ብሔራዊ ቤተመዛግብት አስፈላጊነቱ ሲገመገም ከብሔራዊ ቤተመጻሕፍት እና ቤተመዛግብት ድርጅት November 3,2017


የሰዉ ልጅ ካለፈዉ  ታሪኩና  ከያዘዉ ባህሉ  በመነሳት ራሱን  ከተለያዩ የተፈጥሮም  ሆነ ሰዉ ሰራሽ አደጋዎች  ለማዳንና  የወደፊቱን የኑሮዉን ሁኔታ  በተሻለ የልማት  አቅጣጫ  ለመተለም በጽሁፍ  መረጃዎቸ /መዛግብት/ በከፍተኛ ደረጃ  ይጠቀማል።  መዛግብት የተለያዩ መንግሥታዊ߹  ሕዝባዊና የግል ድርጅቶች  እንዲሁም ግለሰቦች የዕለት ተዕለተ ተግባራቸዉን  ለማከናወን በሚያደርጉት እንቅስቃሴ  የሚፈጠሩ   /የሚመረቱ/ የመረጃ ምንጮች ናቸዉ። 

መዛግብት  ለመነጩበት አካባቢና ሕዝብ በባህላዊ ቅርስነታቸዉ߹  በተጨባጭና በመጀመሪያ ደረጃ  ታሪካዊ  ማስረጃነታቸዉ  ያገለግላሉ።   ምንም እንኳ አፈታሪክና መዛግብት በመጀመሪያ ደረጃ  የመረጃ ምንጭነት ቢታዩም߹ አፈታሪኮች ሊረሱ ወይም የተሳሳተ  መልዕክት  ሊይዙ  ስለሚችሉ  ተጨባጭ ባለመሆናቸዉ  ማስረጃነታቸዉ  ከመዛግብት ጋር ሊወዳደር አይችልም።

ከመጻሕፍት የምናገኛቸዉ መረጃዎች  በሁለተኛ ደረጃ  የመረጃ ምንጭነት ሊታዩ  የበቁትም ዋነኛዉ ምክንያት  የመጻሕፍት መሠረቱ መዛግብት  ስለሆኑ ነዉ።  ከመዛግብት የሚገኙ  መረጃዎች  ማንኛዉም ዓይነት  ማህበራዊ  “ለዉጥ”   ከማምጣት አንፃር  ያላቸዉ ሚና  ሲታይ ራሱን እንደቻለ  “ኃይል”   ሊቆጠሩ ይችላሉ።  “መረጃ ኃይል ነዉ” “Information is power” የሚለዉ አባባል  ይህን ሁኔታ በሚገባ  ከመግለጹም በላይ  የመረጃ  ሳይንስ  በተራቀቀበት  በአሁኑ  ዘመን  ከመቼዉመ  ይበልጥ ትክክለኛ ሆኗል።

በኢትዮጵያ በመጠኑም ቢሆን  በመዛግብት አያያዝ  በኩል  ለዉጥ የታየዉ  የዳግማዊ ምኒሊክ  ቤተመዛግብት የ19ኛዉ ክፍለ ዘመን  የመዛግብት ቅሪት  በማሳባሰብ  “ጥንታዊ  መዝገብ ቤት “  በሚል ስያሜ  በአዲስ መልክ  ተቋቁሞ  ሥራዉን ከጀመረ ወዲህ ነዉ።  ሆኖም  ጥንታዊ መዝገብ ቤትም ሆነ ከዚያ  በመቀጠል  በተከታታይ በየሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ  ለተቋቋሙት መዝገብ ቤቶች   ለመዛግብት አያያዝ  በአዋጅ የተወሰነ ሕግ ወይም ዘመናዊ አሠራር  የተደገፈ አንድ ወጥ ሥርዓት  ስላልነበራቸዉ እጅግ  አስፈላጊ  የሆኑ  ታሪካዊ  መዛግብት  የደረሱበት ሳይታወቅ  ጠፍተዉ  ቀርተዋል ߹ ግለሰቦች እጅ ገብተዋል߹  ለቱሪስት ተሽጠዋል ߹ ወዘተ… በአሁኑ ጊዜ  በየመንግሥት  መሥሪያ ቤቶች  በግል ድርጅቶች  መዝገብ ቤቶች  ዉስጥ  ቁጥሩ  እጅግ  ከፍ ያለ  የመዛግብት ክምችት እንዳለ  ይታወቃል።   እነዚህ በተለያዩ ይዞታዎቸ ሥር የሚገኙ  መዛግብት  የኢትዮጵያን ባሕል  ሃይማኖትና  ፍልስፍና߹ ፖለቲካና አስተዳደር߹    ሥዕልና መዙቃ߹    ንግድና  እንዱስትሪ߹   ሕክምናን የመሳሰሉትን  ሳይንሳዊ መስኮች  የሚገልጹ  የመጀመሪያ ደረጃ  የመረጃ ምንጮች  ናቸዉ።    በመሆኑም እዉነተኛና  ታሪካዊ  ንቃተህሊናን  በመፍጠር  ለሀገሩና ለባሕሉ    ተቆርቋሪ  በራሱ የሚተማመን  ዜጋን ለማፍራት ከማገልገላቸዉ ባሻገር  ለብሔራዊ አንድነትና  ሕልዉና  እንዲሁም ለኢኮኖሚ  ግንባታ  አስተማማኝ  የሆነ ትምህርታዊ  መረጃ ይሰጣሉ።    ነገር ግን  እነዚሀ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ  ግንባታና  ለማኅበራዊ ዕድገት  መሠረታዊ የሆነ የአካባቢ  ነባራዊ  እዉነታዎች ነጸብራቅ  የሆኑት የጽሁፍ መረጃዎች  በሀገር ደረጃ  እና   በመሥሪያ ቤት  ደረጃ ማዕከላዊ አሠራራን  በተከተለ መንገድ በጥንቃቄ መያዝ እና መደራጀት አለባቸዉ። 

በመዛግብት አያያዝ በኩል  ምሣሌ ስለሚሆኑ መዝገብ ቤቶች  በተደረገዉ ጥናት  መሠረት የቦታ ጥበት ባስከተለዉ  ችግር መተኪያ  ሊገኝላቸዉ የማይችሉ  የሀገሪቱ ታሪካዊ ማስረጃዎች  ከጥቅም ዉጪ  ሊሆኑ እንደሚችሉ  ያላቸዉን ስጋት  የየመዝገብ ቤቶቹ ኃላፊዎች  ገልጸዋል። በተጨማሪም  ጠቃሚ ያልሆኑትን /Dead Files/ ጠቃሚ ከሆኑት/Active Files/ በመለየት የማስወገጃ ደንብ ባለመኖሩ አንድ ላይ አስፈላጊ  ያልሆነ ጥበቃ ይደረግላቸዋል ። 

ብሔራዊ  ቤተመዛግብት የጥንታዊት ኢትዮጵያን  የታሪክ መረጃ መሠረት የሆኑትን  የመዛግብት ቅርስ በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲጠበቁና  በማንኛዉም  መስክ ለሚቀናበሩ  ትምህርታዊ  ዝግጅቶች  ከአካባቢ እዉነታ ጋር  የተመሠረቱ ሆነዉ  የፈጠራ ችሎታ እንዲያዳብሩ  አደራጅቶ  በሚፈለጉበት  ጊዜና ሁኔታ  እንዲገኙ የሚያደርግ ነዉ። 

በታሪካዊና በባህላዊ ቅርስነታቸዉ  እንዲሁም በመረጃ ምንጭነታቸዉና  በአገልግሎታቸዉ  አንፃር ታይተዉ  ከመንግሥታዊ  ሕዝባዊና ከግል ድርጅቶች  ከግለሰቦች  እጅ  አስተዳደራዊ አገልግሎታቸዉን የጨረሱትን መዛግብት  በአዋጅ በተሰጠዉ ሥልጣን በግዥ߹  በስጦታና ߹ በልዉዉጥ   ወይም  በቅጂ ለመተካት  ሲባል  በዉሰት  አማካይነት ይሰበስባል። ጠቃሚ  ለሆኑት መዛግብት  ልዩ እንክብካቤ  ያደርግላቸዋል ። ለሰዉ ሠራሽ እና ለተፈጥሮ አደጋ ባልተጋለጠ  ሕንፃ ዉስጥ  በማኖርና  ከተላያዩ ጥፋቶች  በመጠበቅ የመጥፋትና የመንገላታት ዕድል ሳይገጥማቸዉ  በሥርዓት  ተሰብስብዉና  ተከማችተዉ  ለጥናትና  ምርምር  አገልግሎት እንዲዉሉ  አመቺ ሁኔታ  ይፈጥራል።    በተለያዩ ይዞታዎች ሥር ለሚገኙ  መዝገብ ቤቶች በመዛግብት ሳይንስ/Archival Science/ ላይ የተመረኮዘ  አንድ ወጥ የሆነ  የመዛግብት አያይዝ ሥልጠና ይሰጣል።

  ምንጭ߹ ፈለገ ጥበብ የኢ.ብ/ቤ/ቤ/ ድርጅት መጽሔት

 

Advertisement

Solomon Deressa – a prominent #Ethiopia|n poet – passed away, November 3,2017.


ታዋቂው ኢትዮጵያዊ ገጣሚ ሰለሞን ዴሬሳ በ80 አመቱ በአሜሪካን አገር ከዚህ አለም በሞት ተለየ ። በወለጋ የተወለደው ሰለሞን በሚኒሶታ አርፏል ። ገጣሚ፣ መምህር፣ የፍልስፍና ሊቅ፣ ጋዜጠኛ ሰሎሞን የዩናይትድ ስቴትሷ ሚኔሶታ ነዋሪ የነበረ ሲሆን ከሥራው ገበታ በብርቱ ሕመም እስከተለየ ድረስ በሚኔሶታ ዩኒቨርሲቲ የሃይማኖቶች ንፅፅር (ኮምፓራቲቭ ረሊጅን) የፍልስፍና መምህር ሆኖ ሲሠራ ቆይቷል።

ዝርዝር የሕይወት ታሪኩ እነሆ ፦Solomon Deressa Biography  Click Here to read

Solomon Deressa
 Solomon Deressa

 

  • Review by Solomon Deressa Walaloota Zalaalam Abarra  Click Here to read
  • ዊሊያም ሸክስፒር – ጋሽ ሰሎሞን ደሬሳ በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር። CLICK HERE  

44 ሺህ መጻሕፍት ለኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች ያሰባሰቡ ምሁር


ሳይንስ/ቴክኒክ

ነዋሪነታቸውን በውጭ ሀገራት ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ምሁራን በተለያየ መልኩ ሀገራቸውን ለመርዳት ሲሞክሩ ይስተዋላል፡፡ በአሜሪካ የኖርዝ ካሮላይና የግብርና እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ መምህር ዶ/ር አበበ ከበደ ከእንዲህ አይነቶቹ ይመደባሉ፡፡ መምህሩ ወደ 44 ሺህ ማጣቀሻ መጽሐፍትን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ለተለያዩ ትምህርት ቤቶች አከፋፍለዋል፡፡

 

Picture9AK Front
 ዶ/ር አበበ
ካሰባሰቧቸዉ መጻሕፍት ጋር

ምሁሩ ተንቀሳቃሽ ቤተሙከራን ለማምጣት እየጣሩ ነው

የዛሬ ስምንት ዓመት ግድም ነው፡፡ በኦሮሚያ ክልል አሰላ ከተማ የሚገኘው የጭላሎ ተራራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ጥቁር ሰማያዊ የደንብ ልብሳቸውን እንደለበሱ እንግዶቻቸውን ለመቀበል ተሰልፈዋል፡፡ ገሚሶቹ በሌጣ እጆቻቸው እያጨበጨቡ፣ ሌሎቹ ደብተሮቻቸውን እየመቱ በመሀላቸው ሰንጥቀው የሚያልፉትን እንግዶች በፈገግታ ይመለከታሉ፡፡ የባህል ልብስ ያጠለቁ ወጣት የኪነት ቡድን አባላት በባህላዊ ዜማ እና በእልልታ እንኳን ደህና መጣችሁ ይላሉ፡፡ 

Picture8AK12
በተማሪዎች የአቀባበል ስነ-ስርዓት
ሲደረግላቸዉ   

እንዲህ አይነቱ የአቀባበል ስነ-ስርዓት የተከናወነው ከዓመታት በፊት በዚያ ትምህርት ቤት አስተምረው የነበሩ የአሜሪካ የሰላም ጓድ አባላት እና የቀድሞ ተማሪዎች ለጉብኝት እንደገና መምጣታቸውን በማስመልከት ነበር፡፡ ጉብኝታቸው የቆየ ትዝታን ማደስ ብቻ አልነበረም፡፡ ዓላማ ነበረው፡፡ የእዚህ ጉብኝት ጠንሳሽ እና አስተባባሪ የቀድሞው የትምህርት ቤቱ ተማሪ ዶ/ር አበበ ከበደ አንድ ዓመት ቀደም ብለው ወደዚያ ጎራ ባሉ ጊዜ ያስተዋሉት ችግር ነው የጉብኝቱን ዓላማ የወለደው፡፡ ያኔ የቪዲዮ ካሜራቸውን አንግበው በትምህርት ቤቱ እየተዘዋወሩ ያሉትን ችግሮች ጠይቀዋል፡፡ በወቅቱ ስናፍቅሽ አበበ የተባሉ የትምህርት ቤቱ የቤተ መጽሐፍት ሰራተኛ በትምህርት ቤቱ የመጽሐፍት ችግር በከፍተኛ ሁኔታ እንዳለ ነግረዋቸዋል፡፡ 

የቤተመጽሐፍቱን ሰራተኛ ገለጻ በዚያ ወቅት የትምህርት ቤቱ ተማሪ የነበረው በሱፍቃድ ጌታቸውም ይጋራዋል፡፡

በ1941 ዓ.ም የተመሰረተው የጭላሎ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በበሱፍቃድ ጊዜ የመሰናዶ ትምህርት ቤት ሆኗል፡፡ የዘጠነኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ብቻ በሚያስተናግደው በዚያ ትምህርት ቤት ያለውን የመጽሐፍ እና የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች አቅርቦት እንዲህ መለስ ብሎ ያስታውሳል፡፡

“መሰናዶ ትምህርት ቤት ላይ ጠልቀን የተለያዩ መጽሐፍትን ስለማናጣቅስ በሰዓቱ ያን ያህል ብዙ መጽሀፍትን አንፈልግም ነበር፡፡ ግን ያሉትን የምንፈልጋቸው መጽሐፍት ግን በብዛት ደረጃ ጥቂት ነበሩ፡፡ ያው ትንሽ ተማሪዎች ከያዟቸው አይገኙም፡፡ መጠበቅ ይኖርብሃል የተወሰነ ጊዜ፡፡ በተረፈ ግን ጭላሎ ትምህርት ቤት እያለሁ በወቅቱ የነበረው ነገር ኮምፒውተር አለ ብሎ ለመናገርም አያስደፍርም” ይላል በሱፍቃድ፡፡

በትምህርት ቤቶች የመጽሐፍት እና የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች እጥረት በተማሪዎች ውጤት ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ እንደሚያሳድር በጉዳዩ ላይ የተደረጉ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ጭላሎ ተራራን ጨምሮ በአሰላ የሚገኙ ሶስት የመንግስት ትምህርት ቤቶች ላይ በሀሮማያ ዩኒቨርስቲ የተደረገ ጥናትም ይህንኑ በማስረጃ አስደግፎ ዘርዝሯል፡፡ የጥናቱ አማካሪ የነበሩት እና በሀሮማያ ዩኒቨርስቲ የትምህርት እና ስነ-ባህሪ ሳይንስ ኮሌጅ መምህር ዶ/ር ይልፋሸዋ ስዩም ስለ ጉዳዩ ተከታዩን ብለዋል፡፡

“መጽሐፍት እንግዲህ በአሁኑ ሰዓት ታትመው የተጠረዙት ብቻ አይደሉም፡፡ የታተሙት በጣም ውድ ናቸው፡፡

ሶፍት ኮፒዎችን ለማግኘት የኢንተርኔት እና የኮምፒውተር አገልግሎት እንደዚሁ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይህን ዕድል የሚያገኙት ወይ የሉም ወይ ቁጥራቸው በጣም ውስን ነው፡፡

በጣም አስፈላጊ እና መሟላት ያለባቸው ናቸው፡፡ መንግስትም ይህን ይቀበላል” ይላሉ መምህሩ፡፡ 

Picture7AK13

ለጭላሎ ተራራ ትምህርት ቤት መጽሐፍትን ለማምጣት ቃል የገቡት ዶ/ር አበበ መጽሐፍት እንዴት ውድ እንደሆኑ አልሳቱትም፡፡ የግዢውን ወጪ ለመቀነስ ግን መላ ዘይዱ፡፡ ወደ አሜሪካ ከተመለሱ በኋላ ትምህርት ቤቱን ከጎበኙት የቀድሞ የሰላም ጓድ አባላትን እና የአሰላ ወዳጆችን በማስተባበር የቻሉትን ያህል ማሰባሰብ ያዙ፡፡ የፊዚክስ አስተማሪው ዶ/ር አበበ ቅድሚያውን ለሳይንስ ዘርፎች ነበር የሰጡት፡፡ በሌሎች ዘርፎች የተጻፉ እና በርካታ መጽሐፍትን ለማግኘት ደግሞ በዚያው በአሜሪካ የሚገኝ ለትርፍ ያልተቋቋመ፤ በመጽሐፍት ዙሪያ የሚሰራ ድርጅትን በር አንኳኩ፡፡

“የመጽሐፍ ችግር የለም፡፡ መጽሐፍ ማሰባሰብም አያስፈልግም፡፡ ግን እኛ ብዙ ሰብስበናል፡፡ የህክምና፣ ህግ፣ ለልዩ ፍላጎት የሚሆኑ ሰብስበናል፡፡ ለስፖርት የሚያገለግል ጭምር ሰብስበናል፡፡

“Books For Africa” የሚባል ድርጅት አለ፡፡ እዚህ ከተመለስን በኋላ ከእርሱ ድርጅት ጋር ተባበርን እና የመጀመሪያው ጭነት [በጎርጎሮሳዊው] 2010 ሄደ፡፡ በነገራችን ላይ “Books For Africa” የእኛ ድርጅት አይደለም፡፡

እነሱ የሚያደርጉት ዋናው ነገር ምንድነው? ፕሮጀክት ትሰጣቸዋለህ፡፡ ይሄን ይሄን እሰራለሁ ብለህ፣ ተጠቃሚው ለይተህ ትሰጣቸዋለህ፡፡ “Books For Africa” መጽሐፉን በነጻ ነው የሚሰጥህ፡፡ ግን መጽሐፍ ሲላክ በኮንቴየነር ሆኖ እስከ 20 ሺህ መጽሐፍት ይላካል፡፡ ለመላኪያ የሚሆነው ገንዘብ ብዙ ነው፡፡ እስከ 20 ሺህ ዶላር ያወጣል” ይላሉ ዶ/ር አበበ፡፡

በነጻ የተገኘን መጽሐፍ ለመላክ እንዲህ ብዙ ዋጋ ቢያስከፍልም ዶ/ር አበበ እና ጓደኞቻቸው ለሻይ እና ቡና የሚያወጡትን እየለገሱ፣ ከሌሎች ሰዎች ገንዘብ እያሰባሰቡ ከአንድም አራት ጊዜ መጽሐፍት ወደ ኢትዮጵያ ልከዋል፡፡ በአጠቃላይ የላኳቸው መጽሐፍት 44 ሺህ ገደማ መድረሳቸውን ዶ/ር አበበ ይናገራሉ፡፡ ለቀድሞ ትምህርት ቤታቸው የተጀመረው የመጽሐፍት ማሰባሰብ በአሰላ እና አርሲ ለሚገኙ ሌሎች ትምህርት ቤቶችም ተርፏል፡፡ ወደ አሜሪካ ከመጓዛቸው በፊት ያስተምሩበት የነበረው የጎንደር ዩኒቨርስቲም የትሩፋቱ ተቋዳሽ ሆኗል፡፡ የጭላሎ ተራራ ትምህርት ቤትን ማዕከል በማድረግ ስላከፋፈሏቸው መጽሐፍት ዝርዝር አላቸው፡፡ 

“ያንን ትምህርት ቤት አማካይ በማድረግ በአሰላ አካባቢ እና አርሲ ውስጥ ያሉ ወደ 35 ትምህርት ቤቶች ረድተናል፡፡ ጠቀሜታው ሲታይ ቢያንስ ወደ መቶ እና 150 ሺህ ተማሪዎችን ጠቅሟል፡፡ 44 ሺህ መጽሐፍት ለአሰላ አካባቢ ሄደ በምትልበት ጊዜ እዚያ ውስጥ ተጠቃሚ የሆኑ ዩኒቨርስቲዎች አሉ፡፡ የአዳማ ዩኒቨርስቲ የህክምና ትምህርት ክፍሉ አሰላ ነው ያለው፡፡ አሁን አርሲ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ይሆናል፡፡ እርሱ በብዛት የህክምና መጽሐፍት ወስዷል፡፡ ጎንደር ዩኒቨርስቲ በብዛት የህክምና መጽሐፍት ወስዷል፡፡ እንደገና ብዙ የፊዚክስ መጽሐፍት ወስዷል፡፡ ሌላ ደግሞ ብዙ ሳጥን ለአይነ ስውራን የሚሆን ብሬል ለሳይንስ ለሚያሰተምሩ ተብሎ ተሰጥቷል፡፡ እዚያ የሰጣናቸው ብዙዎቹ የሳይንስ መጽሐፍት ናቸው፡፡ አሰላ አግኝቷል፡፡ ጎንደርም አግኝቷል” ሲሉ ያሰባሰቧቸውን መጽሐፍት መዳረሻ ይዘረዝራሉ፡፡ 

Picture5AK Book

ዶ/ር አበበ መጽሐፍት ለየትምህርት ቤቶቹ እና ዩኒቨርስቲዎቹ በማምጣት ብቻ አልተወሰኑም፡፡ ይልቁንም ተማሪዎች ከመደበኛው ትምህርት ጎን ሁሉገብ እውቀት እንዲያገኙ የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ “[ከጎርጎሮሳዊው] 2009 እስከ 2014 ድረስ አንዳንድ አውደጥናቶች፣ ወጣቶችን የማብቂያ (youth empowerment) ዝግጅቶች፣ ትምህርታዊ ጉባኤዎችን አካሄደናል፡፡ እንደውም ከአዳማ ዩኒቨርሲቲ የህዋ ሳይንስ ክበብ ጋር ተባብረን ለመለስተኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የሳይንሳዊ ማስተዋወቂያ ዝግጅት አድርገናል፡፡ ጎንደር ሄደን የጎንደር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ትምህርት መስጫ አቋቁመናል፡፡ እንዴት አድርገን አቋቋምነው? እኔ ወደ ኢትዮጵያ ስሄድ ጎንደር ዩኒቨርስቲ ድሮ እኔ ሰራተኛ ስለነበርኩ ልመጣ ነው ስላቸው እሺ ና እና ትምህርታዊ ጉባኤ ስጥልን ነው የሚሉኝ፡፡ አንድ ብጣሽ ጉባኤ ምን ያደርግላቸዋል፤ ለምን 10 ይዤ አልሄድም እላለሁ፡፡ አስር ልጆች ግማሹ ሂሳብ፣ ግማሹ ኬሜስትሪ፣ ግማሹ የማህበራዊ ጥናት በማንኛውም ዘርፍ አስር ዶክትሬት ዲግሪ ያላቸው ይዤ ልሄድ እችላለሁ ባይ ነኝ እኔ፡፡”

“እንዴት ታደርጋለህ? በለኝ፡፡ ሁልጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ስሄድ ባዶ እጄን መሄድ አልፈልግም፡፡ ምንም ነገር ከሌለኝ አልሄድም፡፡ ይቺን ምክንያት አድርጌ ምን አደርጋለሁ? ጓደኞቼን በሙሉ ለዕረፍት ሲሄዱ ‘እባካችሁን ወደ ጎንደር ልሄድ ነውና እንሂድ አብረን’ እላችኋለሁ፡፡ ለምሳሌ የኢትዮጵያ ተቋም አስር ሰዎች ከአሜሪካን ሀገር ወይ ከቦታው አንስቶ ጎንደር ድረስ ወስዶ፣ ቀልቦ፣ ደህንነታቸውን ጠብቆ፣ ሌላም ነገር አድርጎ አስር ሰው ለማስተናገድ አንድ ሙሉ ቤተ መጽሐፍት የሚሰራ ወጪ ነው የሚሆነው፡፡ ስለዚህ እኛ የምናደርገው በራሳችን ወጪ አዲስ አበባ ድረስ እንሄዳለን፡፡ ከአዲስ አበባ በኋላ የሚያስተናግደን ዩኒቨርስቲ ኑ ይለን እና የሀገር ውስጥ ድጋፍ ይሰጠናል፡፡ እዚያ ሄደን የሚሰራውን ስራ ሰርተን ወደ መጣንበት እንመለሳለን” ይላሉ ዶ/ር አበበ፡፡ ከጓደኞቻቸው ጋር እኒህን ተግባራት በየዓመቱ እንደሚያከናውኑ የሚናገሩት ዶ/ር አበበ በየዩኒቨርሲቲዎቹ እና ትምህርት ቤቶቹ ሲዘዋወሩ ያስተዋሉት የቤተ-ሙከራ እጥረት ለሌላ ውጥን እንዳነሳሳቸው ይገልጻሉ፡፡ አዲሱ ውጥናቸው ተንቀሳቃሽ ቤተ-ሙከራን ወደ ኢትዮጵያ ማምጣት ነው፡፡ አንድ ተንቀሳቃሽ ቤተ ሙከራ ሹፌር፣ መምህር፣ ላብራቶሪ ቴክኒሺያን እና የጥገና ባለሙያ ብቻ እንደሚያስፈልገው በማንሳትም አዋጪነቱን ያሰምሩበታል፡፡ እርሳቸው የሚያስተምሩትን ፊዚክስን በምሳሌነት በመጥቀስ የቤተ-ሙከራን አስፈላጊነት ከኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር አስተሳስረው ያስረዳሉ፡፡

“አሁን ለምሳሌ ፊዚክስ 101 ሁለት ክፍል አለው፡፡ አንዱ ንድፈ ሀሳባዊው ክፍል ነው፡፡ ዋናውን፣ ዓላማውን ይማራሉ፡፡

AK Book 2

ነገር ግን ቤተ ሙከራ ለመስራት ከፈለጉ ምን ይደረጋል መሰለህ? ለምሳሌ ሰመራ ዩኒቨርስቲ [የቤተ-ሙከራ] ዕቃዎች የሉትም ስለዚህ ልጆቹን በአውቶብስ ያደርጉ እና ወይ ጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ ወይም ቀረብ ያለ ቤተሙከራ ያለበት ይወስዷችዋል፡፡ ከአምቦ ልጆቹን ነቀምቴ ዩኒቨርሲቲ ወስደው ያሰሯቸዋል፡፡ ወልዲያም እንደዚሁ፡፡ ይሄ ሁለት ችግር አለው፡፡ አንደኛ ልጆቹ [ትምህርታቸው ላይ] ትኩረት አያደርጉም፡፡ እንደ አገር ጎብኚ በየቦታው ነው የሚዞሩት፡፡ የተረጋጋ አይደለም፡፡ ቤተ-ሙከራ ሊሰሩ  15 ቀን [ወስደው]፣ በአውቶብስ ተጉዘው ነው፡፡ በዚያ ላይ አደጋም ይኖራል፡፡ ለልጆቹም አስተማማኝ አይደለም፡፡

“መደረግ ያለበት ምንድነው? አንድ ታሳቢ ሊሆን ይችላል፡፡ ዕቃ ለመጫን በዚታዎ የምትስበው አለ አይደለም? ያችን ተሳቢ ውስጧን የሚያስፈልጉቷን የቤተ-ሙከራ ዕቃዎች በማድረግ የራሷ ጄኔሬተር ያላት ማድረግ ይቻላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ እንደውም በጸሀይ ሀይል፣ በባዩ ፊዩል ማንቀሳቀስ ይቻላል፡፡ እነኛን የቤተሙከራ ዕቃዎች ካደረግኽ በኋላ ‘ሰመራ ዩኒቨርስቲ ቤተ ሙከራ እሰራለሁ፣ ቤተሙከራ ይምጣልኝ’ ካለ እዚያ ታቆምላችዋለህ፡፡ የቤተ-ሙከራ ስራቸውን ሲጨርሱ ዚታዎ ይመጣና ጎትቶ ጅጅጋ ዩኒቨርስቲ ያስፈልገው እንደሆነ እዚያ ያቆማል፡፡ እንደዚያ ውጤታማ ይሆናል ማለት ነው” ሲሉ ከእቅዳቸው ጀርባ ያለውን ምክንያት ያብራራሉ፡፡

ዶ/ር አበበ ይህንን የተንቀሳቃሽ ቤተ-ሙከራ ፕሮጀክት ማጠናቀቃቸውን እና ደጋፊ አጋር እየፈለጉ እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡ ከመጽሐፍ እርዳታው ጎን በትንሹ የጀመሩትን የኮምፒውተር ልገሳንም ወደ መጽሐፍ ማንበቢያ ታብሌቶች የማሳደግ ህልም አላቸው፡፡

ምንጭ፤http://p.dw.com/p/2hxXf?maca=amh-Facebook-

በአሁኑ  ወቅት በአሜሪካ የኖርዝ ካሮላይና የግብርና እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ መምህር  ናቸዉ፡፡

 / አበበ ከበደን

Abkebede@gmail.com     ኢሜይል በኩል ማግኘት ይቻላል

Picture4AK last
Associate Professor of Physics at NC A&T State University and Higher Education Consultant.
NC A&T State University.
Temple University
Greensboro/Winston-Salem, North Carolina Area 

  

   

 

Advances in Materials Chemistry 2017; 1(2): 55-61 http://www. sciencepublishinggroup.com/j/amcdoi: 10.11648/j.amc.20170102.12


 

Science directPicture2ZA

Dye-Sensitized Solar Cell Using Natural Dye Extracted from Damakase (Ocimum Lamiifolium) and Dambursa (New Plant)

Ashenafi Belete Lejamo1, *, Zekarias Gebreyes Eticha2, Allah Dekama Jarra2

1 Department of Physics, Faculty of Natural and Computational Science, Hawassa University, Hawassa, Ethiopia  2 School of Materials Science and Engineering, Jimma University, Jimma, Ethiopia

Email address:

ashenafibeletescienceh@gmail.com   (A. B. Lejamo), hgoldnet@gmail.com  (Z. G. Eticha), hawwiallah@yahoo.com (A. D. Jarra) *Corresponding author

 

Abstract

Dye Sensitized solar cells were made using two locally available plants, Damakase (Ocimum lamiifolium) and Dambursa (New plant) used to extract the natural dye. The pigment was extracted using four solvents, ethanol, methanol, 0.1M hydrochloric acids and distilled water. Then to construct the DSSCs indium tin oxide immersed in the natural dye were used asa counter electrode and Nano crystalline ZnO were act as a working electrode, iodide/tri iodide were placed in between as an electrolyte. The absorption peak and its corresponding wavelength were measured, and then by varying the resistance value, the open circuit current and potential was calculated. Finally from the results the fill factor, performance efficiency and the incident photon conversion efficiency (IPCE) were calculated. At the end the calculated value revealed that, a pigment extracted from Dambursa leaf using solvent ethanol have relatively maximum efficiency and current densities with a value of 0.3675 and 0.264mAcm-2 respectively. Keywords: Natural Dye, Solvents, Electrode, Fill Factor, IPCE

To cite this article:

Ashenafi Belete Lejamo, Zekarias Gebreyes Eticha, Allah Dekama Jarra. Dye-Sensitized Solar Cell Using Natural Dye Extracted from Damakase (Ocimum Lamiifolium) and Dambursa (New Plant). Advances in Materials Chemistry. Vol. 1, No. 2, 2017, pp. 55-61.  doi: 10.11648/j.amc.20170102.12

Received: May 22, 2017; Accepted: June 5, 2017; Published: August 1, 2017

Introduction

Dye-sensitized solar cell (DSSC) has recently penetrated research and development lines of renewable energy, exploited as a promising concept and simple alternative power source [1]. DSSC offers advantages of low fabrication cost, easy preparation methods, and minimal recombination losses as the role of the semiconductor in the DSSC device is merely to conduct the injected majority charge carriers [2] while the minority carriers are carried by the electrolyte. Recently, ZnO, with similar band gap to that of TiO2, appears to be an alternative material for the fabrication of high efficiency DSSCs. A DSSC is composed of a transparent conductive oxide substrate, a wide band gap semiconductor, photosensitizer (dye), a redox electrolyte (usually comprised of iodide/tri-iodide) or p-type

semiconductor and a counter electrode [3-6]. Due to their aforementioned unique properties they have been proposed as alternative photo electrodes in DSSCs in order to achieve better performance [7-8] However, the efficiencies of these cells were found unsatisfactory compared to those of liquid electrolyte. The two main reasons are: the low conductivity of molten salts, organic polymers and polymer electrolytes and bad contact between the dye and ZnO porous film surface and the p-type semi-conductor for solid DSSCs.

1.1. Operational Principle and Structure of DSSC

The dye-sensitized solar cell, DSSC, consist of a photo active working electrode and a counter electrode contacted by a liquid redox electrolyte.

 

%d bloggers like this: