባል ተረትም አለች።
በዉስጥ እያሴሩ ላዩን ማለት ፈገግ
የሄነዉ ዘመኑ ስልታዊ ማፈግፈግ
ገጽ 86
እንግሊዝም መጣ ደርሶ ተመለሰ
ኢጣሊያንም መጣ ደርሶ ተመለሰ
ክፋት ብቻ ቀረ ቤት እያፈረሰ
ገጽ 88
ፖሊሱም ፀጥ ብለህ ቀጥል ዳኛዉም አፍህን ዘግተህ ዉጣ߹ ሰባኪዉም ዝም ብለህ እመን ፖለቲከኛዉም እኔን ብቻ አይተህ ተከተል … በሚል የማይጠይቅና ሞራል አልባ ትዉልድ ለመፍጠር መትጋቱ ክልብ ሊታረምና ሊጤን ይገባዋል። ገጽ 106
የኃላፊነት ቦታዎች በትክክልኛና በሚመጥናቸዉ ሰዎች ሊመሩ ይገባል። ህዝቡን አግባብቶ እና ተንከባክቦ መምራት ሲገባዉ ህዝቡን እንደበግ በዱላ የሚመራ ከሆነ߹ ………
ገጽ 113
ተጥዶ ያልፈላ ተሹሞ ያልበላ እያሉ ለአለቆቻቸዉ ጭራቸዉን እየቆሉ በቃሪያ እንደሚበላ የህዝቡን ንብረት የሚጠቀልሉ እንዲያ ሲልም በጅራፍ የሚቆሉ ለአለቆቻቸዉ ማር እያላሱ ህዝቡን አፈር የሚያስልሱ ከዶላርም በላይ በድንጋይ ወርቅ የሚመነዝሩ߹ ለበርካታ ሰዉ የሚበቃዉን ግጦሽ ብቻቸዉን የሚነጩ ተዉ እረፉ ሊባሉ ይገባል። ገጽ 118
በእከክልኝ ልከክልህ በላሽ አላሽ ትንኝ የማያስገባ መረብ ሰርቶ እሸሼ ገዳሜ መደለቁ ስህተት ነዉ። በመረቡ እንዳይጠለፉ አይተዉ ዝም የሚሉም ብዙዎች ናቸዉ አልያም የጥፋቱ ተጋሪዎች ናቸዉ። “ A dog with a bone in its mouth can’t do two things” በአፉ አጥንት የያዘ ዉሻ መጮህም መንከስም አይችልም። ገጽ 119
የዘመኑ ልጆች ደግሞ ከመጥሚጣ በላይ የሚያቀጥሉ ናቸዉ። ጊዜያቸዉን በምግብ ዓይነት ጥናት የሚገድሉ ናቸዉ። ለምሳሌ የድሮ ልጆች ቤት እንግዳ ሲመጣ ጓዳ ነበር የሚደበቁት። የአሁኑ ጊዜ ልጆች ደግሞ እንኳ ንስ ሊደበቁ ይቅርና እንግዳውን እንደ ርዕስ ብሔር የራሳቸዉ ክፍል ዉስጥ አስገብትው ካነጋገሩ በኃላ ነዉ ወደ ዋናዉ ቤት መርተዉ ይዘዉት የሚገቡ߹ ….ገጽ 136
መንገድ ላይ ብቻዬን በመሄድ ላይ ሳለሁ አንድ ሰዉዬ ከበዓል ገበያ መልስ ብቻዉን እንዲህ ያወራል። ምነዉ ፈጣሪ ይህን የመሰለ የጅብ ሆድና ስለት የአዞ ጥርስ ሰጥቶ ስጋ ይነሳኛል። ዘመድ ዘንድ ሄጄ በዓሉን እንዳላሳልፍ እንኳ ን በዚህ ዘመን ዘመድን ዘመድ ጥልቶታል። ዘመድ ተብዬዉ እራሱ ኑሮወ እንደመርግ ተጭኖታል። በስም የስጋ ዘመድ እንጂ ስጋ የሚያበላ አሁን ከወዴት ይገኛል። ግበረ ስጋ በረከሰበት ጊዜ እንዴትስ ከረሜላ የምታክል ስጋ ሰማይ ጥግ ትደርሳለች ። ገጽ 142
ትዉልድን የሚያጠፉ የትዉልደ አትዮጵያዊያንን አንገት የሚያስደፉና የሚያሳፍሩ ጭፈራ ቤቶች እንደተበራከቱ አይተናል። በዚህ ዉስጥ ሴቶቻችን የጨለማ ንጉስ ሆነዉ ተሹመዋል። ገጽ 185
ዛሬ የመማርና የማወቅ ዋጋ ምንም በመሰለባት ሀገራችን ለመመራመርና ለንባብ የሚነሳሳ ሰዉ ማግኘት ቢቸግር አይደንቅም። ይልቁንም በከተሞቻችን እንደ አሸን የፈላዉ ቡቲክ በዋነኛነት በሴቶች አልባሳትና ጌጣጌጦች ተሞልቶ ለተመለከተ አንደ እኔ ዓይነቱ ….. በየዕለቱ የሚያስጨንቀዉ የዩኒቨርሲቲ መምህር …… አይፈረድበትም ። ገጽ189
ጊዜዉን ከመጽሐፍ ንባብ ይልቅ ለቪዲዮ ፊልሞች ያስረከበ ትውልድ ስለ ሀገሩ ይቅርና ስለእራሱ የሚያስበዉን መገመት አያዳግትም። ገጽ 206
መልካም ንባብ
SHARING IS CARING! Please Share Clicking On The below Social Network Buttons Like this: Like Loading...
You must be logged in to post a comment.