Ethiopian Lawyer: Disability Advocate Yetnebersh Nigussie Receives Right Livelihood Nobel Prize Award September 26.2017


 INTERVIEW                                                                                                                                             By Aarni Kuoppamäki

YN
 Yetenebersh Nugussie

The Ethiopian lawyer spoke with DW about the importance of education and supporting the disability community in Africa and around the world. The award honors those who have found practical solutions to global problems.

DW: You lost your eyesight when you were five years old. Some people in your family considered it to be a curse, but today you say the loss of your eyesight was an opportunity. Why?

Yetnebersh Nigussie: Many people in Ethiopia think that someone’s disability is due to a curse because of a fault that their family has committed. I say that my blindness was an opportunity, because not many people in my village had the chance to get an education. Because I was blind, I was not considered suitable for an early marriage, which is a common practice in our village. All of my friends got married when they were ten, eleven or twelve. I was the only exception. Education liberated me, and allowed me to become who I am today.

According to the World Health Organization (WHO), you are one out of more than a billion people who are living with a disability. For many years you have advocated for the rights of people with disabilities. Which achievement are you most proud of?

Every little milestone is a big achievement, but I can highlight some in my life. The first is my education. The second is my decision to study law, because law was considered to be a men’s subject in Ethiopia. I am among the first three blind women who went to law school.

The next one is the establishment of the Center for Students with Disabilities in the Addis Ababa University, because there was no institution responsible for them beforehand. Now nearly all universities in Ethiopia have a similar organization.

 

Advertisement

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የዋናዉ ግቢ የሪኮርድና ማህደር (ቤተመዛግብት) አገልግሎት ዋና ክፍል ኃላፊ ከአቶ ደስታ ሐርዲሎ ጋር ቆይታ፤


Picture3Interview
የLINK-UP Library Newsletter አዘጋጅ
አቶ ደስታ ሐርዲሎን  ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ 

በዚህ ርዕስ ሥር ይዤላችሁ የቀረብኩት  ቤተኛችን የሆኑትን የሪኮርድና ማህደር ዋና ክፍል ኃላፊ አቶ ደስታ ሐርዲሎን ነዉ።  እኚህ ሰዉ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዉስጥ  ለ 41 ዓመታት የረዥም ጊዜ አገልግሎት በማበርከት ወደፊት ከመስከረም 16 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ጡረታ ለመዉጣት በዝግጅት ላይ ይገኛሉ። “እረ ስንቱ! የቤቱን (የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲን) ዉለታ  እና ትዝታ አልረሳዉም ይላሉ።

 LINK-UP:  የሕይወት ታሪክዎን  ባጭሩ ቢገልጹልኝ?

አቶ ደስታ ߹በ1951ዓ.ም. ልዩ ስሙ አሎሌ በሚትባል መንደር ተወለድኩ ። ለአባቴ የበኩር ልጅ ነኝ። ዕድሜዬ ለትምህርት ሲደርስ በከምባታና ጠምባሮ ዞን ጠምባሮ ወረዳ ሙዱላ ከተማ  ቅዱስ ገብርኤል 1ኛ ደረጃ ት/ቤት߹  የ2ኛ ደረጃ ትምህርቴን አዋሳ ታቦር ከ/2ኛ /ደረጃ ት/ቤት እና የመጀመሪያ ዲግሪዬን በሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ  በማኔጅመንት የትምህርት መስክ አጠናቅቄአለሁ።  

LINK-UP: በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ቆይታዎ በኮሌጅ እና በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ከተላያዩ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ሠርተዋል።  ሰለዚህ  የነበርዎትን የሥራ ግንኙነትና አፈጻጸምን  በተመለከተ   ባጭሩ ቢገልጹልኝ?

አቶ ደስታ߹ በዩኒቨርሲቲ የሥራ ቆይታዬ ከተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ጤናማ እና መልካም የሥራ ግንኙነት በመፍጠር ሥርዓት ባለዉ መልኩ የመንግሥት ደንብና መመሪያ በመጠበቅ መደበኛ ሥራዬን በአግባቡ ሳከናዉን ነበር አሁንም በማከናወን ላይ እገኛለሁ።

LINK-UP:በአሁኑ ወቅት  የሪኮርድና ማህደር አያያዝ እና አደረጃጀት አገልግሎት አሰጣጥ ምን ይመስላል?

አቶ ደስታ߹ በካይዘን አሠራር   በአምስቱ “መ” ዎች 1.ማዘጋጀት 2.መለየት  3.ማስቀመጥ 4. ማዛመድ 5.ማላመድ መሠረት የሚንቀሳቀሱ/Active files/ እና የማይንቀሳቀሱ/Dead Files/  መዛግብትን በአግባቡ ለይቶ በማደራጃት ለተጠቃሚዉ ማህበረሰብ  ቀልጣፋ የሆነ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

Picture2 Lecture
አቶ ደስታ የሪኮርድና ማህደር ዋና ክፍል  የመዛግብት አደረጃጀትና አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ ማብራሪያ ሲያደርጉ 

LINK-UP:በዩኒቨርሲቲዉ የሪኮርድና ማህደር ዋና ክፍል አሠራር ወይም አደረጃጀት ዙሪያ መታረም ያለባቸዉ ድክመቶች እና መሻሻል አለበት የሚሉት ጉዳይ ይኖራል?

አቶ ደስታ߹  መሻሻል ያለበት ጉዳይ የክፍሉን የሰዉ ኃይል በትምህርት ዝግጅት ብቃት ባላቸዉ ባለሙያዎች ማጠናከርና አሠራሩንም በዘመናዊ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ማድረግ ነዉ እላለሁ።

LINK-UP: በትርፍ ጊዜዎ ምን ማድረግ ያዘወትራሉ?

አቶ ደስታ߹  በትርፍ ጊዜዬ በመኖሪያ ቤቴ አካባቢ አበባዎች እና ዛፍች መትከል  እና ስፖርት መሥራትን  አዘወትራለሁ። እንዲሁም  በመሥሪያ ቤቴ ደግሞ አበባዎችን እና ፍራፍሬዎችን ተክሎ በመኮትኮት   የቢሮዬን አካባቢዎች  ማስዋብ  አዘወትራለሁ።

Picture1DEsta Prunning
ቶ ደስታ  የሰዉ ሀ/ሥ/አ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ፊት ለፊት  የተከሏቸዉን አትክልቶች ሲኮተኩቱ

LINK-UP: ጠቅለል ባለ መልኩ ማስተላለፍ የሚፈልጉት አጠር ያለ  አጠቃላይ የሆነ መልዕክት  ካለዎት? ቢገልጹልኝ?

አቶ ደስታ߹

ቀደም ሲል የመዝገብ ቤት አመጣጥ߹ አደረጃጀትና አሠራር ታሪክ ራሱን የቻለ አካሄድና ሂደት ያለዉ ሲሆን  በሀገራችን  በመዝገብ ቤት  ዙሪያ ሥራዉን የሚያንቀሳቅሱ ሠራተኞች  ማንበብና መጻፍ  የሚችሉ ብቻ ነበር።

በአርካይቫል ሳይንስ  ሙያ ዙሪያ  የሰለጠኑ  ባለሙያዎች  ካለመኖራቸዉ የተነሣ  ለሙያዉ ማሕበረሰብም ያለዉ ግንዛቤና አመለካከት  የተዛባ  ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ  የሚሰጠዉ ትኩረት እየዳበረ ከመምጣቱ የተነሣ ምንም እንኳ  የነበረዉ የተዛባ ግንዛቤ   የተቀረፈ ቢመስልም  በሪኮርድና ማህደር አገልግሎት ክፍል  ዉስጥ የሚመደቡ ሠራተኞች በትምህርት ዝግጅት ብቁ የሆኑ  ሲሆን  ነገር ግን በአሁኑ ወቅት አልፎ አልፎ  አገልግሎት አላቸዉ በሚል ሰበብና በዘፈቀደ  ከሙያዉ ጋር ተያያዥነትና ዝንባሌ የሌላቸዉን  ሠራተኞች  በመመደብ  ሥራዉን እንዲያከናዉኑ የማድረግ  ሁኔታዎች ስለሚስተዋሉ  የሚመለከተዉ ክፍል  በዚህ አካሄድ ዙሪያ ተገቢዉን ጥንቃቄ ቢያደርግ  ለክፍሉ ሥራ ጤናማ  ክንዉን መልካም ነዉ እላለሁ።

በአሁኑ ወቅት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የመምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች ማህደሮች  ቁጥር  ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ እየጨመረ በመሄድ ላይ ነዉ ። የሰዉ ሀብት የሪኮርድና  ማህደር  አገልግሎት መረጃ ߹የፋይንንስ በጀት አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ሰነዶች በልዩ ሁኔታ ’Secured’ በሆነ ቦታ ወይም ክፍል ዉስጥ  ከእሳት አደጋ ሊታደጉ በሚችሉበትና እርጥበት ሊያገኛቸዉ በማይችልበት ሁኔታ  ትኩረት ተስጥቷቸዉ ተገቢ ክፍሎች ዉስጥ የማደራጀት ሥራዎች ቢሠሩ መልካም ነዉ በማለት߹

በረዥም ዘመን ቆይታዬ  በመደበኛ ሥራዬ  ዙሪያ  ቀደም ሲልና እስከ አሁን ድረስ ከዩኒቨርሲቲዉ የሥራ ኃላፊዎች እና ማሕበረሰብ  ለተደረገልኝ ድጋፍና ማበረታታት  በዚህ አጋጣሚ  ላመሰግን እወዳለሁ ብለዋል።

በመጨረሻም መደበኛ የሥራ ሰዓትን በተመለከተ አንድ አባባል አለ ካሉ በኃላ “ስንት ነዉ ሰዓቱ  የሠራም ያልሠራም እኩል ገባ ቤቱ”  የሚል ቁምነገር አዘል አባባል በማከል የተደረገላቸዉን ቃለመጠይቅ  ቋጭተዋል።

አስተያየቶች  እና ሽልማቶች  ለአቶ ደስታ ሐርዲሎ በሥራ ዘመን ቆይታቸዉ

ዶ/ር ገረመዉ ኃይሌ ለአቶ ደስታ ሐርዲሎ በቁጥር ዲ/2405/83 በቀን  24/07/83 ዓ.ም. ከጻፉት የአስተያየት ደብዳቤ ዉስጥ የተቀነጨበ የምስክርነት ቃል የሚከተለዉን ይመስላል፤

ለሚመለከተዉ ሁሉ

ʺ…… የሥራ ጉብዝናና ጥራት ብቻ ሳይሆን የተሰጣቸዉን ሥራ በሙሉ  በታማኝነት የመፈጸም ችሎታቸዉ በጣም የሚያስደንቅና እርሳቸዉን  የሚያስከብር ነዉ ። አሁን ያሉበት የሥራ ድርሻ በረዳት ሬጅስትራር ክፍል ሥር ሲሆን  የተማሪዎችን የአካዳሚክ ሪኮርድ ማስላት߹ እስታቲስቲክስ ማዉጣት߹ የሴሚስቴር ዉጤት ማቀነባበር ናቸዉ።

አቶ ደስታ ሐርዲሎ በመምህራን በሌሎች ሠራተኞች እንዲሁም በተማሪዎች የሚደነቁት߹የሥራቸዉ ልክ መሆን ߹የዉጤታቸዉ ጥራት ߹የአፈጣጠናቸዉና ፍጹም ታማኝነታቸዉ ነዉ።

አቶ ደስታ ሐርዲሎ ሥራቸዉን የሚሠሩት መንግሥት በአወጀዉ  ሰዓት ብቻ ሳይሆን በትርፍ ሰዓታቸዉ ጭምር ነዉ። የዕዝ መስመራቸዉን ጠንቅቀዉ የሚያዉቁ ግለሰብ ሆነዉ አግኝቻቸዋለሁ። እንዲሁም ዲስፕሊናቸዉ ߹የሥርዓት አክባሪነታቸዉ በጣም የሚያረካ ነዉ።…….”

ለሚያጋጥማቸዉ ሁሉ መልካም ዕድል እመኝላቸዋለሁ።

ኢትዮጵያ ትቅደም

የማይነበብ ፊርማና ማህተምአለዉ

ገረመዉ ኃይሌ(ዶ/ር)

                              ዲን

ፕሮፌሰር ዝናቡ ገ/ማሪያም ለአቶ ደስታ ሐርዲሎ በቁጥር ዲ/1511/91 በቀን  23/04/91 ዓ.ም. የጻፉት  የአስተያየት ደብዳቤ የምስክርነት ቃል የሚከተለዉን ይመስላል፤

ለሚመለከተዉ ሁሉ

በኮሌጁ  በነበረኝ የአካዳሚክ ረ/ዲንነትና አሁን ባለኝ የዲንነት ኃላፊነት ወቅት ከእርስዎ ጋር ባለኝ የሥራ ግንኙነት  ስለእርስዎ አገልግሎትና የሥራ አስተዋጽኦ ያለኝን አስተያየት እንድጽፍልዎት በጠየቁኝ መሠረት እንደሚከተለዉ  ለመግለጽ እወዳለሁ።

1.ከማህደርዎና የእርስዎን የሥራ ዕድገት በመመልከት መረዳት እንደሚቻለዉ ከዝቅተኛ  ጊዜያዊ ሠራተኝነት  በመነሳት አሁን ላሉበት የሪኮርድ አጠባበቅ ኃላፊነት  መድርስዎ   በሥራዎ ትጉህና ታታሪ  መሆንዎን  በግልጽ ያሳያል።

  1. እኔም በቅርቡ ተከታትዬ እንዳየሁት ደከመኝ ሰለቸኝ የማይሉ፤ የእረፍት ጊዜዎን  ሳይቀር መስዋዕት  አድርገዉ  የለዕረፍት የሚሠሩና  ከግል  ጉዳይዎ ይልቅ ለተመደቡበት ሥራ ቅድሚያ  የሚሰጡ  ሠራተኛ መሆንውን  መረዳት ችያለሁ።3. እርስዎ ያሉበት የተማሪዎች ሪኮርድ ክፍል ከፍተኛ ጥንቃቄና ታማኝነትን የሚጠይቅ በመሆኑ  ሠነዶችን በሚስጢር በመያዝና  ብኩንነት ሳይታይብዎት ለረዥም  ጊዜ  መሥራትዎ ኮሌጁ  ከሚኮራባቸዉና ከሚተማመንባቸዉ  ሠራተኞቹ አንዱ አድርጎዎታል
  2. ከዚህም የተነሳ የኮሌጁ ኮከብ ሠራተኛ በመሆን ለምሥጉን ሠራተኞች የሚሰጠዉን ሽልማትና ምሥጋና አግኝተዋል።

በአጠቃላይ እርስዎ በሥራ ክብርነት የሚያምኑ፤ ኃላፊነትዎን  በብቃት  የሚወጡ፤ በሥራዎ  የሚደሰቱ መመሪያን ና ደንብን ጠንቅቀዉ  ተረድትዉ  በሥራ  የሚተረጉሙ ሠራተኛ  መሆንዎን ለመረዳት የቻልኩ  መሆኔን ስገልጽልዎት  ለወደፊቱ  ከዚህ የበለጠ ኃላፊነትን የመሸከም ጥረትዎ እንደማይቋረጥ  በመተማመን ነዉ።

በወደፊቱ የኮሌጁ ቆይታዎ  መልካም የሥራ ጊዜና የተሻለ ዕድል እመኛለሁ።

ከሠላምታ ጋር

የማይነበብ ፊርማና ማህተም አለዉ

                                    ዝናቡ ገ/ማርያም   ዶ/ር    ዲን

 ሽልማቶች

  • በ1989 ዓ.ም.በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮከብ ሠራተኛ በመሆን በ1ኛ ደረጃ ተሸላሚ߹Picture5ZA
  • በግብርና  ኮሌጅ 20ኛ ዓመት ምሥረታ በዓል ላይ ከ20 ዓመት በላይ በማገልገል  ምስጉን ሠራተኛ በመሆን ተሸላሚ߹Picture6MA

 

Desta Hardilo:

He holds his BA in Management in 2008 Eth.C. Besides he has been trained :

  • In Records Management training conducted by Ethiopian Management Institute.
  • In Customer Service, Human Resource Governance & Emotional Intelligence training conducted by HU-CPDR/Nothed-DEG Project

Contact Address:

        Office Phone   +251 0462200291

        Mobile Phone: +251 0916863232

%d bloggers like this: